Get Mystery Box with random crypto!

የነቢዩ ﷺ የዘር ሀረግ እሳቸውም ሙሐመድ ብን ዐብዲላህ ብን ዐብዲል ሙጦሊብ ብን ሃሽም ብን ዐብዲል | አፍሪካ ቲቪ | Africa TV1

የነቢዩ ﷺ የዘር ሀረግ
እሳቸውም ሙሐመድ ብን ዐብዲላህ ብን ዐብዲል ሙጦሊብ ብን ሃሽም ብን ዐብዲል
መናፍ ብን ቁሶይ ብን ኪላብ ብን ሙርራ ብን ካዕብ ብን ሉአይ ብን ጋሊብ ብን ፊህር
ብን ማሊክ ብን ነድር ብን ኪናና ብን ኹዘይማ ብን ሙድሪካ ብን ኢልያስ ብን ሙዶር
ብን ኒዛር ብን መዕድ ብን አድናን ናቸው።
ዐድናን ደግሞ የመስዋዕቱ ኢስማዒል ብን ኢብራሂም ልጅ ናቸው። በመሆኑም የአላህ
መልእክተኛ ﷺ ከምርጦች ሁሉ ምርጥ የተመረጡ ናቸው።

ከዋኢላ ብን አል አስቀዕ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፤
“አላህ ከኢስማዒል ዘር ኪናናዎችን መረጠ፣ ከኪናናዎች ደግሞ ቁረይሾችን መረጠ፣
ከቁረይሾች ደግሞ በኒ ሃሺምን መረጠ፣ ከበኒ ሃሺምም እኔን መረጠ።”

አባታቸው
ዐብዱላህ ብን ዐብዲል ሙጦሊብ ናቸው። እሳቸውም ከቁረይሽ ወጣቶች በሸጋነት ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነበሩ።
እናታቸው
አሚና ቢንት ወህብ ስትሆን አባቷም ከበኒዙህራ ጎሳ የተከበረ ዘር ያላቸውና የጎሳው መሪም ነበሩ።
አያታቸው
ዐብዲል ሙጦሊብ ብን ሃሺም ሲሆኑ የቁረይሾች መሪ ናቸው። በርካታ የተከበሩ ስነ-ምግባር ያላቸው ሲሆን የዘምዘም ውኃ ጉድጓድን በመቆፈር ይታወቃሉ።

—————————————————
አፍሪካ ቲቪ
የሕይወት ጎዳና
ናይል ሳት | 11554 | V | 27500

በማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከታተሉን | Follow us፡
ዩትዩብ || ሰብስክራይብ ለማድረግ ፡
https://bit.ly/388zRIJ
ፌስቡክ || ላይክ ለማድረግ :
https://bit.ly/2WCp9Fn