Get Mystery Box with random crypto!

#Block......un block ቀን አትናፍቀኝም ጭራሽ ትዝ አትለኝ ስምህም ሲጠራ ድን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#Block......un block


ቀን አትናፍቀኝም
ጭራሽ ትዝ አትለኝ

ስምህም ሲጠራ ድንቄም አልደነግጥ
ፎቶህንም ሳየዉ ልቤ አትልም ድልቅ።

ድንገት ትዝ ካልከኝ
ራሴን 'ረግማለሁ
ምን አጃጅሎኝ ነዉ ብዬ እገረማለሁ።

ያንተ ስም ሲጠራ
ብዙ መሠል ስሞች ይመጣል ከኔ ጋር
ሌላም አስባለሁ ከትዝታ ጋራ

የአፍቃሪዬን ብዛት..............

በቃ ረስቻለሁ ብዬ ስደሳሰት
Block

ልክ ሲመሻሽ ደርሶ
ስምህ ይጨንቀኛል
ሳቅህ ይሰማኛል

እንደ ቀኑ አይደለ ፎቶህ ግርማ አለዉ
መፀፀት አይደለ ልቤ አምጪዉ ነዉ ሚለዉ

ምን አተሽ ነዉ ከሱ
እድል ነበር እሱ

እያለኝ እንደቀልድ
ቀን ያመንኩት ልቤ ካንተ ጋራ ሲነጉድ
እንዲሁ አነጋለሁ
ስላንተ አነባለሁ።


ከዛ..............
un block ሳደርግህ ራሴን አገኛለሁ።

ድሮስ ከጨለማ ምን ነበር ጉዳዬ
አንተ መቼም አታዉቅ ሆነ እድል ፈንታዬ

አንተና ጨለማዉ ግብራችሁ አንድ ነዉ
ብቸኝነት ፍርሀት መልሳችሁ ዝም ነዉ።

ደሞ ዛሬም ነጋ.................


ተፃፈ በትዝታ ወልዴ


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19