Get Mystery Box with random crypto!

(አባት ሀገራችን) ታደሰ ደምሴ እኔ ግን የምለው ... አባትን ሳያውቁ እናት እንደምነው? ያባ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

(አባት ሀገራችን)

ታደሰ ደምሴ

እኔ ግን የምለው ...
አባትን ሳያውቁ እናት እንደምነው?
ያባት ሥም ተትቶ ሁሌ በናታችን መጥራት ለምነው?
ወይንስ....
ወይንስ ኢትዮጲያም ጸንሳ ምትወልደው በድንግልናነው!???

እንዴት ነው ሁልጊዜ "እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ"
አባት አልነበር ወይ አለኝታና መኩሪያ!

እኔ ግን የምለው...
በዚህ በጭንቅ ቀን በናታችን ባዕት መኖር ስንነፈግ
ምን አይነት ፍዘት ነው ያባት ዓገርን ውርስ ወጥቶ አለመፈለግ!?

ኧረ እንቃ ጎበዝ...
ይችን እናት አገር ደፈር እንበልና አንድ ቃል እንጠይቅ
ካባታችን ወስዳ ሸሽጋ ታኑረን ተረሽነን ሳናልቅ!!!

ምንድነው ዝምታው ማንም እየተነሳ እንዲ እየደፈረን
አባት የለን እንደሁ ወይ ቁርጡን ታስታውቀን
ከቁባቶቿ እንደሁ ባሻት ተፈንግላ ድንገት የጸንሳን

እውነት አባት ካለን...
ከቀያችን ገፍቶ የሚያሳድደንን ወግቶ ይግደልልን
ይህም ባይሆንኳ በቀል ካልወደደ ወይ ከሱ ይውሰደን!

ሀሳብ ካለዎ

@Maryam21161