Get Mystery Box with random crypto!

መቼ ናት ፀደዬ? መሬት ለመለመች ፀሀይ ደምቃ ወጣች ፍክት ፍክት አሉ ካሉበት አበቦች ግሩም መአዛ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

መቼ ናት ፀደዬ?

መሬት ለመለመች ፀሀይ ደምቃ ወጣች
ፍክት ፍክት አሉ ካሉበት አበቦች
ግሩም መአዛቸው መንደሩን አወደው
ፀደይን ተቀበሉ ክረምትን ሸኝተው
ፍቅሬ ትዝታዬ
የእኔ ግን ፀደይ ገና ገና አልገባም
ደመናን አባራ ፀሀዬ አልወጣችም
ትዝ ይልሻል አይደል
ክረምት ገባ አሉ ብዬ ያጫወትኩሽ
ትዝታና ፍቅር በልቤ አስቀምጠሽ
በዛ በበረዶ ስንገበገብልሽ
ትዝ ይልሻል አይደል
ዶፍ እየዘነበ እኔን ሲያቃጥለኝ
የክህደትሽ መርዶ እበድ እበድ ሲለኝ
አስታወሽው አይደል
ከእልፍ ሰው መሀል ብቻዬን ሳወራ
ስስቅ ሳለቅስ አንዴ ስምሽን ስጠራ
መሸከም አቅቶት ናፍቆትሽን ልቤ
በመብረቅ ነጎድጓድ ትዝ ስትይኝ ውቤ
ዛሬ ላይ ግን ቆንጂት
አሮጌው አልፎ በአዲስ ተተክቷል
ለብዙዎች ደስታ ሰላም ይዞ መጥቷል
እኔም እናትዬ
እልህ ከቁጭት ጋር ተደምሮ ይዞ
ልክ እንደተበላ በቁማር አስይዞ
እህህ እያልኩኝ በማያባራ እንባ....
ብዬ እንደከተብኩ እያልኩ ፈራ ተባ
ደህና ነኝ ደህና ነኝ እሷን ረሳኋት
ህመሙ ወጥቶልኝ ሳቄን አገኘሁት
እያልኩ ማወራበት ደስታ እኔን ከባ
መቼና እንዴት ይሁን የኔ ፀደይ 'ምትገባ??????


ሰላም( Selito)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19