Get Mystery Box with random crypto!

ነበረ የዛሬን አያርገውና ትናንትና ከትናንትም ወዲያ እወድሽ ነበረ ፣ ግን ምን ያደርጋል ባ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ነበረ

የዛሬን አያርገውና ትናንትና ከትናንትም ወዲያ እወድሽ ነበረ ፣
ግን ምን ያደርጋል ባደረግሽው ነገር ልቤ ተሰበረ።

ነበረ ነው ደሞ

አዎ! እወድሽ ነበረ

ገላሽን አቅፌ
ከንፈርሽን ለክፌ
ዓይንሽን አይቼ
ላገኝሽ ጓጉቼ
ብዙ ቀን አቃለሁ፣
አንቺን ተርቤያለሁ ።
ብዬ የነገርኩሽ ቀን ፣
ሰቀቀን ሰቀቀን ።

አዎ! ሰቀቀን ነበረ ካንቺ ፊት ያየሁት

እኔን ተሳቀሽኝ
ገፍተሽኝ ገፍተሽኝ
ጥለሽ ጠፋሽና
ቤቴን አርገሽ ወና፣
ልቤ ተሰባብሮ
ብቻውን ኖሮ... ኖሮ... ኖሮ... ኖሮ...
ከዛም ተቀይሮ፣
ከእለታት ባንዱ ቀን
"ልቤን የሚጠግን አንድ ሰው አገኘሁ"
ብዬ ያወራሁ እለት ፣
ልቤን ልታፈርሺው ደግሞ መጣሽለት ።

ምን አይነት ክፉ ነሽ ?

እያለ ሲያወራ እኔም ሰምቻለው ፣
ሞኛሞኝ አፍቃሪሽ ፍቅርሽ ያሰከረው ።

ታድያ አሁን እኔን "አፋልገኝ" ትያለሽ?
ምን አይነት ሞኝ ነሽ?


አላወቅሽም እንጂ ብታቂማ ኖሮ፣

እንዲያ የተከፋ
እንዲያ የተገፋ
ካንቺ ዘንድ ቢጠፋ
እኔ 'ልፈርድበትም
የተሰበረ ልብ  ይሰደዳል የትም።

                   ክንዴ ሙላት

                 


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19