Get Mystery Box with random crypto!

በታሪክ ለሀይማኖቶች መከፋፈል እንደ ዋና ዋና ጥቅል ምክንያት ሁለቱ ይጠቀሳሉ :: አንደኛው ም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በታሪክ ለሀይማኖቶች መከፋፈል እንደ ዋና ዋና ጥቅል ምክንያት ሁለቱ ይጠቀሳሉ ::

አንደኛው ምክንያት ከስልጣን(authority )የሚመነጭ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከእምነት ( doctrine ) የሚመነጭ ነው::
በተለይ በክርስትና ታሪክ ከዘር ልዩነት የሚመነጭ ዲኖሚኔሽን ወይም ሴክት የለም ::ወይም አልታየም ::

ለምሳሌ የኢስተርን ኦርቶዶክስን:የካቶሊክንና የፕሮቴስታንት መከፋፈል ብናጠና ከሁለቱ ምክንያትች በ authority እና doctrine የመጡ እንጅ በዘር ወይም በቋንቋ ልዩነት የተፈጠሩ አይደሉም ::እንዴውም በታሪክ የልዩነት ምንጭ ተብለው የሚጠቀሱ አብዛኛዎቹ እምነት ወይም Doctrine ተኮር ልዩነቶች ናቸው ::
ለምሳሌ :-በDoctrine ዙሪያ የሚጠቀሱ

1- Nature of Jesus
( የእየሱስን ባህሪ አስመልክቶ ከ Devine ና salvation አንፃር በመመርመር ላይ ያለ ልዩነት)

2- Biblical hermeneutics
የመፅሃፍ ቅዱስ ጥናትን አስመልክቶ የትርጏሜ ሜትዶችና ፕሪንስፕሎች ላይ ያለ ልዩነት

3- Theology
የክርስትናን አስተምሮትና ተግባረት መሰረት አድርጎ የትኩረት ማዕከልን ፕራዮታይዝ የማድረግ ልዩነት primarily upon the texts of the old Testament and New Testament , as well as Chrestian tradition.
ቴዎሎጂያንስ መፅሀፍ ቅዱስን መነሻ አድርገው በሚሰጡ አናሊሲስና አርጊውመት ያለ ልዩነትም ይጨምራል::

4-Ecclesiology
ይሄ ደሞ መሰረት የሚያደርገው ጥንታዊ ቸርቾችን በማጥናትና ከክርስትና ኦሪጅንና ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ዝምድና በመመርመር ብያኔ የሚሰጥበት ዘርፍ ነው ::በዚህም ልዩነት ይኖራል ::

5-Eschatology
ይሄ ደሞ በሁሉም ክርስቲያኖች የመጨረሻ ዕጣ ፈንታና በአጠቃላይ ስነ ፍጥረት የመጨረሻ መጨረሻ ዕጣ ፈንታ ላይ የመፅሀፍ ቅዱስን ቴክስቶች መነሻ አድርጎ የሚያጠና ብያኔ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ዝርዝር ጉዳይ ላይም ልዩነቶች ያሉ ሲሆን

በ Authorities ያሉ የልዩነት ምንጮች ደግሞ

1-The authority of apostolic succession
የሓዋሪያትን የስልጣን ተዋረድና መተካካት አስመልክቶ ያለ ልዩነት

2- Papal primacy
በስፉት primacy of the bishop of Rome የሮማን ካቶሊክ ቸርችና የኢስተርን ኦርቶዶክስ ቸርች የተለያዩበት የመጨረሻውን ፖፕ ሃይራርኪ አስመልክቶ ያለ ልዩነት ሲሆን ይሄም ከቋንቋና ዘር ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ::

እንግዲህ ከላይ በተዘረዘሩት የልዩነት ምንጮች ውስጥ ቋንቋና ዘርን አስመልክቶ የተፈጠረ የልዩነት መስመር በታሪክ አልታየም :: በሀገራችን ምን እየተፈጠረ ነው ??
ሀይማኖትን ከአንድ ዘርና ቋንቋ ጋር ብቻ አጣብቀው የሚያስቡም ሆነ ቋንቋና ዘርን እንደ ሽብልቅ መፈልቀቂያ አድርገው የሚያስቡ ሰዎች ከዚህ ጠባብ ሣጥን ቢወጡ ጥሩ ነው::

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19