_ ልጅነት ይዞሻል መውደዴን ስትሰሚ : ሳቅ ያሸንፍሻል ናፍቆቴን ሲነግሩሽ : ሹፈት ይቀናሻል ሰው ማፍቀር መሳሳት : ጨዋታ መስሎሻል ልጅነት ይዞሻል ችለሽ ባልሰማሽው : የመውደዴ ጥጋት ምንድን ነው መለመን? ምንድን ነው ፊት መንሳት? ህይወት ዥዋዥዌ : አይደለም ጨዋታ ፍቅር ዥዋዥዌ : አይደለም ጨዋታ ህይወት ማለት ፍቅር ፍቅር ማለት ህይወት : ህልምና ትዝታ የመውደዴን ቃላት : አልሰማም ማለትሽ የማፍቀሬን ሀሳብ : እንዲ ፊት መንሳትሽ ሲመስለኝ ሲመስለኝ : በልጦ ልጅነትሽ ያ እግዜሩ ታላቁ አፍቃሪን በመግፋት : ፍቅርን በመናቅሽ እንደምን ይቆጣ? እንደምን ያዝንብሽ? ብዙም አትቆጣ : ተው አትዘንባት እሷ ምን ታውቃለች : ልጅነት አለባት ሀጥያትሽ ብዙ ነው : አንቺ አልታወቀሽም ከእግሩ ስር አልወደቅሽ : ይቅርታ አልጠየቅሽም እኔ እወድሻለሁ (ከነልጅነትሽ) ካለልጅነትሽ ለዚህ ነው አምላክን ተው ማራት እያልኩኝ የምለምንልሽ . . . ባላወቀው ገላሽ : ሀጥያትሽን የጫርኩት እኔ ነኝ ጠላትሽ : ተገፋ የተባልኩት የቅጣትሽ ምክንያት : የሰይጣንሽ አቻ ከምድር ላይ ሆኜ : በመለመን ብቻ በመፀለይ ብቻ ሀጥያትሽን ማጠቡን : ማመን ስላልቻልኩኝ ካለበት ልነግረው ከሰማይ መንበሩ : አንፃት ልለው ሄድኩኝ ተጫወች እስከዛው.... በአቤኒ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19 7.2K viewsAbela, 05:54