Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞንኛ ባለፈው የመገናኛን ጎዳና በእግሬ ስዠልጠው፥ አንዱ ለማኝ ግብዳ መጽሀፍ ቅዱስ ገልጦ ያ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሰሞንኛ

ባለፈው የመገናኛን ጎዳና በእግሬ ስዠልጠው፥ አንዱ ለማኝ ግብዳ መጽሀፍ ቅዱስ ገልጦ ያነብባል፤ በአቅራቢያው እሚተራመሱ የጎዳና ፓስተሮች ልባቸው ተነክቶ ይመጸውቱኛል ብሎ አስቦ ነው፤ መቸም ዘንድሮ ትንሽ እርድና ካልጨመርክበት በማሳዘን ብቻ ጠብ እሚል ነገር የለም፤ ያደባባይ ሰባኪዎች ግን ባላየ ያልፉታል፤ እንዲያውም አንዱ ሰባኪ “ በውኑ እምታነበውን ታውቀዋለህን?” አለና በባዶ ሆዱ፥ አርባ ደቂቃ ያክል አዛገው፤ በመጨረሻ ለማኙ ተስፋ ቆርጦ፥ ብቻ ሳይሆን ተስፋ ፈልጦ” ከፌስታሉ ውስጥ Get rich or die tryin የሚል መጽሀፍ አውጥቶ መጨምጨም ጀመረ::

ስሙማ ! አንዳንዴ ምን ስሜታዊ እንደሚያደርገን ልንገምት አንችልም፤ ዓለማዊ ነኝ የምለው ሰውየ,፥ በሀይማኖት ዙርያ ጎራ ለየቼ ስከራከር ተገኘሁ ቢባል ማን ያምናል! ሰሞኑን አንድ የፌስቡክ ጉዋደኛየ “ በውቄ ምን አጥፍቼ ነው አንፍሬንድ ያደረግከኝ?” የሚል የወቀሳ መልክት በውስጥ መስመር ላከልኝ::

“ አባ ሳዊሮስ የተባለውን አማጺ ካህን ፕሮፋይል ፒክቸር አድርገህ ከኔ ጋ ጉዋደኛ ልትሆን አትችልም” ብየ መለስኩለት::

“ በውቄ አይንሽ ይሸቅላል እንዴ? ፎቶው የሳዊሮስ አይደለም ! የአቡነ ማቲያስ የወጣትነት ፎቶ ነው “ ሲል መለሰልኝ፤

የተናገረው አሳማኝ ቢሆንም በአይኔ ላይ ያቀረበው ትችት ደበረኝ::

“ ጭራሽ “ወጣት ሲኖዶስ “ እና “ ሽማግሌ ሲኖዶስ “ ብለህ ልትከፋፍልም ያምርሀል? “ ብየ ቦለክሁት::

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19