Get Mystery Box with random crypto!

ዕድሌ ነው... (መላኩ አላምረው ) . ዕድሌነው... በሚስትልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤ ሳታገባ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ዕድሌ ነው...
(መላኩ አላምረው )
.
ዕድሌነው...
በሚስትልወሰን፣ እኔ ትዳር ሲያምረኝ፤
ሳታገባ 'ምትቆይ፣ አንድም ሴት አትገኝ
.
ዕድሌነው...
እኔዲግሪ ስይዝ፣ ዲግሪ ዋጋ ያጣል፤
ገንዘብ ያለው ሁሉ፣ ዶክትሬት ያመጣል
.
ዕድሌነው...
እኔመድረክ ስይዝ፣ ይፈታል ጉባኤ፤
እኔ መጾም ሲያምረኝ፣ ይሆናል ትንሣኤ።
.
ዕድሌነው...
በቁርባንለመኖር፣ ንሰሐ ስገባ፤
አቁራቢው ፖትልኮ፣ ቤተመንግሥት ገባ።
.
ዕድሌነው...
እኔኳስ ስገዛ፣ ሜዳው ይታረሳል፤
እኔ ቤት ሲኖረኝ፣ ሰፈሬ ይፈርሳል።
.
ዕድሌነው...
ለተሾመሁሉ፣ እንዳልኖርሁ ስለፋ፤
እኔ አለቃ ስሆን፣ የሚታዘዝ ጠፋ።
.
ዕድሌነውና...
ከዕለታትአንድ ቀን፣ መንገሤ ባይቀርም፤
እኔ ንጉሥ ስሆን፣ ሀገሪቱ አትኖርም። 

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19