#ከጎንደር_እስከ_መኧለ #ምዕራፍ_1 #ክፍል_1 (መንደርደሪያ) "ወገኛው ዛሬ ምነው ዝም አልክ እንደበፊቱ ማቅራራቱን ተውከውሳ ነው ወይስ ፉት የምትላት አረቂ እስክታሞቅህ እየጠበካት ነው።(የፌዝ ሳቅ) ኧረ ያዝማሪውን መሰንቆ ድምፁን አስዋጥከው የሆነ ነገር በለው እንጂ(ድጋሚ የፌዝ ሳቅ)"። የሰፈሩ መንደርተኞች ከሰፈራቸው የበቀለውን ደራሲ አብዮት ወጋየሁን የራስ መዥገር ይመስል አለቅህ ብለውታል። ሁሌ ከሚያዘወትርባት ታንጉት ግሮሰሪ ውስጥ በሚናገረው ነገር አብዛኞቹ ጠምደውታል አንዳንዶቹ ደግሞ ልክ እንደ "አሃ..." መርህ ከልብ ያዳምጡታል። ደራሲው ሊናገር የፈለገውን ነገር ከመናገሩ በፊት ስለ አለባበሱ አስተያየት ይጠይቃል...አንዳንዱ "ምነው ዛሬ ደሞ የከሰረን ነጋዴ መሰልከን" ሲሉት አንዳንዱ ደሞ አለባበሱ ሳይጥማቸው "አሪፍ ነው..እእእ..ምንም አይልም" ይሉታል በፈገግታ መልሳቸውን ያብሰለስላል ትንሽ ቆይቶም ስለሰጡት መልስ ለእያንዳንዱ የተቃረነ መልስ ይናገራል በዚህም የተነሳ ከአብዛኞቹ ጥላቻን አትርፏል። የታንጉት ግሮሰሪ ካሉበት ስፍራ እውቅናን አትርፏል በአሁን ሰዓት አንቱ የተባሉ ሰካራሞችን ለሰፈሩ ነዋሪዎች አበርክቷል የግሮሰሪው መስራች ወ/ሮ ታንጉት አንዴት ገበያሽ ደራልሽ ስትባል "እንዲያው ያደረኩት ነገር የለም ለሰፈሬ ታቦት ተስዬ ነው እንጂ" ትላለች የምታምነው አምላክ ወጣት ሳትይ ሽማግሌ አክብሪ(አስክሪ) ያላት ይመስል። ከግሮሰሪው በአንዳንዶቹ አንቱታን በአንዳንዶቹ ደግሞ አንተ የሚል ስምን ካገኙት መካከል አቶ ሳሙኤል ዋነኛ ናቸው(ነው) ። አቶ ሳሙዔል ባለው ትህትና ሰፈርተኛው "ውይ ሳሚዬ የኔ የዋህ......ጋሽ ሳሚ አሳቢየችን..."እና የመሳሰሉትን ሲሉት የሚሰራውን ስራ ልብ ብለው የተረዱት ደግሞ "እጄ ላይ እንዳይጥለው ብቻ..."እያሉ ይዝቱበታል። ስለ ሁሉም የሰፈሩ ሰዎች የሚያውቀው አብዮት ከታንጉት ግሮሰሪ በሚቀማምሳት አረቂ የሰከረ በመምሰል ያዝረጠርጣቸዋል...ከጎናቸው በሚቀመጠው አዝማሪ ስንኞቹን እየወረወረ እስከ አዝማሪው ድረስ ይናገራል የሚረዳው የለም እንጂ። ከምሽቱ 3:13 ሆኗል የአለምን ክፋት የተፀየፈች ይመስል ጨረቃ ከሰማዩ ላይ የለችም...ጭልምልም ብሏል ከታንጉት ግሮሰሪ ወጥተው ወደቤት የሚሄዱት ሰካራሞች የድማዛን ድልድይ ማቋረጥ ይኖርባቸዋል...የድማዛ ወንዝ ድልድይ ጣልያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለ 5 አመታት ቆየች በተባለ ሰዓት የመኸንደሱት ድልድይ ነው...ታድያ ያሁኖቹ ሰዎች አፍርሰው በቻይና አሰሩት የሚል ወሬ ተንሰራርቶ መነገር ከጀመረ ድፍን 3 አመታት ካለፈው 1 አመት ሆኖታል....ደራሲ አብዮት ድልድዩን ባቋረጠ ቁጥር "ከድጡ ወደ ማጡ - ሸሹ እንጂ መች አመለጡ" የምትለውን ስንኝ ሳይወረውር አያልፍም...የጎንደር ክፍለከተማ የሆነችው አዘዞ የድማዛን ወንዝ በሆዷ ታፈሰዋለች ከታንጉት ግሮሰሪ ወደ 25 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የድማዛ ድልድይ ፈርሶ ከተሰራ በኋላ ከጭነት እስከ ተሳቢ ባንድላይ ማሳለፍ ችሏል። የደራሲው አብዮት የፍቅር ታሪክም እዚሁ ተጠንስሷል። አንዳንዴ በሚቀማምሳት አረቂ ብርታት ካገኘ በኋላ "ተቀበል" ይለውና "ጠጅ አይሉት ወይ ጠላ ህመምን ለመርሳት ተገበረ ገላ ምነዋ ብትፈርጂኝ ያሻገርሺኝ ወንዜ አረቂ እና አዝማሪ ተደበላልቀዋል ዛሬ በኔ ግዜ ባንቺ እንዴት ነበሩ በጠጅ ነው እንጂ ባረቂ አልዘመሩ" ይልና በረጅሙ ይተነፍሳል ከዛ በመንሾካሾክ ይመስል "ሃና...የትነሽ..." እያለ ከፊት ለፊቱ የተቀመጠውን አረቂ ይጨልጣል። ይቀጥላል.... ዮኒ ኣታን @yonatoz ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19 5.6K viewsAbela, 17:40