Get Mystery Box with random crypto!

እመ መከራ ****** /በእውቀቱ ስዩም/ ኢትዮጵያ እመ መከራ የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እመ መከራ
******
/በእውቀቱ ስዩም/

ኢትዮጵያ እመ መከራ
የግዜር መመራመሪያው
የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና ፣
የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ ፣
መውድቅ ÷ መውድቅ ÷ መውድቅ ብቻ…

ሰዓሊ /ፀጋልደት/

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19