Get Mystery Box with random crypto!

#ከጎንደር_እስከ_መኧለ #ምዕራፍ_1 #ክፍል_02 (ታሪክ ወደኋላ) ደራሲ አብዮት ወጋየሁ 1 ክፍ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_02 (ታሪክ ወደኋላ)

ደራሲ አብዮት ወጋየሁ 1 ክፍል ቤት ተከራይቶ መኖር ከጀመረ አመታት አልፈውታል በተለያዩ የመድረክ ስራዎች ላይ በመሳተፍ በሚያገኛት ሳንቲም የቀን ቀለቡን እና የቤት ኪራይ ክፍያውን ይሸፍናል ከዛ በዘለለ ለምንም ነገር አይሆነውም አንዳንዴ የቀን ቀለቡን በመሰረዝ ከታንጉት ግሮሰሪ ውሎ ያድራል።
ደራሲ አብዮት ወጋየሁ ከቤቱ ሳይወጣ እዛው በተኛበት የኪስ ቦርሳውን አወጣ...ከቦርሳው ውስጥ የልጅነት ጓደኛውን ፎቶግራፍ ተመለከተ
በመጠጥ የቀሉ አይኖቹ በእንባ ተከበቡ...በደረቁት ትናንሽ ከነፈሩ ላይ የአይኑ እንባ አረጠቧቸው...የገረጣው መልኩ በእንባ ተሞላ...ለብቻው እያንሾካሾከ"የት ነሽ..."ይላል።

#ጎንደር_ዩኒቨርስቲ_የማህበረሰብ_ት/ቤት
( #1990)

"የ 48 አንድ ሁለተኛ ስንት ነው?...እስኪ ማነው ሚነግረኝ...አብዮት እስኪ አንተ ተናገር!..." የ3ተኛ ክፍል ሂሳብ መምህር አብዮትን አይወዱትም ነበር ምክኒያቱም አንድም ቀን ተከታትሏቸው አያውቅም ብዙ ግዜ ወላጅ አስመጥቶታል ብዙ ግዜ አንበርክኮ ገርፎታል ግን ምንም ሊሻሻል ስላልቻለ መምህሩ በእሱ ተስፋ ቆርጧል። "አብዮት አንተን እኮ ነው አትመልስም!" አሁንም ዝም ብሎታል መምህሩ በጣም እየተናደደ መጣ ግን በድንገት "24" ብሎ መለሰ መምህሩ ትኩር ብሎ እያየው "ነገ ቤተሰብህን ማናገር እፈልጋለው" አለው።
አብዮት ከመቀመጫው ተቀምጦ በሹክሹክታ "አመሰግናለሁ" ብሎ ፈገግ አለ... አብሮ አደጉን #ሃና_አረጋዊን።

#2013

ሰፈሩ ሁሉ በጥይት እሩምታ ታምሷል የሴት ልጅ ጩኸት በየቦታው ይሰማል የቴሌቭዥን ሚዲያዎች እንዳለ "መከላከያ ሰራዊታችን ፅንፈኛውን ቡድንን ደምስሶታል" የሚል ዜና ብቻ ነበር የሚዘግቡት።

የትግራይ ተወላጆች ካሉበት ቦታ ተነስተው ትግራይ ክልል ገብተዋል በአንዳንዶቹም ብዙ እንግልት ደርሷል። ዲሞክራሲ ብሎ የሰየመው መንግስት ለህዝቡ መዘዝ አምጥቷል....ትግራይ ክልል የሚገኙት የሌላ ብሄር ተወላጆች ትግራይን ለቀዋል አንዳዱም ህይወታቸውን አጥተዋል።
ብዙ እንግልት ሃገሪቱ ላይ ደርሷል በ 1 ሃገር ውስጥ የ 2 ጎሳ ግጭት አለምን አነጋግሯል...ብዙ ጭንቀት....ውጥረት...ኢትዮጵያውያኑ በየሃይማኖቱ ፀሎተ ምህላ ገብቷል።

አብዮት በጭንቀትና ውጥረት የስለኩን ቁጥሮች ይነካካል...ይደውላል...አይነሳም
ይጠራል...አይነሳም
ማበድ ቀረው የሚያደረገው አጣ....እንደገና ሞከረ
"የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁ...." አላስጨረሳትም ስልኩን ዘጋው። ሀገሯ ተደበላልቃለች የጥይት እና የጩኸት ድምፅ ብቻ ይሰማል።


#2025

"የደራሲ አብዮትን መፅሃፍ በቅናሸ....እየጨረስን ነው....አነጋጋሪው መፅሃፍ....አለች በቅናሽ" ገበያው በ አብዮት መፅሃፍ ተጥለቅልቋል። በጣም ተፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ 8ኛ ዕትም በቀላሉ ደርሷል...በተለያዩ ሚዲያዎች ስለሱ መፅሃፍ ሃያሲያንን ጋብዘው ትንታኔን ይሰጣሉ። የፃፈው መፅሃፍ ርዕሱ እና መዝጊያ ቃሉ ከሌሎች መፅሃፎች ተለይቶ ሳቢ አድርጎታል።

"ሄሎ ደራሲ አብዮት...ስለ መፅሃፍህ አንዳንድ ነገር እንድትለን ነበር ፈቃደኛ ከሆንክ".....

ይቀጥላል....


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19