Get Mystery Box with random crypto!

እንኳንስ የሮጠ ጀግኖ ሳይደክመው ያነከሰው ሁላ ይቀድመኛል ምነው? ማነው የሰፈረልኝ ጋሻ ሙሉ ለቅሶ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እንኳንስ የሮጠ ጀግኖ ሳይደክመው
ያነከሰው ሁላ ይቀድመኛል ምነው?
ማነው የሰፈረልኝ ጋሻ ሙሉ ለቅሶ
አይኔን ማን ሸለመው መሀረብ ተኩሶ??
በእዬዬ ዬ ዜማ አሸበል ገዳዬ
ወረዱበት መሰል ጠርጥሯል ጆሮዬ
ህልሜን ይህ ደመና ዋጠው ሳይፈታ
አምኜ እየካድኩት ሊመጣ ነው ጌታ
የኔን ደፋ ቀና ማን ፃፈው ገድሌን
በችግር ፈትኖ መች ዘገበው ስሜን
ፍርዴ ተገማድሎ በየቀኑ ስሞት
ማነው አስተውሎ ነህ ያለኝ ሰማእት?!!
እየኖርኩ ሞቻለው!!!
@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19