Get Mystery Box with random crypto!

ዝም አልክ አትበለኝ!!! «ስለምንሰማው - የሀገር ውጥንቅጥ አፍህ አይለጎም - ለሀቅ ፍንጭ ስጥ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ዝም አልክ አትበለኝ!!!

«ስለምንሰማው - የሀገር ውጥንቅጥ
አፍህ አይለጎም - ለሀቅ ፍንጭ ስጥ
ምድሩ ረስርሷል - በንፁሀኖች ደም
ማዳበሪያ ሆነ - ስጋ ቀልጦ እንደ ሰም»

እያልክ አትንገረኝ!

«አንድ ኢትዮጵያ ብሎ - ፍቅርን አስቀድሞ
አንድ የሚያደርገንን - ባንዲራዋን ስሞ
የሚለያየንን - ጀመረ ማውለብለብ
ተንኮል ብቻ ሆነ - የህዝባዳም ቀለብ»

እያልክ አትንገረኝ!

እውነቱን ልንገርህ ፣ ምርር ብሎኛል
ድፍንፍን ያለ ሀቅ ፣ ደቁሶ ገሎኛል
ህጉ ሆኗል ጎታች ፣ ምሬት ሚያሰንቅ
ከሳሽ እያነቀ ፣ አጥፊን ሚያራቅቅ

ምንም አትንገረኝ!
ህግ ሃቅ እስኪሆን ፣ በሃገሬ ሰማይ
እንባተገድቦ ፣ ሳቂ ጥርሶች 'ስካይ፡፡

እስከዛ • • • እኔን ተወኝ
#ዝም_አልክ_አትበለኝ !


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19