Get Mystery Box with random crypto!

አገባህ ነበረ…………… ቆሎ 'የቆረጠምን እኖራለን ውዴ ልጅ በልጅ ይሆናል ቤታችን መውደዴ አንቺ ው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አገባህ ነበረ……………

ቆሎ 'የቆረጠምን እኖራለን ውዴ
ልጅ በልጅ ይሆናል ቤታችን መውደዴ
አንቺ ውሀ አጣጬ የእግዜር ባለ አደራ
እሺ በይኝ ላግብሽ ፍቅራችንም ይድራ::

አለኝ የኔ ሚስኪን..............
               አገባህ ነበረ..................

ቆሎ ባልቆረጥም እርሀብ ባይደፋኝ
ሊያውም በዚ ዘመን..........

ቆሎ ያልከው ውዴ
ዝም ብለህ ስታየኝ የኤርፎራ ዶሮ እመስላለሁ እንዴ?

ጭራሹን.................

ልጅ በልጅ ሆኜልህ
አንዱን ከኃላዬ ሌላውን ከፊቴ
ገሚሱን በግራ ገሚሱን በቀኜ
እሪ እምቧ ሲሉብኝ መንምኜ መንምኜ

የድስት ፍቅፋቂ በጋራ ስንበላ
ጎረቤት ቢረበሽ ይደብራል ኃላ

እኔም ተማርሬ እግዜር ከሚከፋዉ
ቆሎህን ለብቻህ ተደብቅህ ብላው::


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ (@Tizita21)


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19