Get Mystery Box with random crypto!

#ከጎንደር_እስከ_መኧለ #ምዕራፍ_1 #ክፍል_04 (ትረካ) ምሽት 3:00 ፋና 98.1 #20 | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_04 (ትረካ)


ምሽት 3:00 ፋና 98.1


#2013
"የጎንደር ኤርፖርት ላይ የወደቀው ሮኬት የአዘዞን ክፍለከተማ ነዋሪ አሸብሯል...የስልክ መስመር በሃገሪቱ ተቋርጧል....ጭንቀት ብቻ....ብዙ ሚዲያዎች የሚዘግቡት ዘገባ እልህ አስጨራሽ ነው....የ ህውሃት  እና የብልፅግና ቡድን ጦርነት መክፈታቸው ያብዛኛው ኢትዮጵያዊያን የሞት ምክንያት ሆነዋል....የብልፅግና ቡድን 'እድሜው የደረሰ ወጣት ሁሉ ለ ሀገርህ ዝመት' የሚል መልዕክት አስተላለፈ.....ወንድሜን ለመግደል....ሀገሬን ለመግደል ለሀገሬ ልዝመት አይደል......ከትንሽ ማንሰላሰል በኋላ የመንግስታችንን ሃሳብ ተቀበልኩ....ደስ እያለኝ...."

(አዘዞ:የምዕራብ ዕዝ የጦር ካምፕ)

"መለዮ ለብሰናል....በተለይ ለኔ የለበስኩት መለዮ አዘንጦኛል ማለት ይቀላል....ከፊቴ ላይ ያሉትን ውብ ፂሞቼን ተቆርጫለሁ...ለነገሩ መቆረጥ አይባልም መላጨት ልበለው...እየሸሸ የነበረውን ፀጉሬንም ድራሽ አባቱን አጥፍቼዋለው....ትግራይ ሄጄ ድል ከማድረጌ በፊት አካሌ ላይ ያሉት ነገሮች ደምስሼ ተቆጣጠርኳቸው...አቤት ወኔ...አቤት ግርማ ሞገስ..."

(ጉዞ--ከአዘዞ-ደሴ)

"አውቶቢሱ ደሴ ሊደርስ ትንሽ ሲቀረው ሹፌሩ እያጫወተው የነበረውን ሙዚቃ ቀየረው....ከዛ በፊት 'የጨነቀ ለት..እየየ' የሚለውን እያጫወተ ነበር ከዛን ደሞ 'ደሴ ላይ....ደሴ ላይ ነው ቤቷ አሄ....የሚያምረው አንገቷ' የሚለውን ከፍቶ ዘማች ወታደሩን የደሴን ጉብል አግብት እንዲሄድ ልቡን ቀሰቀሰለት...ወታደሩም የዋዛ አይደል አንገቱን በመስኮት እያወጣ መቁለጭለጭ ጀመረ።

"ደሴ ገራገሩ ደረስን ካድባሩ...ሃሃሃሃሃሃ(በረጅሙ ተነፈስኩ)...ከአውቶቢሱ በፍጥነት ወረድን...አካባቢዋን ቃኘሁት...ደስ ትላለች ደሴ...የህዝቡ አይን እኛ ላይ አርፏል በደስታ ተቀበሉን የደሴ ልጆች ደስ ብሏቸዋል...ትንሽ ከተረጋጋ በኋላ ከወታደሩ ቡድን በቀስታ እያፈገፈኩ መጣው...መቼስ የደሴ ሰው መልካም ነው..ከላይ የለበስኩትን የወታደር ልብስ አወለኩት...ወደአንድ እናት ጠጋ ብዬ እየተቁለጨለጭኩ 'ማማ እባኮትን ከጉድ ያውጥኝ የዛሬን ያውጡኝ እባኮትን...ውለታዎትን አረሳም'

ይቀጥላል....

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19