Get Mystery Box with random crypto!

#እንቶ_ፈንቶ ፡ ፡ ፡ ««በጭራሽ አትምጪ በፍፁም አልመጣም፣ የፍቅርን ፅዋ ዳግም እንደገና ባብሮነ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#እንቶ_ፈንቶ



««በጭራሽ አትምጪ በፍፁም አልመጣም፣
የፍቅርን ፅዋ ዳግም እንደገና ባብሮነት አንጠጣም።
ተቀብሯል ነገርሽ ተቀብሯል ነገሬ፣
በይ ትፊኝ አንቅረሽ ተፋውሽ አንቅሬ።»»


የሚል ግጥም ልፅፍ ብዕሬን ስመዘው፣
እጅ ለካ አይፅፍም ልብ እስካላዘዘው።


ቢፅፍም ቢጭርም በንዴት ተገፍቶ፣
ሀረጉ አርቲ ቡርቲ ስንኙ እንቶ ፈንቶ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19