Get Mystery Box with random crypto!

ፅድቅ ነው አውቃለው ..... የሷን እጅ መያዝ ድምጿን እየሰሙ በፈገግታ መጓዝ ደሞ'ም ኩነኔ ነ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ፅድቅ ነው አውቃለው .....
የሷን እጅ መያዝ
ድምጿን እየሰሙ በፈገግታ መጓዝ
ደሞ'ም ኩነኔ ነው ከሷ ጋራ መራቅ
ውሎ ማደር ከንቱ ሳይሰሙ የሷን ሳቅ

ፅድቅ ነው አውቃለው ...
ሀቅ እና እውነታ እምነት የሷ ድንበር
መታበይ የማያውቅ በዚች ከንቱ ምድር
.......
ከሰማይ የሰፋ የመታመን ጥጋት
ከባህር የሚልቅ የመውደድን ጥልቀት
በእፍኝ ቦታ ላይ አዛምዶ የያዘ
ልብሽ ነው አውቃለው ለፅድቅ የተጓዘ

እኔ ግን ተኮነንኩ ከሃጣን ተመደብኩ
እቅፏን ሰብሬ
ወዲያ አሽቀንጥሬ
ንፁህ ፍቅሯን ገፋው በስሜት ሰክሬ
ተስፋዋን አጨለምኩ መንፈሷን ረበሽኩ
ደስታዋን አጥፍቼ ፈገግታዋን ገደልኩ
.......
ግን አንድ እውነት አለ እሱንም አውቃለው
ከሃጢአት ለመዳን ንሰሃ ምርኩዝ ነው
ፍቅር መድህን ሆኖ ከመጣ ለህማም
ይቅርታ ፈውስ ነው ዳግም ለመታከም
......ዳሩ ግን
ከባድ ስለሆነ የበደሌ ስፋት
ምስኪኗ ልብሽን በይቅርታ መግፍት
እ.ን.ዳ.ላ.ስ.ቀ.ፅ.ፋ.ት
ምህረት አልጠይቅም ከደጅሽ ላይ ቆሜ
እንዴት አንቺን ላርክስ እኔ ተረግሜ
እናልሽ አለሜ
እናልሽ ተስፋዬ
እናልሽ ህመሜ
.......
ይቅር ባለማለት ሃጣን እንዳትባይ ኩነኔ እንዳትሰሪ
ቢያንስ አንቺ ኑሪልኝ ከፃድቃናት መሀል ስሜን እንድትጠሪ
መገኘት አለብሽ ከገነት አጥቢያ ላይ እውነቴን ለመንገር
መጥፎም ሆነ ጥሩ ታሪክ ይኖረዋል ወንድ ልጅ ሲያፈቅር!!!

By JAHA

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19