Get Mystery Box with random crypto!

ሞኝ እና..? አንቺ የዘመን ጓድ መኖር የማይበቃሽ ሁሉ በተኛበት ብልጥ ሁነሽ የነቃሽ እኔ የቀን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሞኝ እና..?

አንቺ የዘመን ጓድ መኖር የማይበቃሽ
ሁሉ በተኛበት ብልጥ ሁነሽ የነቃሽ

እኔ የቀን ጥለኛ ፥መኖር የሚበቃኝ
ሁሉ በተኛበት ፥ ሞኝ አርጎ ሚያነቃኝ

አንቺ የደግ እናት ፥መወደድ የቀናሽ
ጡትሽ ባልኖረበት ፥መፈቀር የጠባሽ

እኔም የሰው አባት መወደድ ያልቀናኝ
ጩኸት ብቻ ትርፉ ዝምታ ሚጠማኝ

ሆኖ ግን

በእኔ በአንቺ ገመድ የመቀኘት ፍቅሩ
ፊደል ይለይ እጂ አንድ ነው ሚስጥሩ


ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19