Get Mystery Box with random crypto!

እየወደዱ መራቅ ትንቅንቅ ግብ ግብ ከራስ ጋር መታገል ከ አፋፍ ላይ መቆም ከ ዝናብ መጠለ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እየወደዱ መራቅ


ትንቅንቅ ግብ ግብ
ከራስ ጋር መታገል
ከ አፋፍ ላይ መቆም
ከ ዝናብ መጠለል

መውደቅ እየፈለጉ
መበስበስን ሽተው
እግርን ከመራመድ ፍርሀት ሲመክተው
አፋፍ ደለል ሲሆን
ዳመናም ሲበተን
ፍቅር ሲኮሰምን
መውደድም ሲመክን

አይተው እንዳላዩ
አውቀው እንዳላወቁ
ተሰምቶ እንዳልተሰሙ
ራስን ሸሽገው
እውነትን በሀሰት አጣፍተው ገልድመው
አንገት አዘቅዝቀው መንገድ ሲራመዱ
ልብ ያለቅሳል እውነት ለጎረቤት ሆዱ

እየወደዱ መራቅ

ከነብስ ጓደኛ ከልብ ከታሰረ ነጠላ ቁራኛ
ሀሳብ ከገባ በችሎት አልባ ዳኛ
በውድም በግድም ከሆነ ቤተኛ
ከነብስ ትራስ ላይ ከተንተራሰ
ከአንድ ማዕድ ቀርቦ ከእጅ ከጎረሰ
በአንድ ሀዘን ስሜት እኩል ካለቀሰ
በአንድ ደስታ ስሜት እኩልም ከሳቀ
የህይወት መንጠቆ-ን ከስር ከሰበቀ
የኑሮውን ጓዳ ገልጦም ካልደበቀ

ምን ተብሎ ይሸሻል ምን ፈር ተይዞ
እንዴት ይሰጣል ጀርባ ፊትን አጠማዞ
ይሰቃል ይከብዳል አጥንትን ይወጋል
አይን እያለቀሰ ነብስ እዥን ያዣል
መላው ቢጠፋብን ነው እንጂ ቢቸግር
እንዴት ያለ ጉልበት ይራመዳል እግር

በሀሳብ መበለት መከፈል በሁለት
በናፍቆት መናጥ በትዝታ መቅለጥ
እሹሩሩ ማለት ራስን በለሆሳስ
እፍ ብሎ መጥፍት ልክ እንደ ንፋስ
ያሰኘኛል ከርሞ ከምወደው መራቅ

ከአፌ ልቃቂ አንድ ቃል አላወጣው
እወድሻለሁ ያለ ምላሴ እንዴት ሌላ ሊቃጣው
ከማንም አልባው ከከንፈር ላይ መሶብ ቅንጣትን ቀንሼ
ወደ ማንም አልሄድኩ እንኳን በሙሉ እግር ከጉልበቴም አንክሼ
ልላን ሰው አላቀፍኩ በርሀ አቋርጬ እርቀትን ጥሼ

ዛሬ ብዘጋ አንድበቴን
ከፊትሽ ብጋራድ እንዳታይ እኔነቴን
ጠልቼሽ አይደለም መውደዴም ተቀብሮ
አስችሎኝም አይደል ካንቺ መሄድ ዞሮ

ህምምምምምምም

ሁኖብኝ ነው እቴ እየሞሉ ማለቅ
በነገ ፍራቻ ዛሬ ላይ መጨነቅ
በስስት ሙሉ ፍቅር በስጋት መጨመቅ
ስነግርሽ ሀቂቃውን እውነታውን ሀቅ
የሞት ማቅ መልበስ ነው ካንቺ ጎን መራቅ
ቧልትም ነገር አይደል ዝባዝንኬ እንዲያው
ደርሶበት ያየው ነው ነገር የሚነባው



▾▵Řu‌▴▿

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19