መልከ ቀና አድርገኝ ህይወቴ ቢቀለኝ.. . አውለኝ በክብር ቀባኝ ሞገስ ቅባት ቀኖቼ ላይ ልንገስ በሌሎች ፍርሀት። ስጠኝ የመሪ ድምፅ አጥር የሚሻገር... መንገዴ እንዲሳለጥ እንዲሆን ገር በገር ። አልያ አልገፋትም... ይህችን ስንኩል ዕድሜ ለአይን አስቀይሜ፥ ቀልዬ ያለ ሞገስ... ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው ከሞት ደጅ የሚደርስ !! (ሚካኤል.አ) ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19 5.2K viewsAbela, 14:16