Get Mystery Box with random crypto!

#ዝም_ብትል_ምን_ትሆናለህ? ስታስበው የሚቆጭህን ለመጨረሻ ጊዜ የተናገርከውን መጥፎ ነገር አስታው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

#ዝም_ብትል_ምን_ትሆናለህ?

ስታስበው የሚቆጭህን ለመጨረሻ ጊዜ የተናገርከውን መጥፎ ነገር አስታውስ፡፡ ለምን ተናገርከው? ማለት የማያስፈልግህ ለመሆኑ እድል ነበረህ፤ አንተ ግን መናገርህ ብልህ ወይም የተረጋጋ ወይም ከሰው እኩል እንደሚያደርግህ   አሰብክ፡፡

ሮበርት ግሪን እንደጻፈው፣ “ብዙ ባልክ መጠን፣ በበለጠ ሁኔታ የማይረቡ ነገሮችን የመናገር አጋጣሚ ይኖርሃል፡፡” በዚህ አባባል ላይ እኛም፤ የበለጠ በተናገርክ መጠን፣ በበለጠ ሁኔታ ያለፉ መልካም አጋጣሚዎችን ልታበላሽ፣ ምላሽን ችላ ልትልና ራስህ ላይ ስቃይ ልታመጣ ትችላለህ የሚል እንጨምርበታለን፡፡

ልምድ የሌላቸውና በፍርሃት የተሞሉ ሰዎች ራሳቸውን እንደገና ለማረጋገጥ ይናገራሉ፡፡ ሆን ብሎ ከንግግር ልውውጥ ውጪ ለመሆንና ያለ እሱ ተቀባይነት ለመቀጠል የማዳመጥ ችሎታ ብዙም የማይገኝ ነው፡፡ ፀጥታ ጥንካሬና በራስ በቂ የመሆንን መንገድ የምንገነባበት መንገድ ነው፡፡

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19