Get Mystery Box with random crypto!

የማይታወስ አፅም ስንሄድ ስንመለስ ፥ እግራችን ሲያዘግም ተራምደን ያለፍነው ፥ ማን ይሁን አናውቅ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የማይታወስ አፅም

ስንሄድ ስንመለስ ፥ እግራችን ሲያዘግም
ተራምደን ያለፍነው ፥ ማን ይሁን አናውቅም
ታሪክ ያልዘከረው ፥ ያልተጠራ በስም
አለ የተረሳ ፥ የማይታወስ አፅም

እንደ ሰራተኛ ፥ ፈርኦን ቤት ኖራ
እምነት ከጡቷ ጋር ፥ ያጠባችው አብራ
ያቺ የሙሴ እናት ፥ ገድሏ መች ተወራ
ዮሴፍ ቢያባብለው ፥ አምላክን በቅፉ
ዘውትር መች አነሳው ፥ ሰባኪው በአፉ

ከአሸዋው ክምር ፥ ከበርሃው ግድም
ከተራራው ግርግም
አለ የተረሳ ፥ የማይታወስ አፅም
ተራምደን ያለፍነው ፥ ማን ይሁን አናውቅም

ከድል በስተጀርባ ፥ ብዙ ወድቆም ቢቀር
ንጉስ ነው ሚዘከር
መንግስቱን ያፀናው ፥ አሽከር መች ይወሳል
ታሪክ እየለየ ፥ መርጦ ያስታውሳል

አቤል ታደለ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19