Get Mystery Box with random crypto!

ቤተልሄም በ ኤልሳ ክፍል 4 •••••••ወደ ውስጥ ገባ ሁሉም ክብ ሰርተው መጠጥ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 4

•••••••ወደ ውስጥ ገባ ሁሉም ክብ ሰርተው መጠጥ እየታዘዘ ነበር ምንም የተለየ ነገር እንደማያይ ሲገባው ተመልሶ ወጣ 11 ሰአት ሊሆን ነው የቀጠሯቸው ሰአት እየደረሰ ነው ልብሱን ለመቀየር ወደቤት ሄደ ልብስ ቅየራው ብቻ አንድ ሰአት ፈጀበት ይህ ይሻላል?
አይ ይህ ይሻላል? .እያለ ሲያማርጥ የመጨረሻ ምርጫው ሸሚዝ እና ሱሪ ላይ አረፈ ያንን አድርጎ ስልኳን መጠባበቅ ጀመረ እንደምትደውልለት እርግጠኛ ነበር ሰአቱ እየሄደ ነው 1 ሰአት ሆነ አሁንም አልደወለችም ከምሽቱ 2 ሰአት ሲሆን ትግስቱ አለቀ ደወለላት
"ሄሎ"
"ሄሎ"
"ቤቲ እስካሁን ስልክሽን እየጠበኩ ነበር እኮ"
"ኦ ይቅርታ ዛሬ ከሰው ጋር መዝናናት ሙዴ ስላልሆነ ነው" ወዲያው ቅድም ከሰዎች ጋር ግሮሰሪ የገባችው ትዝ አለውና
"ከሰዎች ጋር ወይስ ከኔ ጋር?" አላት
" ካንተ ጋር " አለችው ንዴቱ አናቱ ላይ ሲወጣ ይታወቀዋል
"እሺ" ብሎ ስልኩን ዘግቶት መኪናውን አስነስቶ ወጣ ቅድም አያት ግሮሰሪ ሄደ ቅድም አየው ቦታ ላይ የለችም ወደውስጥ ገባ ባንኮኒው ጋር ተቀምጣ ብቻዋን እየጠጣች አያት ቀጥ ብሎ ከሄደ ቦሀላ "ወምበሩ ሰው አለው?" አላት ከፊቷ ወዳለው ባዶ ወምበር እየጠቆመ
"እ?" ምላሿ ዝምታ ነበር የንቀት መሆኑ ስለገባው በ እምቢተኝነት ወምበሩ ላይ ተቀመጠ ቤቲ እስካሁን እያጨሰች እየጠጣች ነው ድንገት ስልኩ ጠርቶ ወደ ውጪ ወጣ ቶማስ ነበር
"ሄሎ ቶም!"
"ሰላም ነው?"
"አለሁ ምን አዲስ?"
"እንኳን ደስ አለህ!"
"ምን ተገኘ?"
"በ እግር በፈረስ ስታፈላልጋት የነበረችው የ ፊሊጶስ እህት በ እጃችን ገብታለች "
"እና ምን እየጠበቃችሁ ነው አስወግዷታ"
"እሱ የማይቀር ነው ግን ለሁሉም አንተ ማንነቷን መኖሪያ ቤቷን እና አኗኗሯን ማየት አለብህ ከዛ ፖሊስ ጣቢያ ለጥያቄ ብትፈለግ እንኳን ብዙም ቃል ለመስጠት አትቸገርም !"
"መልካም ነገ እንገናኛለን ሁሉንም ትነግረኛለህ"
"እሺ ደህና እደር"
ስልኩን ዘግቶት ወደ ውስጥ ተመለሰ አሁንም እያጨሰች ነው

"ቆይ ለምንድነው የምታጨሽው?"
" ለምን ይመስልሀል? "
"እኔ በምን ላውቅ እችላለሁ"
"አላውቅም!"
"እሺ የሆነ ህይወትሽን ያበላሸው ነገር ያለ ይመስለኛል ምንድነው?"
"ምንም ደህና ነኝ"
"አይ ጥሩ መጠጥ ወጪ ዛሬ በኔ ነው በደምብ ጠጪ" ከ ፌዝ ፈገግታ ጋር
" ይቅርታ ጋብዤ እንጂ ተጋብዤ አላውቅም " በተያያዘ አፍ
" እሺ በቃ ደስ ያለሽን አድርጊ"
ፍዝዝ ብሎ እያያት ነው ልቡን ስታሸንፈው ይታወቀዋል ግን ሽንፈቱ በጣም አናዶታል ምክንያቱም የተሸነፈው ከማንም በላይ ለምትንቀው ሴት ነው
"ቆ..ቆ...ቆ...ቆይ ግን እዚህ እንዳለሁ እንዴት አወክ?" በጥርጣሬ የስካር አይን እያየችው ...
"ወፏ ነግራኝ"
"ሀ..ሀ..ሀ ያንተዋ ወፍ ደግሞ ትለያለች ባክህ?" ከ ለበጣ ሳቅ ጋር
"አንቺ ያለሽበትን ቦታ ማግኘት ለኔ እጅግ በጣም ቀላል ነው"
"እኔን ግን የማይታሰብ ነው!"
"አንቺን ምን?"
"ማግኘት!"
"ጊዜ ይፍጅ እንጂ አህያ የጅብ ናት ቤቲዬ!"
"እውነት ነው ችግሩ አህያና ጅቡን መለየቱ ላይ ነው"
" ሀሀሀ ቅኔዎችሽ ጦር ናቸው ባክሽ?"
"ጥሩ ትፈታለህ ማለት ነው እንውጣ?"
"እሺ"
በመኪና ከሸኛት ቦሀላ በደስታ ወደቤቱ ገባ ነገር ግን አንድ ነገር አየ ቤቲ ቦርሳዋን ረስታው ነበር ያ ደግሞ ነገ በጠዋት ቤቷ እንዲሄድ ምርጥ አጋጣሚ መሆኑ ከምንም በላይ አስደስቶታል......
አይነጋ የለም ነጋ 2 ሰአት ላይ ውጭ በሯ ጋር ተገኝቶ በክላክስ ሰፈሩን መበጥበጥ ጀመረ ወጥታ በሩን ከፈተችለት እና ሳሎን ገባ
"በጠዋቱ ምንድነው እንደዚህ ..." ሳትጨርስ ማውራት ጀመረ
" ትላንት ቦርሳሽን.... " ብሎ ቦርሳዋን በ አንድ እጁ ከፍ አደረገላት
"ኦ ...ይቅርታ !" ብላ ተቀብላው
"አረፍ በል" ስትለው እንደማንገራገር እያለ አንድ ፎቶ አይኑ ውስጥ ገባ ከመጠን በላይ ደነገጠ እጆቹ መንቀጥቀጥ ጀመሩ በጣም እንደደነገጠ ፊቱ ያሳብቃል ቤቲ"ምን ሆነህ ነው?" ብትለውም በድን ሆኖ አይኑን ፎቶው ላይ ተክሎ ቀረ ምክንያቱም ፎቶው•••••••••
የሚያውቀው ሰው ነበር እጁ እየተንቀጠቀጠ ወደፎቶው እየጠቆመ
"ይ ይ ይ ... ይሄ ማነው ? " አላት
"ይሄ....." ወደ ፎቶው ተራምዳ ከ ብፌው ላይ አንስታ ይሄ ወንድሜ ነው ፊሊጶስ ይባላል " ይባስ ደነገጠ
"ምነው ደነገጥክ? ችግር አለ?"
"ይ..ይቅርታ መሄድ አለብኝ!"
"ይሻላል?"
" አ አ አ ዎ ይሻላል !" ምራቁን ከጉሮሮው ላይ ለመዋጥ እየታገለ
" እሺ! " ብሏት ቤቱን ለቆ መውጣት ጀመረ አራት እርምጃ ሳይራመድ ጠራችው
"ናሆሜ"
"ወዬ"ወደ ኋላ እየዞረ
"ለቦርሳው አመሰግናለሁ እሺ? በጣም የምፈልገው ፋይል ነበር ውስጡ" ብላ ተንደርድራ መጥታ አቀፈችው ሁኔታዋ ግራ አጋብቶታል ትላንትና ከዛ በፊት እንደዛ ስትንቅ እና ስታንቋሽሸው የነበረች ልጅ ዛሬ እንደዚህ መሆን ቅድም ካየው ፎቶ በላይ አስደንግጦታል ስታቅፈው የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶታል
"እሺ ምንም ችግር የለውም" ብሎ ተሰናብቷት ሄደና መኪናው ውስጥ ገብቶ ለ ቶም ደውሎ በፍጥነት ሊያገኘው እንደሚፈልግ ነግሮ ቀጥሮት መኪናውን ወደ ቀጠረበት ቦታ ማክነፍ ጀመረ
°°°
ቤቲ ሲወጣ ጠብቃ በሩን ከውስጥ ከዘጋች ቦሀላ ሶፋ ላይ ያለውን የወንድሟን ፎቶ አንስታ ካቀፈችው ቦሀላ ወንድሜ አሁን እኔ አለሁልህ ገዳይህን በቁሙ እገልልሀለሁ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች አደርግልሀለሁ!" ብላ ትላንት የተፈጠረውን ማስታወስ ጀመረች ትላንት ከ ልዑል ጋር ተገናኝተው የ ወንድሟን ገዳይ ፎቶ ሲሰጣት ትዝ አላት አገዳደሉን ምክንያቱን የነግራት ትዝ ሲላት አይኗ ደም ለበሰ ፊቷ ቲማቲም መሰለ የያዘችውን ፎቶ ወረወረችው ...ፍሬሙ ድቅቅ አለ ደንግጣ አንስታ አቀፈችው እና ወዲያው ፍሬሙን ለማስቀየር በመኪናዋ ይዛው ሄደች ከሰፈር ወደ ዋናው አፓልት መውጫ አካባቢ መኪኖች ተጨናንቀው ነበር....
°°°

ናሆም ቶማስን ቀጠረበቅ ሞል ደርሶ ወደ ካፌው ገባ ቶማስ አንድ ወምበር ይዞ ተቀመጧል እንዳየው እጁን አወዛወዘለት ናሆምም ወዲያው በቀላሉ አየውና በፍጥነት ወደ ቶማስ ሄዶ ሰላም እንኳን ሳይለው ወምበር ስቦ ተቀምጦ
"እ ... የታለ ፎቶዋን አሳየኝ !"አለው
"ኧረ ተረጋጋ ......እሺ ቆይ " እጁን ወደ ደረት ኪሱ ውስጠኛ ክፍል እያስገባ.... ጥቂት ቆይቶ አንድ ፎቶ አወጣና "ቆይ የቤቱ ደግሞ ... ብሎ በሌላኛው እጁ ኪሱ ሲገባ ናሆም ትግስት በማጣት በ እጁ የያዘውን ፎቶ መንጭቆ አየውና ፊቱን በ አንድ እጁ ሸፍኖ በረጅሙ እየተነፈሰ ወደኋላው ተደገፈ ሁኔታውን ያየው ቶማስ
" ምነው አለቃ ችግር አለ እንዴ?" አለው
"አዎ ያውም እጅግ በጣም ትልቅ !" እጁን ከፊቱ ላይ ሳያነሳ
"ኧረ አለቃ ምንም አታስብ ይሄኛው እንደውም ቀላል ነው ልጅቷ ብቻዋን ነው የምትኖረው ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም አደገኛ ብትሆንም ለማስወገድ ግን ሴኮንድ አትፈጅም ሁሉም የቤተሰቦቿ አባላት በህይወት የሉም ማንም አይጠይቀንም የድመት ነፍስ በለው እሷን ማስወገድ ከ ፊሊጶስ በላይ ቀላል ነው እንደውም ናፍቋታል እያሉ ነበር " ከ ፌዝ ሳቅ ጋር
'' በዛ ላይ እኮ ቤት ያለው ሀብት ራሱ....."
"በቃህ!" ብሎ ጠረጴዛውን ሲመታው ሁሉም የ ካፌው ሰዎች ደንግጠው ዝም ብለው ሲያፈጡበት አጎምብሶ ዝም አለ......


.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19