Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 133.72K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
✥--------------------✥
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 12

2023-04-23 07:08:04 ሴትም እግዜር ትሆናለች
ወንዱ ካፈቀራት

ገጣሚ :-ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.4K viewsAbela, edited  04:08
Open / Comment
2023-04-22 14:57:01 ----እውነት፣ተስፋና ፍቅር----

በሐዘን ቤት እንባ ይነዳል፤
እቶን ሆኖ በቀዬ ላይ ይቃጠላል፤
የወላፈን ጅራፍ፥ስቦ ይገርፈኛል።
ግማሽ ልቤን በእቅፉ ውስጥ እያሞቀ፤
የቀረውን በጅራፉ ሞሸለቀ።
.......
ዝቅ ስል ሲዖል ላይ አፈጠጥኩ፤
ከዛም ዘወር ስል፥ከሞት ጋር ተፋጠጥኩ፤
ዙሪያ ገባ ሞት ነው፤መላክ መሳይ ሰይጣን፤
እኔና ሰላሜን እንቅልፍ የሚነሳን።
.......
ተስፋ ርቆ ሸሽቶ ሄደ፤
ፍቅር ዋጋው ከርሞ ናኘ፤
ልቤ ቅስሙ ተሰባብሮ.....ሊደንዝ ዘንድ 'እየተመኘ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ማየት ተውኩኝ፥ጸሐይ ሄዳ፥ብርሃን ጠፍቶ፤
በጠፈር ሀይል፥ጽልመት ባህር፥ውብ ፀዳሏ ተሰውቶ ፤
አይሄድ ይመስል የሚያበራው፥ያ ውበቷ፣
ከዋክብትን የሚሸፍን፥ደም ግባቷ፣
አለሁ ብሎ የደለለኝ፣
በፍቅር ቀትር፥በደስታው ጨጅ ያሰከረኝ፣
ጀንበር ገብታ፥ጥላኝ ስትሄድ ተነጠለኝ።
...
እኔ ምስኪን መፃተኛ፣
በፀሀይ ናፍቆት የምቃትት፥የማልተኛ፣
ነግቶ አያት ዘንድ ጠብቃለሁ፤
ብርሃነ ፍቀሬ ሆይ......
እስክትመጪ ድረስ......ኩራዜን ይዣለሁ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በልቤ ግድግዳ ትልልልልልቅ ስዕል አለ፤
ውበትን የሚያስንቅ፥መልክሽን ያዘለ፤
እሱ ብቻ እንዲታይ፥
እሱ ብቻ እንዲደምቅ፥ሁሉን የከለለ፤
......
በልቤ ግድግዳ......
እንቡጥ ከንፈሮችሽ፣
አበባ ጉንጮችሽ፥
ደሜን ይጣራሉ፣
"ና ሳመን...ና ሳመን....ና ሳመን" እያሉ።
........
በአይኖችሽ ነጸብራቅ ምሉዕ ፊትሽ በርቷል፤
ልክ እንደ ፈንዲሻ፥ፈገግታሽ ፈንድቷል፤
ያ መረዋ ድምጽሽ፣
ያ መረዋ ድምጽሽ፣
እንኳን ከንቱ ልቤን፥መለዐክትን ይጣራል።
.........
እቴ ባንቺ ፍቅር ልቤ እየነደደ፣
እግርሽ በረገጠው፥ጎዳና እየሔደ፤
ባይኖችሽ ጮራ ስር እንደ ጨው አምድ ሲናድ፣
በፈገግታሽ ሞገድ፥ወኔ እብሪቴ ሲርድ፣
ፍቅር ያሳሳው ልቤ....
ፍቅር ያሳሳው ልቤ...
መከተል አድክሞት፥'እንደ ንፋስ ነፈሰ፤
ጨዋታ ፈረሰ፥ዳቦውም ተቆረሰ።

~ተፃፈ በኢሮስ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.0K viewsAbela, 11:57
Open / Comment
2023-04-22 08:31:22 የትም ፍጭው………

የኔ ልጅ ጨዋ ነው፤
ውሎው ከስራ ነው።
የምፈልገውን የሰኘኝን ሁላ፣
እንዳይጎል ያደርጋል ሁሉን እያሟላ።
ልጄ እኮ ልባም ነው፤
ጥሩ ደሞዝ ያለው፤
ብር እንካ የሚለኝ፤
ጠጅ የሚገዛልኝ፤
ሁሉን የሚሰጠኝ፤
ስራውምንእንደሆን
ጠንቅቄየማላውቀው፣
ልጄ እኮ ሌባ ነው።

≈ ተፃፈ በኤሮስ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.9K viewsAbela, 05:31
Open / Comment
2023-04-21 20:49:48 ጥያቄ?
ልብ ስጋ ነው ወይ ነፍስ ??
____
ተይ በታቦቱ
ተይ በሰማእቱ
ተይ በአርባራቱ

ላስይዝሽ እባክሽ በእናትዋ ባታ
በተወለድሽባት በቅብአ ቦታ

ታቦት ብዘረዝር ጎንደሬ አረጉኝ
አድባር ብጠራ ጎጃሜ ነህ አሉኝ

ይቆጠራል እንዴ ታቦት በአንድ አድባር
እምነት ለዓለም ነው ማን ሰጠው ለአባናር

ጥያቄ ?

ታቦትን ለጎንደር የሰጠውስ ማነው
አባይን ለጎጃም የሰጠውስ ማነው
የኔን ልብ ላንቺ የሰጠውስ ማነው
እንደው አትፍረጂ ያው ያንቺ አምላክ ነው
ወንድ አዳም ልቤን፥ በሔዋን ሚያመልከው
ያፈቀረ ንፉግ እግዜር ከየት ሊያቀው?

መልስ ?

ታቦቱን ማንሳቴ
ጠበሉን ማንሳቴ
እንድትመጭ ነበር ያስያዝኩሽ በእምነቴ

እምነቴ አልበጀኝ ለልቤ ባረዳ
ነፍስ አፀድቅ ተብሎ ስጋ ለሚጎዳ

ምንድነው መልሱ?
ጥያቄ?

ልብ ግን ስጋ ነው?
ከስጋ ተርታ ነውስ ሚመደበው?
ወይስ
ከነፍስስ ነው?
በእግዜር ዘንድ በሰማይ ሚታዬው ?

እና
የስጋ ከሆነስ ለፅድቅ ይሆናል?
አንቺን ማፍቀሬ ለነፍስስ ይባላል?

መልሽልኝ ????

ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.8K viewsAbela, 17:49
Open / Comment
2023-04-21 14:51:02 (ነበር ለካ  ...)
==============

በለመድነው ውብ ጎዳና
ፈሩን ሳይለቅ የእግርሽ የእግሬ ኮቴ ዳና
የለኮስነው ብርሃን ፋና...
ሩቅ ሳይደርስ ከመድመቁ ጨለመና
ያልጀመረ ታሪካችን አምና ሊባል ወይ አቻምና
ቀናት ቀሩ ወይ ሰው መሆን ወይ ፈተና....
:
የጊዜ ህግ ከቶ ይገርማል
ሚያልፍ ባይመስል ዛሬ ሲባል
ሺ ቢያወሩ እልፍ ቢማል
'ካሁን' ይልቅ 'ነበር' ለካ ቅርብ ኖሯል

By #kiyorna

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.1K viewsAbela, 11:51
Open / Comment
2023-04-21 09:16:28 ​​የውብ ተሰጥኦ ዳር
(በእውቀቱ ስዩም)

የሳምንቱ ትልቅ ክስተት፥ የታላቂቱ የረቂቅ ሙዚቃ ደራሲ እማሆይ ጽጌ ገብሩ እረፍት ነው፤ ታታሪ አድናቂዋ እንደመሆኔ መጠን መሰናበቻ ጥቂት ሀሳብ ባልጽፍ ህሊና ይወቅሰኛል! የፒያኖው ሽቦ ይወጋኛል::

ከእማሆይ ጽጌ በፊት የውብዳር ነበረች፤ አባትየው ከንቲባ ገብሩ እናቲቱ በየነች ኤሌምቱ ይባላሉ::

የውብዳር በሁለት መንገድ እድለኛ ናት፤ ባንድ በኩል እጅግ የላቀ ተሰጥኦ ይዞ መወለድ መታደል ነው፤ ከገዥው መደብ መወለድ ደግሞ ሌላ መታደል፤ የውብዳር ስዊዘርላንድ አዳሪ ትምህርት ቤት የመሄድ እድል ያገኘችው አባትየው ባለማእረግ በመሆናቸው ነው፤ በጊዜው ከመፍጨት ከመውቀጥ ውጭ ሌላ የህይወት አማራጭ የማይቀርብላቸው ብዙ ሴቶች መኖራቸውን እናስብ::

የውብዳር ስዊዘርላንድ በነበረችበት ጊዜ፥ ከዘመናዊ የአውሮፓ ሙዚቃ ፈሊጥ ጋራ ተዋወቀች፤ ባገራችን ለአመት በአል ለልጅ የሚሰጠው ትልቁ ስጦታ ድፎ ዳቦ ነው፤ የውብዳር ግን ለክሪስማስ የፈረንጅ ማሲንቆ( ቫዮሊን ) ተሸለመች፤ እንደሚጠበቀው ባይተዋርነት ይሰማት ነበር፤ በጊዜው የነበራትን ስሜት በማስታወሻዋ እንዲህ ገልጻዋለች፤
“ በጊዜው ከስነፍጥረት ጋር ወዳጅነት ነበረኝ ! አበቦችን እንደ ውብ ልእልቶች ፥ ዛፎች ዘበኞቻቸው፥ ነፋስ ፈጣን መልእክተኛ ፥ ጸሀይ ደግሞ የአለም ንጉስ ሆኖ ይታየኝ ነበር”
የማስታወሻው ፍሬ ሀሳብ የውብዳር የነበረችበትን የብቸኝነት ጥልቅት ያሳያል፤ በሌላ በኩል ረቂቁን ወደ ግዙፍ የመቀየር ተሰጥአዋ ይታያል::

የውብዳር ወጣትነት ህይወት ውስጥ ያለው አንድ ቁልፍ ቃል ቢኖር “ ማምለጥ” የሚባል ቃል ይመስለኛል፤ ባይተዋርነት ይከብዳታል፤ ያም ሆኖ ባገር ቤት መቀመጥ የምትወድ ሴት አልነበረችም፤ የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤት ውስጥ የነበራትን ስራ ለቀቀችና ወደ ካይሮ ሄደች፤ እዚያ እያለች ሮማንቲክ ልቦለዶችን ማንበብ ብቸኝነቷን ለማምለጥ ተጣጣረች፤ ግን በልቦለዶቹ ውስጥ የምታገኛቸው መራር ታሪኮች ፍቅርና ሰውን እን እንድትጠላ አደረጋት፤ ከካይሮ መልስ የእንግሊዝ የትምህርት እድል አገኘች፤ የትምህርት ምኒስትሩ አቶ ሳህሌ ጸዳሉ፤ ከአባትየው ጋራ ተጠማምደደው ስለነበር እድሉን አጨናገፉባት:: በዛሬ አነጋገር “ዲፕሬሽን “ የተባለ ቀውስ ውስጥ ሰተት ብላ ገባች :: “ ዲፕሬሽን “ በዘመኑ አማርኛ “ድብርት” ተብሎ ሲገለጽ አያለሁ፤ ግን ከዚያም የከፋ ነው፤ ችግሩ ከጥንት ጀምሮ ይታወቅ እንደነበር ፍንጭ የሚሰጡን ታሪካዊ መዝገቦች እናገኛለን፤ ለምሳሌ፤ የዋድለው ደብተራ አሰጋኸኝ ስለአጼ ቴዎድሮስ የመጨረሻ ሚስት ፥ እቴጌ ጥሩነሽ ህመምና ሞት ሲጽፍ ‘ሕመማቸው የሀዘን ህማም ነው “ ይላል፤ በርግጥም፥ ዲፕሬሽን እስከሞት የሚያደርስ ህመም ነው፤ የውብዳር እንደ እቴጌ ጥሩነሽን አዋክቦ ከወሰደው ሞት የታደጋት ፥ “ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ነው ‘ ብላ ታምናለች::

በመጨረሻ ከአዲስ አበባ ወደ ግሼን- ከግሼን ወደ ኢየሩሳሌም ከየውብዳር ወደ እማሆይ ጽጌ መነነች::

ዘጠና ዘጠኝ አመት ለጥቂት ሰዎች ብቻ እሚደርሱበት እድሜ ነው፤ አባትየው ከንቲባ ገብረእግዚአብሄር ደስታም ፥ በአምስት ነገስታት ዘመናት ውስጥ ኖረው፤ በዘጠና አራት አመታቸው ነው የሞቱት፤ ረጅም እድሜና ታላቅ ስራ የቤተሰቡ ነው !

ብዙ ጊዜ የአውሮጳ ታላላቅ ረቂቅ ሙዚቀኞችን ሙዚቃ ለማጣጣም ያደረኩት ጥረት በቅሬታ ተጠናቋል:: የእነ ቬትሆቨኝ ሙዚቃ ጆሮየ ላይ ነጥሮ ተመልሷል፤ እኔ ረቂቅ ሙዚቃ ለማጣጣም አልተፈጠርኩም ከማለት ያዳኑኝ የእማሆይ ጽጌ ዜማዎች ናቸው! በብቸኝነት ውስጥ የተወለዱ ዜማዎቿ ብዙ ጊዜ ከብቸነት ገላግለውኛል!

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
514 viewsBewketu, 06:16
Open / Comment
2023-04-20 19:42:36
ለመላው ሙስሊም የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። 

ዒድ-ሙባረክ

@bewketuseyoum19
3.0K viewsAbela, edited  16:42
Open / Comment
2023-04-20 14:36:43 ታላቅ ክቡር : ወግ ፀሀፊ
ህይወት ገናዥ : ሞት ፈልሳፊ
ብዙ ብዕር : ይዞ ባለም
እልፍ አእላፍ : ህብረቀለም
ሲያሻው ቢጫ : ሰማያዊ አረንጓዴ
ነጭ ከጥቁር : ደሞ አንዳንዴ
በብዕሩ በቀለሙ...
ሚፈጥራቸው ፍጡር ሁሉ
ደራሲዎች...
ፀሀፊዎች...
የራስን ወግ : በራስ ቀለም አታሚዎች

እኛ ደቃቆቹን
ከንቱ ፍጥረቶቹን
በምስሉ : ስላተመን
የኛን ድርሰት : የምንፅፈው እኛኮ ነን
ብዕር ሰጥቶን...
የማይነጥፍ : የማይጠፋ
ብናከስመው : የሚፋፋ
ብናጠበው : የሚሰፋ...
ያ ፀሀፊ(ትልቁ)
አፈር ክቦ : ጭቃ አቡክቶ
ከንፋስ ላይ : ብራናውን አዘጋጅቶ
...ፃፉ ሲለን
ብዙ ብዕር : እንኩ ብሎ
ለሁላችን ሲያ'ድለን
በኛ ፍቃድ : በኛ ምርጫ
ሲያሻን ጥቁር : ሲያሻን ቢጫ
ስናጠቁር ስናፈካ
ስናሳምር ስንነካካ
ነገ ከፍተን ልናነበው
ከታሪክ ላይ ልናትመው....

ሰው ሚኖረው
(ኖርኩኝ ሚለው)
አንድም ፅፎት : በእስክርቢቶ በብራና
አንድም ኖሮት : በእድል መንገድ በመከራ

ቀለም ተርፎን - እንፅፍበት መች ቸገረን
ታሪክ ሞልቶን - እንተርከው አልቸገረን
ደስ ሲለን
ቢጫችንን - አንስተን እንፅፋለን
ሳቃችንን ፌሽታችንን : ንገር ልንል እንለፋለን
ባናታችን በጫንቃችን : ሀዘን ከቦ ሲሰፍርብን
እንበርበት እንጠፋበት : ስፍራ ቦታ ሲጠብብን
ጥቁሩን መዘን - ልንፅፈው ያሰኘናል
እንደሚያልፍ ስላመንን..
እንዳንረሳው : ለትዝታ ይሆነናል

ቀለም ፃዲቅ : ቀለም እርጉም
ለአንድ ህይወት : እልፍ ትርጉም

እልፍ ቀለም..
ብዙ ፍጡር : ብዙ መልአክ
ለ1 ህይወት : በአንድ አምላክ

በአበኒ የተጻፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.8K viewsAbela, 11:36
Open / Comment
2023-04-20 11:39:56 እኔማ ዘንቦብኝ ፥ ኑሮዬ አካፍቶ
እንኳን አካሄዴ ፥ አቋቋሜ ጠፍቶ
በተገተርኩበት!
ቆሜ በዋልኩበት ፥ በግዑዝ አካሌ
ልጠጣ ገባለሁ ፥ አንድ ጠጅ ብርሌ
                     

በ ኪሩቤል አሰፋ

@Cher7ub

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.1K viewsAbela, 08:39
Open / Comment
2023-04-20 08:38:41 ደህና ነበርኩ እኮ

ሳልወድሽ በፊት ገና ልቤ ሳትነግሽ
በአይኔ ሳትዞሪ እንደውሃ ሳትፈሽ

እንደልጅ ጨርቅ ኳስ አይኔ ሲንከባለል፣
ያላወቀ መስሎ በአንቺው ሳይደለል

መርሳት ራሱ ራሴን ሳይረሳው
የሸጥኩት ደስታዬ በውድ ሳለምነው

ፊቴ ወዝ ሳያጣ ትዝታን ሳይተካ
ዓይኔ ሳያብጥ የእንባ ውሃ ሳይነካ

ፀጉሬ ሳይጨበርር ቅባት ሳያጣው
ከንፈሬ ሳይደርቅ መሳምሽ ሳይመታው
አይኔ ውሃ ሳያጣ ትዝታሽ ሳይሞላው
የአሁን መልኬን ጎረቤት ሳይጠላው

ያኔ ገና ሳልወድሽ በነበርኩ
ማሪያምን ነው ምልሽ እኔ ደና ነበርኩ


ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.9K viewsAbela, 05:38
Open / Comment