Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 130.11K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 126

2022-05-23 14:22:46 .


ተወደድኩ እል ነበር

ያዋራሁት ሁሉ በሳቀልኝ ቁጥር
በድካም ህመሜ እልፍ ሰው ሲያጣጥር

ተናፈቅኩ እል ነበር

ስሜን እየጠራ ጠፋህ ባለኝ ሁሉ
ሲያየኝ ፈገግ ባለ ባገር ሰው በሙሉ

ተገፋሁ እል ነበር

አስሬ የሳቀው ላንድአፍታ ቢዘጋኝ
ያቃሰተው ሁሉ ከጎኔ ቢጠፋኝ

ተሸነፍኩ እል ነበር

እንዴት ነህ? ባይ ባጣ ጧት ማታ ጠያቂ
ጠፋህ! የሚል ባይኖር እኩል ተብሰክሳኪ

አሁን ግን እላለሁ
ሁሉንም ስቻለሁ
ምክንያቱም አውቃለሁ
ይሄን ሁሉ የሆንኩት ዛሬ ላይ በእሷ ነው

በእሷ ስወደድ ነው መወደድ የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

መንሰፍሰፏ ስቦ ገዛኝ ከልብ መውደድ
ወደእሷ ያመራኝን መረቅኩት ያን መንገድ
ገና አሁን ተወደድኩ
ከአፌ ቃል ላይ ቀድማ ልቤን ሰማችልኝ
ቀልዱን ሳልኮምካት
ልነግራት ስላሰብኩ ፈገግ አለችልኝ

ይሄን ሁሉ አይቼ
እኔም ይሄን አልኩኝ ተወደድኩ እንደሰው
ተቅበዥባዡ ልቤን ፍቅር አለበሰው
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ ስናፈቅ ነው ናፍቆት ቃሉ የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

በስልኳ ውስጥ ባዳመጥኩት በውብ ድምጿ በላከችው
በደብዳቤ በሰፈረ በቃሎቿ በሳለችው
ገባኝ መውደድ አየሁ ናፍቆት
መንሰፍሰፏ ልቤን ፍቆት
።።።፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ ስሸነፍ ነው መሸነፍ የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

ታገልኳት እንደሰው እጥላት መስሎኛል
እንኳንስ ልረታት
በቅጡ እንኳ ቆሜ መፋለም ከብዶኛል
አላወቅኩም ነበር መሰበር መሸነፍ
ሲነቁ መጋደም ቀና ሲሉ መክሸፍ
እሰይ ተማርኩላት ልኬን አሳየችኝ
ይሄው ወደቅኩላት እልል ረታችኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ ስገፋ ነው መገፋት የገባኝ
የጠበበ አለሜ በልኳ የሰፋኝ

ልክ እሷ ስትገፋኝ
እስከዛሬ የወደቅኩት ህመም ሁሉ ለኔ አነሰ
የጨበጥኩት ህልሜ ሁሉ ከቅዠቴ ተላወሰ
በሷ ስገፋ ነው
የመገፋት ህመም ሰርስሮ የተሰማኝ
የመናቅ ትርጉሙ ሆድ ሆዴን የበላኝ
በሷ ስገፋ ነው
ያፈቀርኩት ቀኔ አመድ የሞላበት
ሁሉን ያለ ልቤ ፌዘኛ የዋለበት
በሷ ስገፋ ነው የተሰማኝ ይሄ ሁላ
ባዶ የሆንኩት ስም የሌለኝ ስሜት አልባ
ዋጋቢስ ነኝ የማልጠቅም የማልረባ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእሷ'ኮ ነው ከ'ሀ' ጅምር
እስከ 'ለ' 'ሉ' ፊደል ድርድር
ቃል እያማጥኩ እየፃፍኩኝ የሰረዝኩት
ይሄን ግጥም ግጥም ብየ የጨረስኩት

የምር በእሷ
አይ እሷ!

በአቤኒ የተፃፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.5K viewsAbela, 11:22
Open / Comment
2022-05-23 06:39:45 መልካም ዜና

|| ቤቲንግ እየተበሉ ተቸግረዋል ?? እንደዛ ከሆነ ከኛ ጋር ወዳጅ ይሁን እና በቀላሉ ያሸንፉ ስራችን ምስክር ነው ቻናሉን ገብታችሁ ተመልከቱት 100% የተረጋገጡ Fixed Oddኦችን እንለቃለን
123 viewsENFALOTE‌‌ ° , 03:39
Open / Comment
2022-05-23 06:29:32
• አስደሳች ዜና • !

•ማንኛውም አይነት አዲስ የአማሪኛ ዘፈኖችን የሚገኝበት ምርጥ ቻናል ነው
ከ 140,000 በላይ ተከታዮች የሉት ን ቻናል ይቀላቀሉ

https://t.me/joinchat/7b8Hl8TeX1xiMGQ0
https://t.me/joinchat/7b8Hl8TeX1xiMGQ0
80 viewsENFALOTE‌‌ ° , 03:29
Open / Comment
2022-05-22 16:01:40
ልጆች ኘሮግራም

ልጆቻችሁን በብላቴና የ YOUTUBE ገጽ ላይ “ከልጆች አንደበት” የተሰኝ ትኩረቱን በልጆች ላይ አድርጎ የሚሰራ ዝግጅትችን ላይ እንዲቀርቡ የምትፈልጉ ወላጆች ከወዲሁ ልጆቾን እንዲያስመዘግቡ እንጠይቃለን።

የልጆን መሉ ስም እና ስልክ ቁጥሮን በመላክ ማስመዝገብ ይችላሉ ።
@ab1639 ላይ ይላኩልን ።
4.3K viewsAbela, 13:01
Open / Comment
2022-05-22 13:20:06 አይ እኔ እድለኛው
አይ እድል ጉደኛው
ስንቱን ያሳየኛል
ማፈቅራትን ነጥቆ
አፍቃሪ ይሰጠኛል

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.3K viewsAbela, 10:20
Open / Comment
2022-05-22 09:25:54 አሸዋው የማን ነው?
አለቱስ የእግዜር?
ቤት ስሩ ለማለት
ምንድን እንዲህ ማሴር?



«...አለቱ
አይበገር ቢገፋ፣
ላይፈርስ ሚያለፋ፣



«...አሸዋ
እፍፍ ናት፣
ብንን ናት፣
የነፋስ ድል እራት፣
በእርሷ ታዛ ስታድር፣
“መፍረስን ግን ፍራት”!
ታዲያ
ተናናነቀኝ በቀኝ መልስና ጥያቄ፣
ይገለጣል ቢሉኝ፣
መገላለጥ ሆነ፣
ማደሪያዬን ፍቄ!

«...አለት ነኝ
አልነቃነቅም ብል አፌን ሞልቼ፣
ፈራሽ ነኝ ለንፋስ ብል ግፊት ሸሽቼ፣
ነፍሴን ምን ሊጠቅማት?
መኖሯን ነው የቀማት!

ከአለት
ካ'ሸዋ
አልተሰራም ቤቴ..
ከምን?
ለሚሉኝ ግን ለመመለስ ፈራው፣
አሸዋውስ ነበር ከቤቴ የተሰራው!

ናታን ኤርሚያስ

.
@nathanErmias
@nathanErmias

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.0K viewsAbela, 06:25
Open / Comment
2022-05-22 06:24:36 የ 25 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው
13' ደቂቃ ነው የቀረው ተዘጋጁ ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ተቀላቀሉ በቀጣይ የ50 ብር ይለቀቃል ሼር ያድርጉ
190 viewsENFALOTE‌‌ ° , 03:24
Open / Comment
2022-05-21 23:33:21
ጦቢያ ላይ የምታውቁት ተስፋሁን (ፍራሽ አዳሽ) የተቀነጫጨቡ ቀልዶችን ለማግኘት ተመራጭ ቻናል አቅርበንላችኋል አሁኑኑ JOIN በማለት መቀላቀል ይቻላል።
https://t.me/+W8C914USXYY0NDNk
1.2K viewsENFALOTE‌‌ ° , 20:33
Open / Comment
2022-05-21 19:32:16 ኑ ተቀራመቱ !
'''''''''''''''''''''
አንድ ቁራሽ ዳቦ ያጠግበኛል ብለው
እዩ ሲቧቀሱ ከጓዳዋ ገብተው
ኑ ተቀራመቱ፣
ድርሻን ሊካፈል ነው ሁሉም ሰው ጉጉቱ
ከዚህ ቅንጣት እህል ምን እርባን ይገኛል?
የአንድ ዕለት ጉርሻ ስንት አመት ያጠግባል?
ለስንትስ ዘመናት ረሀብ ያርቃል?
ሰው ይጋደላል ወይ ለቁራሽ ጠበኛ
ይናዳል ወይ ካስማ ለአንባሻ ቅሚያ?
ብቻ ፣ ኑ ተቀራመቱ፣
ከጉርሻ ባታልፍም ዙሪያዋን ቀንጥቡ
ቁጭ ብለን ከምናይ ሆድ በከርስ ተክቦ
እኛም እንቃመስ ይቺን የሀገር ዳቦ።
'ካለም የተቀዳ ስንዝር መሬትሽን የሚሸነሽኑ
ከምኑ ምን ቆርሰው ከየቱስ ምን ሊያስቀሩ
የግማሽ ብርጭቆ ውሃ ለመጠጣት
ሸክላው ይሰበራል ከመጋፋት ብዛት
አትቀነጣጥቧት አትቦጫጨቋት
መልኳን አትደልዙ ይልቁን ጠብቋት
ትቀመጥ በመሶብ ትኑር ተዘልላ
ክብሯ ጌጧ ይሁን ታመስግን በተድላ
አትቀራመቱ !
እንኳን ሀገር ቀርቶ፣ አለምም አይበቃም ለሰው ልጅ ስፋቱ።

Nuniyat

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.1K viewsAbela, 16:32
Open / Comment
2022-05-21 18:49:54
Liyu Furniture
የተለያዩ ምርጥ ምርጥ ሶፋዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንሰራለን። ይዘዙን
በጥራት አንደራርም

0911468394
@abela1987
3.1K viewsAbela, 15:49
Open / Comment