Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 144.53K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 13

2023-03-16 20:38:21 ክፍል ፩

"ልሳልህ?" አልኩት
ዝም ብሎ በተቀመጥኩበት ካፌ ወንበር ስቤ ከተቀመጥኩ በኋላ(መቀመጤን እስካሁን አላየኝም ነበር ከየት እንደመጣችሁ ራሱ የሚያውቅ አይመስለኝም)
ቀና ብሎ አየኝ ምኔን እንዳየኝ አላውቅም ለመመለስም ላለመመለስም የሚሆን ነገር ያጣ ይመስላል ሁኔታው

"አቤት?"

"አቤት አይባልም እሺ ወይም እንቢ ነው የሚባለው ል ሳ ል ህ ወ ይ?"
ተስተካክሎ ለመቀመጥ ሞከረ ምን እንደሚል እያሰበ ይመስላል
ክብ ፊቴ ላይ አፈጠጠብኝ ለነገሩ እኔን አይቶ ብቻ ምንም አይገባውም ጥልቅ ትመስላለች የሆነች ሊያነቧት ቢጀምሩ የማታልቅ ነገር ይሉኛል ብዙወች የሚያምር እና የማያምር አካሌን ለመቁጠር የሚያስችል ሁኔታ ላይ ያለ አይመስልም። የሴት ውበት ለመለካት ቀርቶ ከሴት ጋር አደለም ከሴት ጋር ከሰው ጋር መነጋገር ራሱ አላሰኘውም።ምን ሊሰራ እዚህ ካፌ እንደገባ እንኳን የሚያውቅ አይመስለኝም ኧረ ምን ያህል እንደቆየ ማወቁንም እንጃ

"ፌቨን እባላለሁ" አልኩት

"እሺ"

"ኧረ እሺ አደለም የሚባለው እኔ ደሞ እገሌ አባላለሁ ነው የሚባለው"

"ምኔን ነው የምትስይው?"

"እ?"

"ማለቴ ለምን ነው የምትስይኝ?"

"አንዳች ነገር ስላየሁብህ"

"ምን ነገር?"

"እሱን እንኳ ከሳልኩህ በኋላ ባሳይህ ነው ደስ የሚለኝ"

አሁን ትንሽ ነቃ ያለ መሰለ

ከካፌው ውስጥ የተከፈተው የኤፍሬም ሙዚቃ ይሰማኛል
"
.
ኮኮብ ተገለጠ ተሸኘ ፀሐይ
ልቤ ረጋ ሳይል አይኔ ሰው ሳያይ
እሷም አልተገኘች ብደክም ብለፋ
ፍቅሬስ አቦል ነበር አጣጪው ባይጠፋ
....." ለኔ እንደሆነ እየተሰማኝ ዘና ለማለት ሞከርኩ።

ከኔ ላይ የሚስብ ነገር? ያውም በአሁኑ ሁኔታየ? እያለ የተገረመ ይመስላል

"ተቀመጭ" አለኝ

ሳቅኩ ከልቤ ሳቄ አልሞቀውም አልበረደውም እንዲሁ ነው ስስቅ አልሳብኩትምም አልደበርኩትምም

"ከተቀመጥኩ እኮ ቆየሁ ባይሆን አንተ ተቀመጥ"

"ምነው የኔስ መቀመጥ አይታይሽም?"

"መስሎህ ነው እንጂ አየር ላይ ነህ አልተቀመጥክም በሀሳብ ሩቅ ሄደሀል ከቅድም ጀምሮ የተቀመጥክ መስሎሀል እንጂ አልተቀመጥክም ያለህ መስሎሀል እንጂ የለህም" ይሄን እያልኩት አንዲት ጠይም ልጅ እግር አስተናጋጅ ማኪያቶ ይዛ መጣችና ከፊት ለፊቴ አስቀመጠችልኝ ፈገግ ብየ አመሰገንኩና ማማሰል ጀመርኩ(መቼ አዝዛ ነው? እያለ የተገረመ ይመስላል) ይሄኔ ነበር እሱ ያዘዘው ሻይ እንኳ መጥቶ መቀዝቀዙን ያየው

እንዲህ ሲሆን የመጀመሪያው አይመስለኝም። እዚህ 4ኪሎ ቅድስተ ማሪያም አካባቢ ካለው ካፌ በመስኮቱ አሻግሮ አንዳች ነገር ላይ ያፈጠጠ ይመስላል ወጪውንም ወራጁንም ታክሲውንም ሁሉንም ያያል። ግን ደግሞ በዛውም ልክ ማንንም እያየ አይደለምደ ቅርብ ይመስላል እንጂ ሩ ቅ ነው ሩቅ ነው ቢሉትም ግን እሱ እዚሁ ነው እዚህም ነው እዛም ነው ግን እዚህም የለም እዛም የለም እንዲህ ያረገዋል መሰለኝ አንዳንዴ

አንዴ ፉት ካልኩለት በኋላ እኔም በሀሳብ ሄድኩ የተከፈተው ሙዚቃ ወደማለቁ ነበር። አብሬ እየዘፈንኩ ነው ለማለት በሚመስል መልኩ ከንፈሬ ይንቀሳቀሳል
"
..
መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ
መቼም መተው መርሳት እያውቅበት ሆዴ
ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው
ማን አለኝ እንዳንቺ ነፍሴን የወረሰው
..."

"እኔ እምልህ ለምነህ ታውቃለህ?"

"ማንን?"

"ማንንም ሊሆን ይችላል ፈጣሪህን ወላጆችህን ጓደኞችህን የማታውቀውን ሰው ወይም ራስህን?"

"ራስህን?"

"አወ ራስህን"

"ራሴን ደሞ ምን ብየ ነው የምለምነው?"

"እስኪ ብሮ 15 ብር አበድረኝ ብለህ ልበልህ?" ብየ ፈገግ አልኩ
ፈገግ አለልኝ(ያለ መሰለኝ)

"ለምሳሌ የሆነ ባህሪን እንዲተውልህ የወደድካትን ልጅ እንዲያናግርልህ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወይም ሲጠየቅ ይቅር እንዲል አለ አደል ለምነኸው አታውቅም?"

"እኔ እንጃ"

"እንዴት እኔንጃ"

"ማነሽ?"

"ማለት?"

"ማለትማ አንቺ ማነሽ እንዴት ከመሬት ተነስተሽ ስለይቅርታ ልታወሪኝ ቻልሽ? እንተዋወቃለን? ማነው የላከሽ ምንድን ነሽ? ማነሽ?".....

...ይቀጥላል...

በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.5K viewsAbela, 17:38
Open / Comment
2023-03-16 13:56:51
እረፍቶትን ቤት ውስጥ እያሳለፉ መጽሐፍ ማንበብ ትረካ መስማት ምርጫው ከሆነ ትክክለኛው ቦታ ላይ መተዋል የሚፈልጉትን መርጠው ያዳምጡ ያንብቡ
3.5K viewsAbela, 10:56
Open / Comment
2023-03-16 13:01:47 ሲመሽ
____

ሚደምነው ለኔ ፥ ሚጨልመው ለአንቺ፣
ሚያነቅፈኚ እኔ፥ የምትደሚው አንቺ፣

ገና ሳላውቅ መንጋት
ገና ሳላውቅ ማለም፣
ሲነጋ እንዲታወቅ
ይመሽ ጀመረ ይበልጥ እንድደመም፣

በድንግዝግዝ ሰማይ፥ መማሩን ለሚችል፣
መሽቶበት ለሚውል፥
ወገግ ሲል ማዬት ፥ምን ያህልስ ደስ ይል፣

___
ግዕዝ ሙላት


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.6K viewsAbela, edited  10:01
Open / Comment
2023-03-15 21:37:36 #ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_06 (ፍፃሜ)

/2015/ጥር 24

"በ 2 ሰዓቱ በረራ ከአፄ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ ወደ ቦሌ አየር ማረፊያ አመራሁ...ልክ አዲስ አበባ እንደደረስኩ እዛው ወደ መቀለ የሚወስደኝን የአየር ትኬት ቆረጥኩ። እስከ 7 ሰዓት"

"ከአይሮፕላኑ ስሰቀል ሃናን እያሰብኩ ነበር...አይሮፕላኑ ተንደርድሮ መሬትን ሲለቅ ወደሷ እየቀረብኩ መሰለኝ በእጆቼ የሚይዛት መሰለኝ...ከሰዓት በኋላ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ደረስን...ከአየር ማረፊያው እንደወጣው ተደርድረው ከቆሙት የኤርፖርት ታክሲዎች ካንዱ ገባው...የመጀመሪያው ጉዞዬን ወደ ቅዱስ ቂርቆስ  ቤ/ክርስቲያን አመራሁ ልክ ከቤ/ክርስቲያኑ ስደርስ ልቤ በፍጥነት መታ እጆቼ መንቀጥቀጥ ጀመሩ...እየተርበተበትኩ መላ ሰውነቴን በትምህርተ መስቀል አማተብኩ..."

(ትውስታ)

"ድንጋቴ ከቦናል የብርሃን ልክ አለመሆን ሁላችንንም ግራ አጋብቷል ' ምን ሆነሻል....የት ነው ምታውቂያት' አይን አይኔን እያየች 'ጥሩ ልጅ ነበረች በጣም ጥሩ' ቃሏ ጭንቅላቴን የናደው ያህል ተሰማኝ ጉልበቴ መና ሆነ አንደበቶቼ ተሳሰሩ የምጨብጠው አጣሁ ካይኔ ምንም አይነት የእንባ ዘለላ አልወጣም አይኖቼ ዝም ብለው ይቁለጨለጫሉ 'ሁፍፍፍፍፍ ደከመኝ'"

"ከብርሃን ጋር አብረን መቀሌ ገባን ዱዳ የሆንኩ ይመስል መናገር ይከብደኝ ጀመር...ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርሰቲያን የመቃብር ስፍራ ወሰደችኝ...ከልቧ እያለቀሰች 'ይሄ ነው' አለችኝ..ከመቃብሩ የተቸነከረው ጣውላ ላይ 'ወ/ሪት ሃና አረጋዊ ከአባቷ አረጋዊ በርሄ እና ከእናቷ ትርሃስ ፍፁም በ 1980 ተወለደች....1980-2014' ይል ነበር"

#መቀሌ 2015

"የሃና መቃብር ላይ የሷን ፎቶ የያዘ ሀውልት ተሰርቷል...ሀውልቱ ላይ እንደደረስኩ 'አይ ሃና ጥለሺኝ አረፍሽ አይደል....ትንሽ እንኳን ብትጠብቂኝ ምን አለበት...አየሽ ደሞ በራሳቸው ችግር እኛን ሲበጠብጡ አየሽ መንግስታችንን አንቺን ሲነጥቀኝ...ምን እንደሚቆጨኝ ታውቂያለሽ ለመጨረሻ ጊዜ አይንሽን አለማየቴ...ነይ እስቲ ሃያ አመታት እንመለስ አይናፍቅሽም እንዴ...እኔም እኮ ደከመኝ እእእ አንመለስም እስቲ እግዜርን ጠይቂው እንቢን እኮ አያውቅም ሃያ አመታት ይመልሰን' አይኖቼ ማረፏን ከሰሙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንባ አፈሰሱ"......"አድማጮቻችን **(ሁለት ኮኮብ) ከተሰኘው የደራሲ አብዮት ወጋየሁን የአጭር ረዥም ልብወለድ በኪሩቤል እና በፍሬህይወት ቀረበላቹ በሌላ ልብ ወለድ እስከምንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑ።"

/2025

"በጎንደር ከተማ ፍሎሪዳ ሆቴል በተዘጋጀው የስነ ጥበብ ፕሮግራም ደራሲ አብዮት ተገኝቷል። የግጥም እና የትወና ፕሮግራም ከተላለፈ በኋላ ደራሲ አብዮትን ወደ መድረክ ጋበዙት...የድምፅ ማጉያውን ከተቀበለ በኋላ 'እንደምን አመሻችሁ የተከበራችሁ የስነ ጥበብ አፍቃሪዎች...ያው አሁን እዚ መድረክ ላይ የተገኘሁት እስካሁን ድረስ ለጋዜጠኞች መልስ ያልሰጠሁበት ጉዳይን ለመናገር ነው...ብዙዎቹ ስለ መፅሃፌ ጠይቀውኛል እናም ስለመፅሃፌ ልናገር የምሻው ነገረ #አንደኛ ልብወለድ አለመሆኑ #ሁለተኛም ልብ ወለድ አለመሆኑ ነው። እዚህ መፅሃፍ ላይ የምትመለከቱት የራሴን ታሪክ ነው...የምወዳትን ልጅ በተቀበረ ፈንጅ ምክንያት ተሳፍራበት የነበረው መኪና በመፈንዳቱ እስከ እናቷ ድረስ ለዘለአለሙ አርፈዋል..ያኔ ጦርነቱ ተባብሶ እያለ የብዙ ኢትዮጰያዊያን ህይወት አልፏል እናም ደሞ እዚህ መፅሃፉ ላይ የምታዩት ምስል የማይሰራ አምፖል ነው ከተለያየ ቦታ የምንሸምተው አምፖል እኛን ካልጠቀመ ወየንም ደሞ ለትንሽ ጊዜ በርቶ እንደገና ሚጠፋ ከሆነ መወርወሩ አይቀርም ለማለት ነው አመሰግናለው።' አዳራሹ በጭብጨባ ቀለጠ ትላልቅ ደራሲዎች ከመቀመጫቸው ተነስተው አመሰገኑት...የመፅሃፉ መዝጊያ ላይ 'መኧለ ፀነሰቻት መኧለ ወሰደቻት' ይላል"

በዚህ አበቃው!

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.9K viewsAbela, 18:37
Open / Comment
2023-03-15 12:59:19 እንደ አያያዜማ እንደ አስተቃቀፌ
መች እሰጥሽ ነበር አንቺን አሳልፌ

ግን ግዜ ጀግና ነው መቼ እራራልኝ
በትዝታ አስቆ አንቺን መነተፈኝ
.
.
.
.
ከሳቄ እፎይ ብዬ ጎኔን ብዳብሰው
ከግዜ ጋር አድገሽ ለምደሻል ሌላ ሰው

ዳዊት ጌታቸው
@addemiinilik

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.6K viewsAbela, 09:59
Open / Comment
2023-03-15 11:17:39
#መሪጌታ_መንግስቱ የባህል_ህክምና
በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋ 0919525031
1 ለመፍትሄ ሀብት
2 ለህማም
3 ለመስተፋቅር
4 ቡዳ ለበላው
5 ለገበያ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ሚስጥር የሚነግር
8 ራዕይ የሚያሳይ
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ስራይ
14 ጋኔን ለያዘው ሰው
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለቁራኛ
17 ለአምፅኦ
23 ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ

1 የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ  መፍትሄ
2. ከሀገር ውጪ ስራ እድል ላጡ
3. ንግድ ጀምረው አልሳካ ላላቸው
4. ገንዘብ ለሚያባክኑ
5 ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ 
6. ለሀብት  ለንብረት ሚሆንም አለን
7   ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
8 ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
9. ትምህርት አልገባ ላለው
10 መስተፋቅር ፣የህዝብ መስተፋቅር
11. ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸው ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን  ይምጡ ይደውሉ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
0919525031
+251919525031
ባላቹህበት እንሰራለን
229 viewsAbela, 08:17
Open / Comment
2023-03-15 11:01:22 አሁን ደሞ
ነጋ
አሁን ደሞ
መሼ
በሚል ሀሳብ ተወጥሬ ፣
እንዴት ተስፍ ይታዬኚ በምሬት ታጥሬ ፣

ተመስገን ለዛሬ
___

ግዕዝ ሙላት


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
406 viewsAbela, edited  08:01
Open / Comment
2023-03-14 20:18:52 #ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_05 (ደሴ)

"የደሴ ከተማ ከተባለላት በላይ ደስ ትላለች የመሬት አቀማመጧ የገንፎን ቅርፅ ትመስላለች ዙሪያዋን እንዳለ በተራራ ተከባለች...ከተማዋ ውስጥ አይሱዙ ጭነት መኪናዎች ይበዛሉ፣ ጅምር ፎቆች አልፎ አልፎ በየመሃሉ ብቅ ብለው ይታያሉ።"

"ከእናና ለምለሟ ቤት በእንግድነት ካረፍኩ ሳምንታትን አስቆጥሬኣለሁ..የእናና ለምለሞ ቤት ከመንገድ ዳር በጭቃ የተሰራ ሲሆን ውስጡ ደግሞ ዘመድ አዝማድን ይሰበስባል...እናና ለምለሟ ከኔ ጋር ሌላ እንግዳ ይዛለች...እንግደዋ የትግሬ ክልል ተወላጅ ነበረች። ጦርነቱ በተስፋፋ ሰዓት ከእናና ለምለሟ እግር ወድቃ ጦርነቱ እስኪያልፍ ካዘለችው ልጇ ገር እዲያቆዯት ለምናቸው ነበር፣ ያዘለችው ልጅ ገና ጡት ያለቆመ የ 4 ወር ህፃን ነበር። ...አሁን ላይ ከበዳችሁኝ ሳትል አንድ ቤት ውስጥ የበሉትን በልተን እናድራለን። ከቁርስ ሰዓት በኋላ ከጎረቤቶቻቸው ጋር ቡና አፍልተው እንጨዋወታለን...ከሙስሊሙም ከክርስቲያኑም ደስ የሚል ጊዜ። ሙስሊሙም ሲመርቅ ክርስቲያኑም ሲመርቅ አሜን....እግዜር ይስጥልኝ፣ አላህ ይስጥልን አየተባባሉ አብረው ይኖራሉ...በኔ በኩል አስቀንተውኛል።"

"ረፋድ 4:35 ላይ እንደተለመደው ቡና ተቀራርቦ ተመራርቀው ካበቁ በኋላ እንዴትና ለምን እዚ እንደመጣው የእናና ለምለሟ ጎረቤቶች ጠየቁኝ....'የመጣሁበት ምክንያት አብሮአደጌን ፍለጋ ነው። በወቅቱ ወደ መቀሌ ይዞኝ የሚመጣ አውቶቡስ አልነበረም አየር መንገድም ወደ መቀሌ መስመር አይሰራም ነበር። ያለኝ አንድ አማራጭ ወታደር መስዬ ደሴ መግባት ነበር ከዛ በኋላ ቀስበቀስ ወልድያ ከዛ...ራያ...ኮረም...እያልኩ መቀሌ መግባት ነበር አላማዬ' በዝምታ እና በጥሞና ካዳመጡኝ በኋላ 'እና የኔ ልጅ መቀሌ ገብተህስ ምን ታደርጋለህ የት ብለህስ ነው ምትፈልጋት?' ብለው የእናና ለምለሟ ጎረቤት ወ/ሮ ነጃት ሲጠይቁኝ ሁሉም ቁጭ ያሉት 'አዎን ልጄ ከዚ በፊት መቀሌን ታውቀዋለህ ለሃገሩ ባዳ እንዳትሆን እዛ ሂደህ' እያሉ ሃሳባቸውን ማጋራት ጀመሩ 'አይ ለሱስ አታስቡ ከዋሌቴ ኪስ ውስጥ ፎቶዋን ይዣለሁ' ብዬ ፎቶዋን አሳየኋቸው...ከኔ ጋር አብራ በእንግድነት የቆየችው ብርሃን የሰጠኋቸውን ፎቶ ስትመለከት ቀይ የነበረው ፊቷ ደም መሰለ...የሚያምሩት ትላልቅ አይኖቿ በፍጥነት ተርገበገቡ...ፎቶውን የያዘችበት ጣቶቿ ተንቀጠቀጡ...ከአይኖቿ ስር የእንባ ዘለላዎች ወረዱ።"

#2015

"ተጣልተው የነበሩት መንግስታት ከተስማሙ ወራትን አስቆጥረዋል እኔም ከደሴ ወደ ጎንደር ከተመለስኩ ቆየሁ። ቤቴ ውስጥ ያሉት እቃዎች ዝርክርክ ብለዋል...ብዙ ወረቀቶች ከአልጋዬ ላይ ተበታትነዋል...ከአልጋዬ ስር ደሞ ተጨመዳደው የወደቁ ወረቀቶች ቄጤማ መስለዋል..በ 1 ወረቀት ላይ በትልቁ የፃፍኩት ፅሁፍ አየሁትና ፈገግ አልኩ
'አገኘኋት' ይላል።

ይቀጥላል....

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.2K viewsAbela, 17:18
Open / Comment
2023-03-14 15:43:42 .........አስለቃሽ ጭስ
አደንጓሬ በበቆሎ
በልቶ በልቶ ተገንፍሎ
ስብሰባ ላይ በድንገት
ሆዱ ተወ ጥሮበት
አስጨናቂ ፈስ ይዞት
ሲያጣ የሚ ገባበት
ሊለቅ ሲል በዝግታ
ብሎ ወጣ ታ ታ ታ ታ
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
706 viewsAbela, 12:43
Open / Comment
2023-03-14 09:30:34 አያ ሙሌ
____

አያ ሙሌን መስዬ
ቅርፅ ጥን ስሰራ፣
ሙሉጌታን ይመስል
ከሀሳቦች ጋራ ፣
ሁኜ ባላጋራ፥
ከራሴ ስዳራ ፣
ማንም ሳይረዳው
ከዘመኔ በሯል የፊደሌ ቁራ፣

እፅፍለው እኔ፣ ብዕርን አምኜ፣
ከዘመን ቀድሞ፥ የፃፍኩት ስንኜ፣
ይረዱትስ ይሆን ከትናንቱ ሁኜ
ትውልድ ይዘክረው ፥እኔ ሞት ላይ ሆኜ፣

እንጃ እሆን_ ይሆን አያሙሌ፣
ለማትነሳ ጥበብ
በስጋ መረገጥ ይሆናል እድሌ ፣

እያልኩኚ በውኔ፣
ስንኚ እቀርፃለው
ፊቱን ሳዬው በአይኔ ፣
____

መታሰቢያነቱ:_

ለባለቅኔው :ሙልጌታ ተስፍዬ (አያ ሙሌ)
( ሳይነሳ ለወደቀው )

---
ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.9K viewsAbela, 06:30
Open / Comment
2023-03-13 23:25:13 ሙዚቃ ትወዳለክ/ሽ ?
356 viewspetelare Stay true, 20:25
Open / Comment
2023-03-13 22:49:02 አንድ ገራሚ ቻናል ልጠቁማችሁ ......  ቻናሉ " ከአለም ድንቃድንቅ " ይሰኛል .....

ይህ ገራሚ ቻናል የተለያዩ አስገራሚ እውነታዎችን ፣ የሰዎች ገጠመኞችን ፣ በተጨማሪም ደግሞ እናንተን ሊፈትኑ እና ሊያዝናኑ የሚችሉ የጠቅላላ እውቀትንና እና የ IQ ጥያቄዎች የሚለቀቁበት ብቸኛ ቻናል ነዉ

ከታች ሊንኩን በመጫን ገብታችሁ ማረጋገጥ ይቻላል .... እመኑኝ በጭራሽ አትቆጩበትም 

እናቴን ከተቆጫችሁበት እኔ እቀጣለሁ
575 viewspetelare Stay true, 19:49
Open / Comment
2023-03-13 20:40:11 #ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_04 (ትረካ)


ምሽት 3:00 ፋና 98.1


#2013
"የጎንደር ኤርፖርት ላይ የወደቀው ሮኬት የአዘዞን ክፍለከተማ ነዋሪ አሸብሯል...የስልክ መስመር በሃገሪቱ ተቋርጧል....ጭንቀት ብቻ....ብዙ ሚዲያዎች የሚዘግቡት ዘገባ እልህ አስጨራሽ ነው....የ ህውሃት  እና የብልፅግና ቡድን ጦርነት መክፈታቸው ያብዛኛው ኢትዮጵያዊያን የሞት ምክንያት ሆነዋል....የብልፅግና ቡድን 'እድሜው የደረሰ ወጣት ሁሉ ለ ሀገርህ ዝመት' የሚል መልዕክት አስተላለፈ.....ወንድሜን ለመግደል....ሀገሬን ለመግደል ለሀገሬ ልዝመት አይደል......ከትንሽ ማንሰላሰል በኋላ የመንግስታችንን ሃሳብ ተቀበልኩ....ደስ እያለኝ...."

(አዘዞ:የምዕራብ ዕዝ የጦር ካምፕ)

"መለዮ ለብሰናል....በተለይ ለኔ የለበስኩት መለዮ አዘንጦኛል ማለት ይቀላል....ከፊቴ ላይ ያሉትን ውብ ፂሞቼን ተቆርጫለሁ...ለነገሩ መቆረጥ አይባልም መላጨት ልበለው...እየሸሸ የነበረውን ፀጉሬንም ድራሽ አባቱን አጥፍቼዋለው....ትግራይ ሄጄ ድል ከማድረጌ በፊት አካሌ ላይ ያሉት ነገሮች ደምስሼ ተቆጣጠርኳቸው...አቤት ወኔ...አቤት ግርማ ሞገስ..."

(ጉዞ--ከአዘዞ-ደሴ)

"አውቶቢሱ ደሴ ሊደርስ ትንሽ ሲቀረው ሹፌሩ እያጫወተው የነበረውን ሙዚቃ ቀየረው....ከዛ በፊት 'የጨነቀ ለት..እየየ' የሚለውን እያጫወተ ነበር ከዛን ደሞ 'ደሴ ላይ....ደሴ ላይ ነው ቤቷ አሄ....የሚያምረው አንገቷ' የሚለውን ከፍቶ ዘማች ወታደሩን የደሴን ጉብል አግብት እንዲሄድ ልቡን ቀሰቀሰለት...ወታደሩም የዋዛ አይደል አንገቱን በመስኮት እያወጣ መቁለጭለጭ ጀመረ።

"ደሴ ገራገሩ ደረስን ካድባሩ...ሃሃሃሃሃሃ(በረጅሙ ተነፈስኩ)...ከአውቶቢሱ በፍጥነት ወረድን...አካባቢዋን ቃኘሁት...ደስ ትላለች ደሴ...የህዝቡ አይን እኛ ላይ አርፏል በደስታ ተቀበሉን የደሴ ልጆች ደስ ብሏቸዋል...ትንሽ ከተረጋጋ በኋላ ከወታደሩ ቡድን በቀስታ እያፈገፈኩ መጣው...መቼስ የደሴ ሰው መልካም ነው..ከላይ የለበስኩትን የወታደር ልብስ አወለኩት...ወደአንድ እናት ጠጋ ብዬ እየተቁለጨለጭኩ 'ማማ እባኮትን ከጉድ ያውጥኝ የዛሬን ያውጡኝ እባኮትን...ውለታዎትን አረሳም'

ይቀጥላል....

ዮኒ
     ኣታን  @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.3K viewsAbela, 17:40
Open / Comment
2023-03-13 19:18:00 አገባህ ነበረ……………

ቆሎ 'የቆረጠምን እኖራለን ውዴ
ልጅ በልጅ ይሆናል ቤታችን መውደዴ
አንቺ ውሀ አጣጬ የእግዜር ባለ አደራ
እሺ በይኝ ላግብሽ ፍቅራችንም ይድራ::

አለኝ የኔ ሚስኪን..............
               አገባህ ነበረ..................

ቆሎ ባልቆረጥም እርሀብ ባይደፋኝ
ሊያውም በዚ ዘመን..........

ቆሎ ያልከው ውዴ
ዝም ብለህ ስታየኝ የኤርፎራ ዶሮ እመስላለሁ እንዴ?

ጭራሹን.................

ልጅ በልጅ ሆኜልህ
አንዱን ከኃላዬ ሌላውን ከፊቴ
ገሚሱን በግራ ገሚሱን በቀኜ
እሪ እምቧ ሲሉብኝ መንምኜ መንምኜ

የድስት ፍቅፋቂ በጋራ ስንበላ
ጎረቤት ቢረበሽ ይደብራል ኃላ

እኔም ተማርሬ እግዜር ከሚከፋዉ
ቆሎህን ለብቻህ ተደብቅህ ብላው::


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ (@Tizita21)


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.6K viewsAbela, 16:18
Open / Comment
2023-03-13 15:58:41
ሁቱትሲ

ፀሐፊ - ኢማኪዩሌ አሊባጊዛ እና ስቲቭ ኤርዊስ

ተርጓሚ - መዘምር ግርማ

በረዋንዳዊቷ ልጃገረድ እዉነተኛ የሕይወት ጉዞ ላይ ተመርኩዞ የተፃፈ ነው ።

የትረካ ሊንኮቹን ይንኩ File ያገኛሉ።

ክፍል 1
ክፍል 2
ክፍል 3
ክፍል 4
ክፍል 5
ክፍል 6
ክፍል 7
ክፍል 8
ክፍል 9
ክፍል 10
ክፍል 11
ክፍል 12
ክፍል 13
ክፍል 14
ክፍል 15
ክፍል 16
ክፍል 17
ክፍል 18
ክፍል 19
ክፍል 20
ክፍል 21
ክፍል 22
ክፍል 23
ክፍል 24
3.1K viewsAbela, 12:58
Open / Comment
2023-03-13 13:40:21 ዝም አልክ አትበለኝ!!!

«ስለምንሰማው - የሀገር ውጥንቅጥ
አፍህ አይለጎም - ለሀቅ ፍንጭ ስጥ
ምድሩ ረስርሷል - በንፁሀኖች ደም
ማዳበሪያ ሆነ - ስጋ ቀልጦ እንደ ሰም»

እያልክ አትንገረኝ!

«አንድ ኢትዮጵያ ብሎ - ፍቅርን አስቀድሞ
አንድ የሚያደርገንን - ባንዲራዋን ስሞ
የሚለያየንን - ጀመረ ማውለብለብ
ተንኮል ብቻ ሆነ - የህዝባዳም ቀለብ»

እያልክ አትንገረኝ!

እውነቱን ልንገርህ ፣ ምርር ብሎኛል
ድፍንፍን ያለ ሀቅ ፣ ደቁሶ ገሎኛል
ህጉ ሆኗል ጎታች ፣ ምሬት ሚያሰንቅ
ከሳሽ እያነቀ ፣ አጥፊን ሚያራቅቅ

ምንም አትንገረኝ!
ህግ ሃቅ እስኪሆን ፣ በሃገሬ ሰማይ
እንባተገድቦ ፣ ሳቂ ጥርሶች 'ስካይ፡፡

እስከዛ • • • እኔን ተወኝ
#ዝም_አልክ_አትበለኝ !


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.1K viewsAbela, 10:40
Open / Comment
2023-03-13 09:25:37 እንኳንስ የሮጠ ጀግኖ ሳይደክመው
ያነከሰው ሁላ ይቀድመኛል ምነው?
ማነው የሰፈረልኝ ጋሻ ሙሉ ለቅሶ
አይኔን ማን ሸለመው መሀረብ ተኩሶ??
በእዬዬ ዬ ዜማ አሸበል ገዳዬ
ወረዱበት መሰል ጠርጥሯል ጆሮዬ
ህልሜን ይህ ደመና ዋጠው ሳይፈታ
አምኜ እየካድኩት ሊመጣ ነው ጌታ
የኔን ደፋ ቀና ማን ፃፈው ገድሌን
በችግር ፈትኖ መች ዘገበው ስሜን
ፍርዴ ተገማድሎ በየቀኑ ስሞት
ማነው አስተውሎ ነህ ያለኝ ሰማእት?!!
እየኖርኩ ሞቻለው!!!
@addemiinilik
ዳዊት ጌታቸው


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.5K viewsAbela, 06:25
Open / Comment
2023-03-12 20:50:10 #ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_03 (ግብዣ)

የታንጉት ግሮሰሪ ከቀን ወደ ቀን ገብያው እየቀዘቀዘ መጣ....እንደዛ ቤቷን የሚያሞቅላት ተተራራቢ ጎልማሶች ዛሬ በግሮሰሪው የሉም...ደራሲ አብዮትም ከግሮሰሪው ከራቀ ብዙ አመታት አልፈውታል...ተከራይቶባት ከነበረችው ትንሽዬ ቤቱን ከለቀቀ ቆይቷል።

ነገሩ ሁሉ አዲስ ነገር ሆኗል...የአዘዞ ድማዛ ድልድይ ከድሮው በይበልጥ አምሮበታል...ከድልድዩ ስር የሚፈሰው ውሃ በተለያዩ አዕዋፋት ተከቧል...ፀሃዯ እጅግ ደስ ትላለች...ድልድዩን በግራና በቀኝ ያጀቡት ረዣዥም ዛፎች አካባቢውን ይበልጥ ሳቢ አድርታል...ከታንጉት ግሮሰሪ ዝቅ ብሎ የተገነባው ትልቅ የገበያ አዳራሽ በሰው ተጥለቅልቋል።

የጎንደር ከተማ በደራሲ አብዮት መፅሃፍ ገበያዋ ሞልቷል...ባሏት ረዣዥም ፎቆች ላይ የደራሲን አብዮትን ምስል የያዘ ባነር ሰቅላለች...ከባነሩ ስርም "ነገር ተቀይሯል...ይቀየራልም" የሚል ጥቅስ ተፅፏል።

ደራሲ አብዮት ያለበትን አድራሻ ማንም የሚያውቅ የለም ከብዙ በአንድ ጊዜ ትላልቅ መድረኮች ላይ ይሳተፋል...በሚሳተፍበትም ወቅት ብዙ ነገሮችን ይናገራል...ብዙውን ጊዜ መድረክ ላይ ግጥም ሊያነብ ወይም ደሞ ከልብ ወለዱ ላይ ቀንጭቦ ሊያነብ አይወጣም...ልክ የድምፅ ማጉያውን እንደጨበጠ የሚናገራቸው ነገሮች ከአለም ውጭ ያሉ ነው ሚመስሉት...ከበፊቱ ይልቅ አሁን ላይ ዝነኛ እና ታዋቂ ሆኗል..ተወዳጅም ጭምር....ማንም የሚዲያ ሰራተኛ ለጥያቄ ቢጋብዙት መልሱ "አይሆንም" ነው። ብዙ ጊዜ በስልክም ቃለ መጠየቅ ሊያደርጉለት የፈለጉ ጋዜጠኞችን መልስ አይሰጣቸውም....ምክንያቱ ደግሞ "እንደዚ ዝነኛ እና ታዋቂ ከመሆኔ በፊት የምናገረውን ቃል አንድም ያላዳመጠኝ ማህበረሰብ አሁን ስሜ ሲገን ለምን እኔን ፈለገ" ይላል።

"አለምን ማስቆም አንችልም ወይንም ደሞ እሷ ጋር እግር በግር መከተልም ይከብዳል...ስለዚህ ያለን አማራጭ አያስመሰልን መግፋት ነው። ከአለም ጋር አብረህ መሄድ ሳይሆን እየሄድክ ማስመሰል ነው ያለብህ...አለም በወደቀች ቁጥር መንገድህን አስተውል።" ደራሲ አብዮት በአንድ ወቅት ከታንጉት ግሮሰሪ እየጠጣ የተናገረው ነበር....በአሁን ሰዓት ከአመታት በፊት አብረውት ለነበሩት ሰዎች የሚነግራቸውን ነገር በ ማህበራዊ ገፅ ያስተላልፉታል...."አቢ...ለምንድነው ምትጠጣው" ሲባል "ከባህር የገባን ሰው ባህር ውስጥ ገብተህ እንጂ ዳር ቆመህ በእንጨት አትስበውም...ብቃት ካለህ የዛን ሰው ህይወት ከባህሩ ውስጥ ታወጣታለህ ደካማ ከሆንክ ግን አብረኸው ትሰጥማለህ....ያወራሁህ ስለመጠጥ አይደለም ስለ እኛ ነው እንጂ"።
"ብዙውን ጊዜ ፍቅረኛ ለመያዝ መጣደፍ  ልክ እሳትን በእጅ እንደመጨበጥ መጓጓት ነው...በእሳት ልጫወትም እንደማለት ነው... ምክንያቱም ፍቅር ምን እንደሆነ ስላልተረዳነው... ዘመናዊ ለመባል ብዙ ሴት ጋር ምታወራ ከሆነ መንገድህን አስተካክል ምክንያቱም ከዘመናዊነት አልፈህ ነፃ የ ዋይፋይ ኔትወርክ ስለሆንክ...ሁሉም በፈለጉህ ሰዓት ከራሳቸው ጋር ያገናኙሃል...መንገድህን አስተውል".....ደራሲ አብዮት ከአመታት በፊት ከሚጠጣባት ታንጉት ግሮሰሪ ውስጥ ከሚያውቁት ሰዎች ሁሉም ስለሱ ሙሉ ነገር አያውቁም...አንድ የሚያውቁት ነገር ደራሲ እና ገጣሚ እንደሆነ ብቻ ነው።

ደራሲ አብዮት ወጋየሁ የፃፈው ልብወለድ በ ሬድዮ መተረክ ጀመረ...." ከምሽቱ 3 ሰዓት ለአድማጮቻችን የሚተላለፈው የትረካ ሰዓታችን እነሆ ጀምረናል የዛሬው ትረካ ** ከሚለው የረዥም አጭር ልብወለድ መርጠን ለናንተ እናቀርባለን ከማስታወቂያዎች በኋላ እንመለሳለን"

" #ትውልደ_መኧለ ....ደራሲ አብዮት ወጋየሁ.....ተራኪዎች ኪሩቤል መስፍን እና ፍሬህይዎት ሺፈረው"

ይቀጥላል...

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.8K viewsAbela, 17:50
Open / Comment
2023-03-12 13:18:43
የሚፈልጉትን የመፅሐፍ ትረካ መርጠው ያዳምጡ
5.9K viewsAbela, 10:18
Open / Comment
2023-03-12 09:51:29 ታላግጪአለሽ አንቺ
____--


መውደቅ እስኪደርስ ጭቃ እስኪነካሽ፣
ንፁህ ያልሽው ወንዙ አስቆ እስኪበላሽ፣

ላለቀሰ ሁሉ ሳቅሽን ስትገልጭ፣
በሀዘን ኮፈን ደመና ቀድሞ እጂ
ሰማዬ ነበር በአንቺ የሚቋጭ፣

በምትሰሚው ሁሉ እየሄድሽ ብትከፍቺ፣
ብቻ ቀን ጠብቂ
በሀዘንሽ ሰአት
ሀዘናት በሙሉ ያለግጣሉ በአንቺ፣

_
ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
952 viewsAbela, 06:51
Open / Comment
2023-03-12 08:22:28
የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች
OPEN
892 viewsDaily promoter , 05:22
Open / Comment
2023-03-11 20:16:32 #ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_02 (ታሪክ ወደኋላ)

ደራሲ አብዮት ወጋየሁ 1 ክፍል ቤት ተከራይቶ መኖር ከጀመረ አመታት አልፈውታል በተለያዩ የመድረክ ስራዎች ላይ በመሳተፍ በሚያገኛት ሳንቲም የቀን ቀለቡን እና የቤት ኪራይ ክፍያውን ይሸፍናል ከዛ በዘለለ ለምንም ነገር አይሆነውም አንዳንዴ የቀን ቀለቡን በመሰረዝ ከታንጉት ግሮሰሪ ውሎ ያድራል።
ደራሲ አብዮት ወጋየሁ ከቤቱ ሳይወጣ እዛው በተኛበት የኪስ ቦርሳውን አወጣ...ከቦርሳው ውስጥ የልጅነት ጓደኛውን ፎቶግራፍ ተመለከተ
በመጠጥ የቀሉ አይኖቹ በእንባ ተከበቡ...በደረቁት ትናንሽ ከነፈሩ ላይ የአይኑ እንባ አረጠቧቸው...የገረጣው መልኩ በእንባ ተሞላ...ለብቻው እያንሾካሾከ"የት ነሽ..."ይላል።

#ጎንደር_ዩኒቨርስቲ_የማህበረሰብ_ት/ቤት
( #1990)

"የ 48 አንድ ሁለተኛ ስንት ነው?...እስኪ ማነው ሚነግረኝ...አብዮት እስኪ አንተ ተናገር!..." የ3ተኛ ክፍል ሂሳብ መምህር አብዮትን አይወዱትም ነበር ምክኒያቱም አንድም ቀን ተከታትሏቸው አያውቅም ብዙ ግዜ ወላጅ አስመጥቶታል ብዙ ግዜ አንበርክኮ ገርፎታል ግን ምንም ሊሻሻል ስላልቻለ መምህሩ በእሱ ተስፋ ቆርጧል። "አብዮት አንተን እኮ ነው አትመልስም!" አሁንም ዝም ብሎታል መምህሩ በጣም እየተናደደ መጣ ግን በድንገት "24" ብሎ መለሰ መምህሩ ትኩር ብሎ እያየው "ነገ ቤተሰብህን ማናገር እፈልጋለው" አለው።
አብዮት ከመቀመጫው ተቀምጦ በሹክሹክታ "አመሰግናለሁ" ብሎ ፈገግ አለ... አብሮ አደጉን #ሃና_አረጋዊን።

#2013

ሰፈሩ ሁሉ በጥይት እሩምታ ታምሷል የሴት ልጅ ጩኸት በየቦታው ይሰማል የቴሌቭዥን ሚዲያዎች እንዳለ "መከላከያ ሰራዊታችን ፅንፈኛውን ቡድንን ደምስሶታል" የሚል ዜና ብቻ ነበር የሚዘግቡት።

የትግራይ ተወላጆች ካሉበት ቦታ ተነስተው ትግራይ ክልል ገብተዋል በአንዳንዶቹም ብዙ እንግልት ደርሷል። ዲሞክራሲ ብሎ የሰየመው መንግስት ለህዝቡ መዘዝ አምጥቷል....ትግራይ ክልል የሚገኙት የሌላ ብሄር ተወላጆች ትግራይን ለቀዋል አንዳዱም ህይወታቸውን አጥተዋል።
ብዙ እንግልት ሃገሪቱ ላይ ደርሷል በ 1 ሃገር ውስጥ የ 2 ጎሳ ግጭት አለምን አነጋግሯል...ብዙ ጭንቀት....ውጥረት...ኢትዮጵያውያኑ በየሃይማኖቱ ፀሎተ ምህላ ገብቷል።

አብዮት በጭንቀትና ውጥረት የስለኩን ቁጥሮች ይነካካል...ይደውላል...አይነሳም
ይጠራል...አይነሳም
ማበድ ቀረው የሚያደረገው አጣ....እንደገና ሞከረ
"የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁ...." አላስጨረሳትም ስልኩን ዘጋው። ሀገሯ ተደበላልቃለች የጥይት እና የጩኸት ድምፅ ብቻ ይሰማል።


#2025

"የደራሲ አብዮትን መፅሃፍ በቅናሸ....እየጨረስን ነው....አነጋጋሪው መፅሃፍ....አለች በቅናሽ" ገበያው በ አብዮት መፅሃፍ ተጥለቅልቋል። በጣም ተፈላጊ ከመሆኑ የተነሳ 8ኛ ዕትም በቀላሉ ደርሷል...በተለያዩ ሚዲያዎች ስለሱ መፅሃፍ ሃያሲያንን ጋብዘው ትንታኔን ይሰጣሉ። የፃፈው መፅሃፍ ርዕሱ እና መዝጊያ ቃሉ ከሌሎች መፅሃፎች ተለይቶ ሳቢ አድርጎታል።

"ሄሎ ደራሲ አብዮት...ስለ መፅሃፍህ አንዳንድ ነገር እንድትለን ነበር ፈቃደኛ ከሆንክ".....

ይቀጥላል....


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.3K viewsAbela, 17:16
Open / Comment
2023-03-11 15:18:11
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.9K viewsAbela, 12:18
Open / Comment
2023-03-11 11:23:22

አስገራሚና አዝናኝ የመፅሐፍት ትረካዎችን ያገኙበታል።

ታዲያ ምን ይጠብቃሉ JOIN በሏ
4.2K viewsAbela, 08:23
Open / Comment
2023-03-11 09:29:56
እመ መከራ
******
/በእውቀቱ ስዩም/

ኢትዮጵያ እመ መከራ
የግዜር መመራመሪያው
የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና ፣
የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ ፣
መውድቅ ÷ መውድቅ ÷ መውድቅ ብቻ…

ሰዓሊ /ፀጋልደት/

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.4K viewsAbela, 06:29
Open / Comment
2023-03-10 20:40:06 #ከጎንደር_እስከ_መኧለ

#ምዕራፍ_1
#ክፍል_1 (መንደርደሪያ)

"ወገኛው ዛሬ ምነው ዝም አልክ እንደበፊቱ ማቅራራቱን ተውከውሳ ነው ወይስ ፉት የምትላት አረቂ እስክታሞቅህ እየጠበካት ነው።(የፌዝ ሳቅ) ኧረ ያዝማሪውን መሰንቆ ድምፁን አስዋጥከው የሆነ ነገር በለው እንጂ(ድጋሚ የፌዝ ሳቅ)"።
የሰፈሩ መንደርተኞች ከሰፈራቸው የበቀለውን ደራሲ አብዮት ወጋየሁን የራስ መዥገር ይመስል አለቅህ ብለውታል። ሁሌ ከሚያዘወትርባት ታንጉት ግሮሰሪ ውስጥ በሚናገረው ነገር አብዛኞቹ ጠምደውታል አንዳንዶቹ ደግሞ ልክ እንደ "አሃ..." መርህ ከልብ ያዳምጡታል። ደራሲው ሊናገር የፈለገውን ነገር ከመናገሩ በፊት ስለ አለባበሱ አስተያየት ይጠይቃል...አንዳንዱ "ምነው ዛሬ ደሞ የከሰረን ነጋዴ መሰልከን" ሲሉት አንዳንዱ ደሞ አለባበሱ ሳይጥማቸው "አሪፍ ነው..እእእ..ምንም አይልም" ይሉታል በፈገግታ መልሳቸውን ያብሰለስላል ትንሽ ቆይቶም ስለሰጡት መልስ ለእያንዳንዱ የተቃረነ መልስ ይናገራል በዚህም የተነሳ ከአብዛኞቹ ጥላቻን አትርፏል።

የታንጉት ግሮሰሪ ካሉበት ስፍራ እውቅናን አትርፏል በአሁን ሰዓት አንቱ የተባሉ ሰካራሞችን ለሰፈሩ ነዋሪዎች አበርክቷል የግሮሰሪው መስራች ወ/ሮ ታንጉት አንዴት ገበያሽ ደራልሽ ስትባል "እንዲያው ያደረኩት ነገር የለም ለሰፈሬ ታቦት ተስዬ ነው እንጂ" ትላለች የምታምነው አምላክ ወጣት ሳትይ ሽማግሌ አክብሪ(አስክሪ) ያላት ይመስል። ከግሮሰሪው በአንዳንዶቹ አንቱታን በአንዳንዶቹ ደግሞ አንተ የሚል ስምን ካገኙት መካከል አቶ ሳሙኤል ዋነኛ ናቸው(ነው) ። አቶ ሳሙዔል ባለው ትህትና ሰፈርተኛው "ውይ ሳሚዬ የኔ የዋህ......ጋሽ ሳሚ አሳቢየችን..."እና የመሳሰሉትን ሲሉት የሚሰራውን ስራ ልብ ብለው የተረዱት ደግሞ "እጄ ላይ እንዳይጥለው ብቻ..."እያሉ ይዝቱበታል። ስለ ሁሉም የሰፈሩ  ሰዎች የሚያውቀው አብዮት ከታንጉት ግሮሰሪ በሚቀማምሳት አረቂ የሰከረ በመምሰል ያዝረጠርጣቸዋል...ከጎናቸው በሚቀመጠው አዝማሪ ስንኞቹን እየወረወረ እስከ አዝማሪው ድረስ ይናገራል የሚረዳው የለም እንጂ።

ከምሽቱ 3:13 ሆኗል የአለምን ክፋት የተፀየፈች ይመስል ጨረቃ ከሰማዩ ላይ የለችም...ጭልምልም ብሏል ከታንጉት ግሮሰሪ ወጥተው ወደቤት የሚሄዱት ሰካራሞች የድማዛን ድልድይ ማቋረጥ ይኖርባቸዋል...የድማዛ ወንዝ ድልድይ ጣልያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለ 5 አመታት ቆየች በተባለ ሰዓት የመኸንደሱት ድልድይ ነው...ታድያ ያሁኖቹ ሰዎች አፍርሰው በቻይና አሰሩት የሚል ወሬ ተንሰራርቶ መነገር ከጀመረ ድፍን 3 አመታት ካለፈው 1 አመት ሆኖታል....ደራሲ አብዮት ድልድዩን ባቋረጠ ቁጥር  "ከድጡ ወደ ማጡ - ሸሹ እንጂ መች አመለጡ" የምትለውን ስንኝ ሳይወረውር አያልፍም...የጎንደር  ክፍለከተማ የሆነችው አዘዞ የድማዛን ወንዝ በሆዷ ታፈሰዋለች ከታንጉት ግሮሰሪ ወደ 25 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የድማዛ ድልድይ ፈርሶ ከተሰራ በኋላ ከጭነት እስከ ተሳቢ ባንድላይ ማሳለፍ ችሏል።
የደራሲው አብዮት የፍቅር ታሪክም እዚሁ ተጠንስሷል። አንዳንዴ በሚቀማምሳት አረቂ ብርታት ካገኘ በኋላ "ተቀበል" ይለውና
         "ጠጅ አይሉት ወይ ጠላ
          ህመምን ለመርሳት ተገበረ ገላ
          ምነዋ ብትፈርጂኝ ያሻገርሺኝ ወንዜ
          አረቂ እና አዝማሪ ተደበላልቀዋል ዛሬ በኔ        ግዜ
          ባንቺ እንዴት ነበሩ
           በጠጅ ነው እንጂ ባረቂ አልዘመሩ"
ይልና በረጅሙ ይተነፍሳል ከዛ በመንሾካሾክ ይመስል "ሃና...የትነሽ..." እያለ ከፊት ለፊቱ የተቀመጠውን አረቂ ይጨልጣል።
     

ይቀጥላል....

ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.6K viewsAbela, 17:40
Open / Comment
2023-03-10 20:08:04 ስለ Hacking ለማወቅ

programing ለመማር

ስለ ቴክኖሎጂ ለማወቅ

የተለያዩ app ለማግኘት

ስልክ እንዴት እንደሚጠለፍ ለማወቅ


wifi password እንዴት hack እንደሚደረግ

mega byte እንዴት እንደሚሰረቅ


telegram እንዴት hack እንደሚደረግ

ሁሉንም የ technology መረጃዎች እኛጋ ያገኛሉይቀላቀሉን
️ ️ ️ ️
122 viewsDaily promoter , 17:08
Open / Comment
2023-03-10 20:02:04
የጠበሳ ዘዴዎች ለወንድም ለሴትም ሴቶች ደፍረዉ የማይናገሩት ግን ከወንዶች የሚጠብቋቸዉ 7 ነገሮች
OPEN
122 viewsDaily promoter , 17:02
Open / Comment
2023-03-10 19:40:31 ሆድ ያባውን ፕሮፋይል ያወጣዋል ይባል የለ #ለፕሮፋይል የሚሆኑ ምርጥ ምርጥ ፎቶዎችን  ለማግኘት ይቀላቀሉን
279 viewsDaily promoter , 16:40
Open / Comment
2023-03-10 19:12:03
ድንግልናዬን ማን ወሰደው
ቤቲ እባላለሁ በጣም ቆንጆ እና ቀበጥ የሀብታም ልጅ ስሆን 12 አመቴ ነው ከትናንት ወድያ ሰለ አረኩት ፊልም የሚመስል .... ታሪክ ልንገራችሁ ልጁ አቤል ይባላል የ ወንድሜ ጐደኝ ነው በብዛት እኛ ቤት ይዉላል በግዜ ማንም አልነበረም በቤት ዉስጥ ልወጣ ስለነበረ ሻወር ልወስድ መታጠቢያ ቤት ገባሁ ስገባ ግን ያልጠበቁት ነገር ነበር ያጋጠመኝ.......ሙሉውን ለማንበብ ይጫኑ
https://t.me/+UDVG8pKU_sO-jVlN
677 viewsDaily promoter , 16:12
Open / Comment