Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 130.11K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 177

2021-12-27 12:19:47 ጉድ
::::::::::::::::::::::::::::
ሠይጣን መነኮሰ
ገዳም ገባ አሉ ከእግዜር ተታረቀ
ነፍሱን አፀደቀ
ሱባኤ ለሀጥያቱ
ቀኖናዉን ያዘ ለአባ ፍትሀቱ
ሁዳዴን 40ቀን
ሳይታክት ቀን በቀን
እያደገደገ.........
ዳዊት ደጋገመ ሊፀድቅ ወስኖ
ሸይጣን ሰይጣኑ ወጥቶ_ከሰይጣን ተቃርኖ
::::::::::
::::::::::
ሠዉ ሆይ አደራህን እንዳታሳስተዉ
እሱም ብዙ ነበር ካንተ የተማረዉ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde
2.2K views09:19
Open / Comment
2021-12-26 18:49:59 ኗሪ እንጂ ሐጅ ቤት አይሰራም
(ታደሰ ደምሴ)

እየተቃቀፍን አንራራቅ
እየተካበርን አንናናቅ

ስንቀራረብ አንቃቃር
እየተሳሳምን ፊት አንዟር

በልሳን ውበት መካን ይብቃን
ከወረት ጸድተን ፍቅር ይግባን

ባንድ ተኝተን አይብረደን
የበረዶ ማት አያስምጠን

የቃል ሽንገላ ግብር አይሆንም
ኗሪ እንጂ ሐጅ ቤት አይሰራም

የናፍቆት ጅራፍ ካልገረፈን
የትዝታ ወጀብ ካላማታን
የዕምባ ማዕበል ካላጠበን

መለየት ከሆነ ተገናኝተን
የመውደድ ጥጉ መቸ ገባን!

ይልቅ...
ነፍስሽ ከነፍሴ ይወዳጁ
ልብሽ ከልቤ ቀን ይዋጁ

ከየራስ አለም ተሰብስበን
አብረን እንክነፍ ሁሉን ትተን

ያኔ ...
አብረን ስንከንፍ...
የጸሀይ ግለት አያጠቁረን~የብርድ በትር አያጠቃን
በኛ ውስጥ ንግስናን ሽቶ ~ሀገረ ገዢ ንቆ አይደፍረን
"ንጉስሽና ንግስቴ"~ መሆናችንን ችሎ አይነጥቀን!

አዋን...!
አብረን ስንከንፍ...
የሲኦል ነፍሳት ግድ አይሰጠን
የኩነኔ እዳው አያስፈራን

አዎን...
አብረን ስንከንፍ...!
ፈጣሪ ከጽድቅ አይነጥለን
ከፍቅር በላይ ምግባር ሽቶ~ትዛዛቶቹን አይጠይቀን
እኔ ባንቺ አንቺ በኔ ~የገነትን በር እንሾልካለን!
:
:
:
ሹልክ...!

#ሼርርርር
@Maryam21161


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.5K viewsedited  15:49
Open / Comment
2021-12-26 08:59:53 ፅልመት

ብርት
ጥፍት
ምጥት
ውጥት
የሆነ ኑሮ ሆነና ነገሩ
ልብህ እና ልቤ መች ተነጋገሩ
አንተም እንደዚ ነህ.....
ልክ እንደ ሀገሬ ሙሁር
ሙጭጭ ጥብቅ ነው ባገኘኸው ነገር
ለምን ይመስልሀል........
የመንገዱ መብራት ቦግ እልም እሚለው
አዋቂ ነን ባዬች እየነካኩት ነው
እ....እና
አንተም እንደነሱ ልቤን አታጉላላው
ብዙ ሴት ስላወክ የኔን ልብ አታውቀው
.
.
.
እንባህ ሲንዠረዠር
ከእግርቼ ስር ወድቀህ ስትል ሰለ ፍቅር
አምኜህ ነበረ ልክ እንደ ጨረቃ
ሀዲያ ምን ያደርጋል...
አንተ አደረከው ተመላላሽ እቃ
ከይህ ለጥቆ ግን....
አንተ እንደለመድከው
እየተመላለስክ ልቤን አትነካካው
እኔ እንደው አልሰግድም ለሄደው ለመጣው
አንድ አንተን እንጂ ስልጣንን አልሻው
አሁን
.
.
.
አሁን
.
.
አሁን ግን ልክ እንደ ፅልመቷ
ሊበቃኝ ነው መሰል ካንተጋ ዋይ ዋይታ

ሐና ይመር
Join us
@hanayimer21


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.5K views05:59
Open / Comment
2021-12-25 22:03:38 ሙሉ አልበሙን በስልክ ጥሪ መልክ በኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪዎች ቻናል ላይ ብቻ ያገኙታል። አሁኑኑ ገብተው ያውርዱ
https://t.me/joinchat/wIvHsnzXVOk3ZGRk
1.6K views19:03
Open / Comment
2021-12-25 21:22:43 ሙሉ አልበሙን በስልክ ጥሪ መልክ በኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪዎች ቻናል ላይ ብቻ ያገኙታል። አሁኑኑ ገብተው ያውርዱ
https://t.me/joinchat/wIvHsnzXVOk3ZGRk
1.0K views18:22
Open / Comment
2021-12-25 21:09:58 ትናንትና ማታ
(በዕውቀቱ ሥዩም)
ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡
2.4K views18:09
Open / Comment
2021-12-25 20:33:42 ሙሉ አልበሙን በስልክ ጥሪ መልክ በኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪዎች ቻናል ላይ ብቻ ያገኙታል። አሁኑኑ ገብተው ያውርዱ
https://t.me/joinchat/wIvHsnzXVOk3ZGRk
2.5K views17:33
Open / Comment
2021-12-25 19:11:17
በጉጉት ስጠብቁት የነበረው የዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ቀን አውጣላት የተሰኘው አልበም በኦርቶዶክሳዊ የስልክ ጥሪ ቻናል አማካኝነት ለስልክ ጥሪ እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል።አሁኑኑ ቻናሉን በመቀላቀል ማውረድ ይችላሉ።
https://t.me/joinchat/wIvHsnzXVOk3ZGRk
273 views16:11
Open / Comment
2021-12-25 18:25:18 እረ ማነው

እረ ማነው ብርቱ
ሞትን የደቆሰ
አፈር ያልቀመሰ
እረ ማነው የቱ
በጥበብ እውቀቱ
የቀረለት ሞቱ
የትኛው አጥር ነው የትኛው አጃቢ
ሞት የመጣች እለት የሚላት አትግቢ
በመታጠቅ ቢሆን ከሞት መውጫ ዘዴ
ጎልያድም ታጥቋል ሰይፍና ጎራዴ
የጨበጠው ጋሻ መች ከሞት አስጣለው
ዳዊት በወንጭፉ በጠጠር ሲጥለው

አቤል ታደለ
989 views15:25
Open / Comment
2021-12-25 14:29:35 ወዶ አደር (ቶ)
---------------------------------
ይገርምሻል አንችየ!

አንችን በመጠበቅ
ከአመቴ ቀንሸ ፤
ትመጣለች እያልኩ
ቀናት ጥሎኝ ሸሸ ።

ይገርማል...
አንችን መጠበቁን
ሞት ነው የሚያስጥለኝ
ብየ ስምል፤
ከናፍቆቴ ጋር ሲወዳደር
መሃላየ ይቀላል ።

ይገርማል አንችየ..

አታውቂኝም እኮ
መልኬን አታውቂውም
ቀለሜን አታውቂም
ዘሬንም አታውቂም

ያ ማዶ ነኝ እኔ
እኔ ያንች ጠባቂ
ማነው ከቶ እንዳትይ
ሰው እንዳጠይቂ

እዚህ ማዶም አለሁ
ባካልሽ ላይ ሳለሁ
አንችን በመናፈቅ
አንችን በመጠበቅ
እሞትልሻለሁ ።

ይግረማት መውደዴ..

ሞትን ረትቼ ዳግም ብገኝ
ዛሬም አጠብቃታለሁ
አሷን በመናፈቅ አፈር እሆናለሁ
እሰዋልሻለሁ እጠብቅሻለሁ ።

እይውልሽ አንችየ ለአንች ያጠላውን ጥላቴን ስጠብቅ፤
ሞቱ እያስደሰተኝ በግንባሬ ስወድቅ፤

አካሌ ተሰውቶ ስጋየ ቢመተር
ነፍሴ ወዳ አድራ ነው
........... ስራየ ወቶ አደር ።

Rebih...

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
58 views11:29
Open / Comment