በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Topics from channel:
Meri
Block
Ethiopia
Fiker
Size
Баллон
Join
Share
Shaer
Available
All tags
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 94.12K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
✥--------------------✥
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 178

2021-10-28 22:14:38 ምርጥ የግጥም ቻናል
292 viewsAbela, 19:14
Open / Comment
2021-10-28 21:50:09 የስም ውክልና

ገና ማንነቴን ሳያውቁ በቅጡ
ያም ይህ ነው
ያም ይህ ነው
ብለ ስም አወጡ
እኔነቴ በስሜ ተከልሎ
ስሜ በውሸት ተወክሎ
ዮኒ-ኣታን ተጥሎ
ከርሞ ከርም
ውሎ ውሎ
ሀገር ምድሩን አካሎ
ሲውል ሰነባብቶ
ሲያድር አመሻሽቶ
መላክ ነህ ተብዬ ይኖር ወይ ተዋሽቶ

ዮኒ
ኣታን
If u have any comments

@yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
861 viewsAbela, 18:50
Open / Comment
2021-10-28 20:25:27 ተቀየሚኝ ደሴ

ተተኮሰ ተብዬ ዲሽቃና መትረይስ

ወሬ ሰማሁ ብዬ የጠላትን መድረስ

አንቺን ጥዬ ብሄድ ፈርቼ ለነፍሴ

ይቅር አትበይኝ ተቀየሚኝ ደሴ

19/02/2014 ዓ.ም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.8K viewsAbela, 17:25
Open / Comment
2021-10-28 19:15:13 የማትናደፍ ንብ ከፈለክ ከዝንብ ጋር ተጋባ "
(በዲ/ን ዳንኤል ክብረት)

ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው ። ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ ፡፡ ቆይተህ ደግሞ ንድፊያውን መልመድ ፡፡ ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ ፣ ንብ እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም ፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት ፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ ቢሆን ፤ ጠብ የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው ፡፡

ይህን ያውቃል ገበሬው ፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል ፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል ፡፡ ንብ ትናደፋለች ፤ ግን እንዳትናደፍ ማድረግም ይችላል ፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ ፡፡ ስትቀርብህ ምን ማድረግና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል ፡፡

በሀገራችን ንብ አትገደልም ፡፡ ነውር ነው ፡፡ ብትነድፍም አትገደልም ፡፡ የንቧን ማር ለመውሰድም ንቧን ገድሎ ፣ አጥፍቶ ፣ ጎድቶ ወይም አሰቃይቶ ሳይሆን በጭስ ራሱን እየተከላከለ ፣ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ፣ ወደ ንቧ ቀፎ ገብቶ ነው ማሩን የሚቆርጠው ፡፡ ንቧም ሳትጎዳ ፣ ማሩም ሳይጠፋ ፣ እርሷም ሳትናደፍ ፡፡

ትዳርም እንዲህ ነው ፡፡ አኗኗሩን ነው ማወቅ ፤ የንቧን ንድፊያ የመቀነሻውን መንገድ ነው ማወቅ ፣ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ ፡፡ ደግሞም‘ኮ አስገራሚው ገበሬው የሚከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው ፡፡ የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች ፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች ፣ ከጉንዳንና ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች ፡፡ ግን ትናደፋለች ፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች ፡፡

ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ ፣ አስጠሊታ ፣ ጨጓራ አንዳጅ ፣ ልብ አቃጣይም ክፍል አለው ፡፡ ይናደፋል ፡፡ ግን ደግሞ ክብካቤም ይፈልጋል ፡፡

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.9K viewsBewketu, edited  16:15
Open / Comment
2021-10-28 12:04:01 የፈረቃ ንጋት

የዛሬው ብርሃን በጨለማ ይዋጣል
የነገው ለሊትም በፀሃይ ይቀጣል

ኣእላፍ ንጋቶች
ኣእላፍ ጨለማ
እቺ ከንቱ ምድር
በቅጥ ቀን ተጥማ

አንድ አይኗን ጨፍና
አንድ አይኗን ገለጠች
በዛቢያዋ ስትዞር...
ለአንዱ ብርሃን
ላንዱ ደም ጨለማን ለገሰች

ዮኒ
ኣታን የፈረቃ ንጋት

የዛሬው ብርሃን በጨለማ ይዋጣል
የነገው ለሊትም በፀሃይ ይቀጣል

ኣእላፍ ንጋቶች
ኣእላፍ ጨለማ
እቺ ከንቱ ምድር
በቅጥ ቀን ተጥማ

አንድ አይኗን ጨፍና
አንድ አይኗን ገለጠች
በዛቢያዋ ስትዞር...
ለአንዱ ብርሃን
ላንዱ ደም ጨለማን ለገሰች

ዮኒ
ኣታን
If u have any comments

@yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.7K viewsAbela, 09:04
Open / Comment
2021-10-28 09:30:04 ተፈታልኝ ህልሜ..

ሌሎችን ወራቶች ቀኖችን ጨምሮ
ልኑር በዝምታ ልኑር በእሮሮ
ስፈልግ አላውራ ዝም ይበል አፌ
አይስማ ጆሮዬ ማየት ያቁም አይኔ
እጆቼ እግሮቼ አይንቀሳቀሱ
አንቺ እስካለሽልኝ ትርፍ ናቸው እነሱ
ልንገርሽ እናቴ ስሚኝማ አለሜ
ፈጣሪ ፈቅዶልኝ ከተፈታ ህልሜ
ህልሜም እንዲ ነበር ድሮ ያለምኩት እኔ
በጨቅላ አይምሮዬ ያሰብኩት በወኔ
በጭስ ውስጥ መኖርን
ለኛ ለልጆችሽ መክፈል መስዋትን
ከዚ አረንቋ ኑሮ ወቶ መለወጥን
ይህ ሁሉ አብቅቶ ማየት ወደፊትን
ይህ ነበር ህልሜ ይህ ነበር ምኞቴ
አንቺ እየሳቅሽልኝ ማየት በህይወቴ
ተመስገን አምላኬ ተፈታልኝ ህልሜ
ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.2K viewsAbela, 06:30
Open / Comment
2021-10-28 07:30:05
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.3K viewsAbela, 04:30
Open / Comment
2021-10-27 23:19:47
Derma Roller
ፀጉሮ እየተነቃቀለ እና አየተመለጠ
ተቸግረዋል
0911468394
Hair Regrowth Derma roller ይዘን መተናል
የፀጉር ማሳደግያ ማይክሮ-ኔፕሊንግ ዴርማ ሮለር
በፀጉር ማደግ ላይ ለሙያዊ የቤት አገልግሎት ተብሎ የተሰራ ነው ፡፡ ይህ በእጅ የሚያዝ መሣሪያ በከፍተኛ ደረጃ 540 ከታይታኒየም መርፌዎች የተሰራ ሲሆን ፀጉራችሁን ያድሳል ፡፡
ምንም አይነት የጎንዮሽ ችግር አያመጣም
መርፌዎች እስከ ቆዳው መካከለኛ ሽፋን ድረስ ይዘልቃ የፀጉርን ሀረጎች ያጠናክራል ፣ ስለሆነም አዲስ የፀጉር እድገት እንዲያገኙ እና ቀጫጭን ፀጉሮች ብዛታቸው እንዲጨምር ያደርጋሉ።
የፀጉር መርገፍን ለማከም እና የፀጉርን እድገት ለማነቃቃት በሕክምናው ተረጋግጧል።
የራስ ቆዳ ተጨማሪ ኮላገን እንዲፈጥር ከማበረታታት በተጨማሪ በፀጉር ሥር ውስጥ ያለውን የእድገት ደረጃ ከመደገፍ በተጨማሪ የደም ፍሰትን እና የፀጉር እድገትን ይጨምራል
የአዳዲስ ፀጉርን እድገት ያበረታታሉ ፡፡
ለበለጠ ውጤት በሳምንት አንድ ጊዜ ይጠቀሙ።

ባሉበት ቦታ በፍጥነት እናደርሳለን።
Price -700
Contact - @abela1987
0911468394
407 viewsAbela, 20:19
Open / Comment
2021-10-27 21:18:04 ተነስ
ትዉልድ ነቃ በል ታጠቅ እና ተነስ
ቀዬህ ሳትበትን ሀገርህ ሳትፈርስ
ጠላትን ድል ንሳ አርገህ እንዳይመልስ
መከታ ጋሻ ሁን ወገንህን ጠብቅ
ክንድህን አሳየዉ ክብርህን ለማያቅ
እንደቀደሞ ጀግኖች እለፍ ታሪክ ሠርተህ
በወኔ ተወጋተህ ብታልፍም ህይወትህ
በዘመንህ ጀግና መኖር ማሣያ ነህ

ገጣሚ እርስትአብ /ፍፄ/
@Erstabfiza
ማሥታወሻነቱ
ለ#ጀግናው_መከላኪያ-ሠራዊት
ለ#ጀግናዉ_ለአማራ_ልዬ_ሀይል
ለ#ሚኒሻዉ_እና_ለፍኖ_ ይሁንልኝ,,,

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.7K viewsAbela, edited  18:18
Open / Comment
2021-10-27 19:46:46 የዘንድሮ አህያ ከመሞቷ በፊት የተናዘዘችው ኑዛዜ ነው። ተጋበዙልኝ


የአህያ ኑዛዜ

ዕፅዋት ይቀጠፍ
ዛፍ ከስሩ ይነቀል
የምድር ታሪኳ ከወዲሁ ይጠቅለል
ሀይቅና ወንዙ ከቶ ውሃ ይጣ
ኣእዋፍ አራዊት በርሃብ ይቀጣ
ደረቅ ሆኖ ይክረም የባህር ዳርቻ
እኔ ከሞትኩማ ለምን ሰርዶ ብቻ።

ዮኒ
ኣታን
122 viewsAbela, 16:46
Open / Comment