Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 130.11K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 197

2021-11-08 20:36:56
ሀገሩን በሙሉ ፣ ጨለማ ሲወርሰው
"ገጣሚ ነኝ" ያለ
ለጨረቃ ውበት ፣ ቢቀኝም ሰዋሰው
እኔ የማደንቀው
ክብሪትና ሻማ ፣ የሸጥሽልኝን ሰው!!
(በላይ በቀለ ወያ)
362 viewsAbela, 17:36
Open / Comment
2021-11-08 08:45:13
እናት ብትሞት ፥ ባገር ይለቀሳል
እሕትም ብትሞት ፥ ባገር ይለቀሳል
ወንድምም ቢሞት ፥ ባገር ይለቀሳል
አባትም ቢሞት ፥ ባገር ይለቀሳል
ሃገር የሞተ እንደው ፥ ወዴት ይደረሳል!?

ደሜን አንቆርቁሩት
ስጋዬን ቆራርጡት
ወዜንም ውሰዱ ፥ አጥንቴንም እንኩ
እናት ሃገሬን ግን ፥ በምንም አትንኩ።






እኛ የነቴውድሮስ የነሚኒሊክ ልጆች እያለን ሃገራችን በዘር ዳንኪራ በሚረግጡ፣ በተንኮል እና በእብሪት ባበጡ፣ የእናታቸውን ጡት ነካሽ ዶሸኛ ባንዳዎች አትፈርስም!!

"እትዮጲያ ትቅደም
የጠላት ይውደም!!"

@learntolearnlearningdude

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
415 viewsAbela, edited  05:45
Open / Comment
2021-11-07 23:41:47 ነገ ተፈታኝ ለሆናቹ ለ 12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆንላቹ እንመኛለን ።
@bewketuseyoum19
255 viewsAbela, 20:41
Open / Comment
2021-11-07 22:03:50 @Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.1K viewsBewketu, edited  19:03
Open / Comment
2021-11-07 14:08:10 " ማነኝ???"
:::::::::::::::::::::::።።።።።።።
ዛሬ ስሽቀረቀር አፈር አልይ ባይ
ልራመድ የከጀልኩ ሳላፍር በሰማይ
"ግን እኔ ማን ነኝ? "
የተቸገረውን ድሪቶውን ንቄ
ከመፈጠሪያዬ ከአፈር ርቄ
ተሸክሜ ዛሬ ይህ ድሪቶ ስጋ
የት ነው ብዬ ማላቅ አልፋ"ና" ኦሜጋ
.
.
...
እኔ ሰው ግን ማነኝ?


የመፈጠሪያዬ አፈር አይንካኝ ያልሁ
መቆሚያ ማረፊያ የልቤ እውነት ያጣሁ

እብለጨለጫለሁ
.
.
.
እሽቀረቀራለሁ
.
.
.
ሁሌ እኳኳላለሁ


ግን እኔ ማን ነኝ?

ማልሞት ማልቀየር አፈር የማይበላኝ
አጥንቴ እስኪቀር ምስጦች ማይቦጭቁኝ

ጸጉሬም በአፈር ማይተራመሠው
ምውደው ገላዬ ጉንዳን ማይበጥሠው

እንደ ተረዳሁት እንዳወቅኩት ግን ሰወ

ቢያምር
ባያምር
ቢዋብ
ቢሽቀረቀር
ቢደላው
ቢከፋው

ዞሮ የትም ላይቀር ገላ ለአፈር ነው
።።።።።።

በቶኒ ይፍቱ
614 viewsAbela, 11:08
Open / Comment
2021-11-07 10:32:12 አላስብም መቼስ እጣዬ አደል ማጣት፣
ቢሆንም ይከፋል እድለቢስ ስትል እድሌ የምላት።
ብትገፋኝ ብትንጠኝ ካሳቧ ብወጣ፣
ሽሽት ይይዘኛል መልሼ እንዳልመጣ፣
ለፍቅሯ ብሰዋ እራሴን አርግፌ፣
መንገዴን ብስተው እግሯን ተደግፌ፣
ዛሬ ጎረበጠኝ ህመም እየሆነ፣
የጨበጥኩት ተስፋ ከእጄ እየበነነ፣
የወጣልኝ ፀሀይ በፅልመት ዳመነ፣
ስቃዬ እየበዛ በፍቅር ማለዳ፣
ከአይኖቼ ማድጋ እንባ እየተቀዳ፣
መንፈሷ ካልቀና ልባዋን ካላራሰው፣
ባ'ካሄዴ ልፅና በመንገድ ልካሰው፣
.
.
ምን አልባት ስቃዬ በደስታዋ እንዲሽር፣
በመራቅ አምኜ ተስፋዬን ልሸርሽር

ናታን ኤርሚያስ
@UniqueDy

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
446 viewsAbela, 07:32
Open / Comment
2021-11-07 07:08:06         የሰዉ ልጅ

  የሰዉ ልጅ እኑስ ነዉ
መቼም ማይሞላለት አካለ ጎዶሎ
         በምኞት በተስፋ
ነገን እያለመ እየለፋ ቢያድር እያለፈ ዉሎ
         ቢጨምር መጨመር
ቢጎድል ኣብሮ መጉደል
        ቢገዝፍ ኣብሮ ገዝፎ
ቢቀል ኣብሮ መቅለል
       ባህሪዉ የሆነ
ምቾት እና እንግልት ሁኔታን መላበስ
      በኩነት መመካት
ሲያገኝ መደሰት ስያጣ የማልቀስ
      የሰዉ ልጅ ስንኩፍ ነዉ
ዛሬን ለማያዉቀዉ ነገን እያለመ
      ተማሪዉ ነገን ሲል
እየደጋገመ ቀለም የቀለመ
      ነጋዴዉ ፈጣሪን
ለወረት ልመና ዘዉትር የሚያስጨንቅ
      ከሀብቱ ሊጨምር
ከበርቴዉ ከደሃዉ በጉልበት ሚነጥቅ
     ገበሬዉ ነገን ሲል
ባዶ መሬት ኣርሶ እህል የሚዘራ
      ለነገዉ ነፃነት
ወታደር በሜዳ ጉድጓድ የሚጋራ
       የሰዉ ልጅ እንዲህ ነዉ
አሁንን ለማያዉቅ ነገን የሚያወራ
      መሄዱን እረስቶ
ኋላ መጠለፉን ሁሉም በየተራ

_-_-_-_-_-_- -_-_-_-_-_-_
           #ገብረስላሴ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
402 viewsAbela, 04:08
Open / Comment
2021-11-06 21:41:32 መለኛ አስመሳይ

በጥቁር ሱፍ ደምቆ
በከራቫት ታንቆ
ከናፍርቱን መጦ አንገቱን የሚነቀንቅ
እኔ አለሁ ከሚለው ከዚ ወጣት ይልቅ
በአልኮል ጠንብዞ
በጫት በሲጃራ ጡዞ
መጠጡ እና ጢሱ ፊቱን ያገረጣት
ወገኔ እያለ የሚያለቅሰው ወጣት
ሺህ ያህል ይሻላል
ለማልቀሻ እንኳን አልኮል ይጠቀማል

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.2K viewsAbela, 18:41
Open / Comment
2021-11-06 19:34:51 እቅጩ ያጣው እንቁ


አንጎራጉራለሁ ባልተገራ ድምጼ
እንባ አፈሳለሁ በአመዳም ገጼ
እቀኛለሁ ቅኔ ሰም ወርቁን ላልፈታው
ግጥም እገጥማለሁ መቋጫ የሌለው
አብሠለስላለሁ የማያልቅ ሀሣብ
መብላት እመኛለሁ ያልቀመስኩት ቀለብ

ሀሣብ........

ሀሣብ..........

ሀ..ሣ.....ብ.........

የማይቋጭ ሀሣብ ወሣኔ የሌለው
ማየው እርቀቱ መቼም የማልደርሠው
ለምን እጄ አጠረ?
ለምን ልቤ አዘነ?
ለምን መቋጫ አጣሁ?
ለምን ውጤት ያጣ ትርጉምስ አልባ ሆንሁ?
ሀሳቤ መቋጫ አጣ
ተንጣጥቶ አለቀ ከምጣድ ሳዮጣ
ና ቀን እባክህ ሀሣቤን ድል መንሻ
ሚቀብረኝ ሚጎዳኝ አርቄ ማሸሻ

በመስከረም መሰለህ አበባ ይዘህ ና
ቀባረህ ቅረበኝ ክፉውን ቋጭና

በቶኒ ይፋቱ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.2K viewsAbela, 16:34
Open / Comment
2021-11-06 15:50:06
889 viewsAbela, 12:50
Open / Comment