Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 133.38K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
✥--------------------✥
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 198

2021-11-06 14:44:47 1 ቀን ቢመለስ.....

ቀኑ ይናፍቀኛል
እማይመለስ ነገር አንዴ ሆኖብኛል
1ቀን መመለስ ቢቻል ኑሮ ያኔ
ያን ቀን መልስልኝ እለው ነበር እኔ
እኔና አንተ ሆነን የፎረፍንበትን
ከአስተማሪያችን ጋር የተሯሯጥንበትን
በ15 ዴቃዋ ሻይ የጠጣንበትን
ከጓድኞቻችን የጠፈንበትን
ደሞም እጄን ይዘህ
አንገቴ ስር ገብተህ
የወደፊት ሚስቴ አንቺ ነሽ እያልከኝ
ከጓድኞቼ ፊት ሳሩን ያሰርክልኝ
በቬሎ መጋባት አደለም ብርቃችን
እኛ ተጋብተናል በዩኒፎርማችን
በፊርማ የተጋባን እስኪመስለን ድረስ
ተማሪ አስተማሪ እስኪረገን ርዕስ
እንዋደድ ነበር
እንዲያ ነበር ፍቅር
ተማሪ ቢሆንም ምንም ባይኖረው ብር
ከታክሲው ቀንሶ ይጋብዙኝ ነበር
አትዘልቁም አትልፉ
አትደርሱም ከአፋፉ
ያሉኝን ሰምቼ ትቼህ የሄድኩበትን
ዛሬም ረግመዋለው አንተን የተውኩበትን

ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
133 viewsAbela, 11:44
Open / Comment
2021-11-06 10:52:01
እናት ስትረገም
በምጥ በሲቃ ደም፣


የርግማኗ ፍሬ
ከሷ ተፈጥሬ፣


ሌላ ዘር እሻለው...


ዘውትር መፀፀት
በዛች ባንዲቴ ቅፅበት
እናቴ የሳተች ለት።


ሳል'ፈለግ መጣሁ....


መንገድ ልያዝ ደሞ


ጉዞ በጨለማ
ከሱ እኔ ልስማማ።


እ ና ማ....







ሲጥ!!


ቅዱስ አርዮስ
የግማሽ ዓለም ጣኦት

።።።።።።።።። ።።።።።።።
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
።። ።።
1.4K viewsAbela, 07:52
Open / Comment
2021-11-06 09:44:54 ፅኑ ቃል

ቀኑ ቢተራመስ
በጠራራ ፀሃይ ጨረቃ ብትወርስ

በውድቅት ለሊት ላይ ፀሀይ ብትወጣ
ምሽቱና ቀኑ ሁሉም ቅጡን ቢያጣ
ጊዜው ተገልብጦ ጎልያድ ቢረታ
አልታዘዝ ብሎ ሙሴም ቢያመነታ
መልካም ሚያበጅ ሰው ውርደት ቢከናነብ
አንዱ ላንዱ ተንኮል ቢቀላለብ
ሺህ ዘመን ቢለወጥ
ሺህ ቀኑም ቢቀየጥ
ትላንት ያልኩሽ አለ ዛሬም እንደዚያው ነው
ድሮም እና አሁን ሁሌም 'ወድሻለው


Yoni
Athan @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.5K viewsAbela, 06:44
Open / Comment
2021-11-05 21:52:28 ከማናቀው ቦታ...

እኔም ከማላቀው
አንተም ከማታውቀው
አለ ሆነ ቦታ ልባችን እሚቀው
ዝም ባለበት ሰፈር
ልባችን አውርቶ እሚሄድ በፍቅር
ያ ማላቀው ቦታ
አንተን እማገኝበት ቢሆነኝ አለኝታ
አብዝቼ ወደድኩት
ደሞም አፈቀርኩት
አንተን ያገናኘኝ
ውለታ የዋለልኝ
ባካል እማላቀው
ሁሌ እምናፍቀው
አንተም ከማታውቀው
እኔም ከማላውቀዉ
እየጠበኩህ ነው ..
አደራ እንዳትቀር እጎዳብሀለው

ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.1K viewsAbela, 18:52
Open / Comment
2021-11-05 20:53:20 dating #1

ፀጥ ያለ ቦታ ነዉ
እኔ ዝም ብያለሁ እሱ ግን ያወራል
ከፀጉሬ አንስቶ ጥፍሬን ይታዘባል
ፀጉርሽ በጣም ያምራል ፀጉርሽ ነዉ አይደለ ብሎ ይጠይቃል

ደሞ ይተወዉና
ሽፋሽፋትሽ እስቲ ብሎ ይነካካዋል
ሲገርም እያለ ደሞ ይተወዋል

ያወራ ያወራና
ጉንጮቼን ከንፈሬን ጥርሴን ያሞካሻል
ሲደንቅ እያለ ደሞም ይተወዋል

ዝም ብዬ አየዋለሁ
እሱ ግን ያወራል
ያወራል ያወራል
ያወራ ይለፍፋል

ወረደ....ወረደ.... ከጥፍሬ ደረሰ
እዉነተኛ ነዋ ጥፍሮችሽ ያምራሉ
ሰዉ ያማልላሉ
ያወራል ያወራል
ዝም ብሎ ይለፍፋል

ሊገዛኝ ነዉ መሰል ልቤ አሁን ፈርቷል።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.8K viewsAbela, 17:53
Open / Comment
2021-11-05 15:47:01
1.8K viewsAbela, 12:47
Open / Comment
2021-11-05 14:23:48 #እሰይ



ከመሳሳት ይልቅ ትክክል መሆንን ሰርክ ስለሚመርጥ
ይላል ያገሬ ሰው “ አስር ግዜ ለካ አንድ ግዜ ቁረጥ”።


እኔ ግን እላለው
በመሳሳትክ ውስጥ የሚገኘው እክል
እሱ ነው ቁምነገር እሱ ነው ትክክል።


አሁንም እላለው
ከትናንቱ ዛሬ በስለ እንድትጎመራ
“ አንድ ግዜ ለካ አንድ ግዜ ቁረጥ ” እሰይ ስህተት ስራ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@henockb

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
669 viewsAbela, 11:23
Open / Comment
2021-11-05 12:10:06 (ለማላቅሽ.....)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ያኔ ስትወለጅ የተሰጠሽ ከኔ
ሳይነግሩኝ ያዋሱሽ አጥንት ግራ ጎኔ

የዛኔ ማሟያ እንደወሰድሽብኝ
ዛሬ በኔ ጎድሏል ማሟያዬ ስጪኝ

ግራዬ ተከፋ አጥንቴ አምጣ ብሎ
ከቀኝ እኩል ሊሆን ሊሞላ ጎደሎ

ቀዘቀዘ አልጋዬ አስቦ አንቺን
ታሞ አላርፍ አለ መርቅዞ ጎኔን

ላንቺው አይጠቅምሽም የሰካሺው ገላ
ብታውሺም አይሆን የኔውን ለሌላ

ለኔ ሳይደርሰኝ አይብሉት ምስጦችም
ድርሻዬ ሳላቀው ላፈር አልፈቀድኩም

ጎደሎሽን መሙያ እንደተበደርሺኝ
አደራ ክፉ ነዉ አካሌን አትብዪኝ

ሳትመልሺው ብትሞች እኔም ሳላቅሽ
ለሌላ ሥጪልኝ ላንቺም አይጠቅምሽ

ሳስስ ሳብስ አልኑር ላላገኝሽ አንቺን
ንገሪኝ ከሄድሽም አካሌ ሳትሰጪኝ

በቶኒ ይፋቱ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.5K viewsAbela, 09:10
Open / Comment
2021-11-05 08:42:01 ምነው በዛው ቀረሽ


እመጣለሁ ብለሽ ቆሜ ስጠብቅሽ
እዚ ነኝ ሳትዪኝ ምነው በዛው ቀረሽ
እንገናኝ ስትይ ቃልሽን አመንኩኝ
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፈጥኜ ደረስኩኝ
ከተባባልንበት ከመንገድ ዳር ቆሜ
አላፊ አግዳሚውን ስቆጥር ከርሜ
አንቺን በመፈለግ አይኖቼን ታምሜ
አትቀርም በሚል በተስፋ ታክሜ
ፈልጌ ሳጣሽ ግን ልቤን በጣም ከፋው
ደግሜ ሴት ላላምን ለራሴ ቃል ገባው

ጠብቄሽ ስትቀሪ
የያዝኩት አበባ ቅጠሉ ረገፈ
ስትቀሪ ጊዜ ሰማይ አኮረፈ
አውቃለሁ አምናለሁ
ምክንያት ይኖርሻል
ቢሆንም ቢሆንም
ቃል ማጠፍ ይጎዳል
የአማኝ ልብ ይሰብራል

እንገናኝ ብዬ ዳግም አልጠይቅሽ
አንቺ ካልተመቸሽ እኔ አላስገድድሽ
ግን ግን ለምን ውዴ?
አምኜ ስጠብቅ ምነው በዛው ቀረሽ።
ተጻፈ (በአብዱየእሙዬ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.1K viewsAbela, 05:42
Open / Comment
2021-11-04 20:55:45 ከግጥሞቼ
ትህትና ትዕቢት
==========

ከተፃፈልን በላይ ላንኖር ነገር
አጉል መጨነቅ አጉል ማማረር
ከማንደርሰዉ ጋ ሙግት መያያዝ
እንዴት በማለት ሙከራ እ/ርን ለማዘዝ
እየተጣደፍን ገደል እንዳንገባ
አሜን ነዉ መፍትሔዉ ሳይዙ ሰጣ ገባ
የሚሆነዉን በየዋህነት እየለመኑ
ከሀሳብ በፀሎት እንባ እየበነኑ
ከከንቱ መሻት ከአጉል ብክነት አድነን ብሎ
ልመና ይሻላል ያልክልኝ ይሁን ማለት በቶሎ
እንደቅርብ ወዳጅ ቀርቦ ማዋየት
እንደ አባት አይቶ በፍቅር አንደበት
ለመጠየቅማ ማንስ ከለከለ እንዴታ
ግና በዚች ትንሿ ልብ ትዕቢት ዘሯን ዘርታ
የኋሊት ከመሆን የጭራቆች ምሳ
ትህትናን ይዘን እንኑር እንዳንበሳ

ትዕቢት

ትህትና


በገጣሚ ሰላም ቢሻዉ
ለማንኛዉም አስታየትና ግጥም ለመላክ
@selamnen

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
1.8K viewsAbela, 17:55
Open / Comment