Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Topics from channel:
Meri
Block
Ethiopia
Fiker
Size
Баллон
Join
Share
Shaer
Available
All tags
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 94.83K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
✥--------------------✥
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 2

2023-05-08 18:26:04 #ዝም_ብትል_ምን_ትሆናለህ?

ስታስበው የሚቆጭህን ለመጨረሻ ጊዜ የተናገርከውን መጥፎ ነገር አስታውስ፡፡ ለምን ተናገርከው? ማለት የማያስፈልግህ ለመሆኑ እድል ነበረህ፤ አንተ ግን መናገርህ ብልህ ወይም የተረጋጋ ወይም ከሰው እኩል እንደሚያደርግህ   አሰብክ፡፡

ሮበርት ግሪን እንደጻፈው፣ “ብዙ ባልክ መጠን፣ በበለጠ ሁኔታ የማይረቡ ነገሮችን የመናገር አጋጣሚ ይኖርሃል፡፡” በዚህ አባባል ላይ እኛም፤ የበለጠ በተናገርክ መጠን፣ በበለጠ ሁኔታ ያለፉ መልካም አጋጣሚዎችን ልታበላሽ፣ ምላሽን ችላ ልትልና ራስህ ላይ ስቃይ ልታመጣ ትችላለህ የሚል እንጨምርበታለን፡፡

ልምድ የሌላቸውና በፍርሃት የተሞሉ ሰዎች ራሳቸውን እንደገና ለማረጋገጥ ይናገራሉ፡፡ ሆን ብሎ ከንግግር ልውውጥ ውጪ ለመሆንና ያለ እሱ ተቀባይነት ለመቀጠል የማዳመጥ ችሎታ ብዙም የማይገኝ ነው፡፡ ፀጥታ ጥንካሬና በራስ በቂ የመሆንን መንገድ የምንገነባበት መንገድ ነው፡፡

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.1K viewsAbela, 15:26
Open / Comment
2023-05-08 17:16:20 መልከ ቀና አድርገኝ
ህይወቴ ቢቀለኝ.. .
አውለኝ በክብር
ቀባኝ ሞገስ ቅባት
ቀኖቼ ላይ ልንገስ
በሌሎች ፍርሀት።
ስጠኝ የመሪ ድምፅ
አጥር የሚሻገር...
መንገዴ እንዲሳለጥ
እንዲሆን ገር በገር ።
አልያ አልገፋትም...
ይህችን ስንኩል ዕድሜ
ለአይን አስቀይሜ፥
ቀልዬ ያለ ሞገስ...
ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው
ከሞት ደጅ የሚደርስ !!

(ሚካኤል.አ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.2K viewsAbela, 14:16
Open / Comment
2023-05-08 13:48:52 ( ባይገርምሽ )
እኔ አንቺን ማስብ በሞተ ሰውነት በቆማጣ ሰው ልብ
በጎደለ ይምሮ ፤ በማይታይ ምናብ
እንደምንም × 2
እያለ ጭልምልም ፤ ቀና ብዬ ባይም
መልክሽ አይታይም፡፡
Amu

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.2K viewsAbela, 10:48
Open / Comment
2023-05-08 09:04:39 እየወደዱ መራቅ


ትንቅንቅ ግብ ግብ
ከራስ ጋር መታገል
ከ አፋፍ ላይ መቆም
ከ ዝናብ መጠለል

መውደቅ እየፈለጉ
መበስበስን ሽተው
እግርን ከመራመድ ፍርሀት ሲመክተው
አፋፍ ደለል ሲሆን
ዳመናም ሲበተን
ፍቅር ሲኮሰምን
መውደድም ሲመክን

አይተው እንዳላዩ
አውቀው እንዳላወቁ
ተሰምቶ እንዳልተሰሙ
ራስን ሸሽገው
እውነትን በሀሰት አጣፍተው ገልድመው
አንገት አዘቅዝቀው መንገድ ሲራመዱ
ልብ ያለቅሳል እውነት ለጎረቤት ሆዱ

እየወደዱ መራቅ

ከነብስ ጓደኛ ከልብ ከታሰረ ነጠላ ቁራኛ
ሀሳብ ከገባ በችሎት አልባ ዳኛ
በውድም በግድም ከሆነ ቤተኛ
ከነብስ ትራስ ላይ ከተንተራሰ
ከአንድ ማዕድ ቀርቦ ከእጅ ከጎረሰ
በአንድ ሀዘን ስሜት እኩል ካለቀሰ
በአንድ ደስታ ስሜት እኩልም ከሳቀ
የህይወት መንጠቆ-ን ከስር ከሰበቀ
የኑሮውን ጓዳ ገልጦም ካልደበቀ

ምን ተብሎ ይሸሻል ምን ፈር ተይዞ
እንዴት ይሰጣል ጀርባ ፊትን አጠማዞ
ይሰቃል ይከብዳል አጥንትን ይወጋል
አይን እያለቀሰ ነብስ እዥን ያዣል
መላው ቢጠፋብን ነው እንጂ ቢቸግር
እንዴት ያለ ጉልበት ይራመዳል እግር

በሀሳብ መበለት መከፈል በሁለት
በናፍቆት መናጥ በትዝታ መቅለጥ
እሹሩሩ ማለት ራስን በለሆሳስ
እፍ ብሎ መጥፍት ልክ እንደ ንፋስ
ያሰኘኛል ከርሞ ከምወደው መራቅ

ከአፌ ልቃቂ አንድ ቃል አላወጣው
እወድሻለሁ ያለ ምላሴ እንዴት ሌላ ሊቃጣው
ከማንም አልባው ከከንፈር ላይ መሶብ ቅንጣትን ቀንሼ
ወደ ማንም አልሄድኩ እንኳን በሙሉ እግር ከጉልበቴም አንክሼ
ልላን ሰው አላቀፍኩ በርሀ አቋርጬ እርቀትን ጥሼ

ዛሬ ብዘጋ አንድበቴን
ከፊትሽ ብጋራድ እንዳታይ እኔነቴን
ጠልቼሽ አይደለም መውደዴም ተቀብሮ
አስችሎኝም አይደል ካንቺ መሄድ ዞሮ

ህምምምምምምም

ሁኖብኝ ነው እቴ እየሞሉ ማለቅ
በነገ ፍራቻ ዛሬ ላይ መጨነቅ
በስስት ሙሉ ፍቅር በስጋት መጨመቅ
ስነግርሽ ሀቂቃውን እውነታውን ሀቅ
የሞት ማቅ መልበስ ነው ካንቺ ጎን መራቅ
ቧልትም ነገር አይደል ዝባዝንኬ እንዲያው
ደርሶበት ያየው ነው ነገር የሚነባው



▾▵Řu‌▴▿

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.3K viewsAbela, 06:04
Open / Comment
2023-05-07 16:06:25 ያበደ ምሽት

በእውቀት ስዩም

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.3K viewsAbela, edited  13:06
Open / Comment
2023-05-07 10:39:42 ሞኝ እና..?

አንቺ የዘመን ጓድ መኖር የማይበቃሽ
ሁሉ በተኛበት ብልጥ ሁነሽ የነቃሽ

እኔ የቀን ጥለኛ ፥መኖር የሚበቃኝ
ሁሉ በተኛበት ፥ ሞኝ አርጎ ሚያነቃኝ

አንቺ የደግ እናት ፥መወደድ የቀናሽ
ጡትሽ ባልኖረበት ፥መፈቀር የጠባሽ

እኔም የሰው አባት መወደድ ያልቀናኝ
ጩኸት ብቻ ትርፉ ዝምታ ሚጠማኝ

ሆኖ ግን

በእኔ በአንቺ ገመድ የመቀኘት ፍቅሩ
ፊደል ይለይ እጂ አንድ ነው ሚስጥሩ


ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.7K viewsAbela, 07:39
Open / Comment
2023-05-06 20:36:23 የእግር እሳት

ሰለሞን ለማ

አጫጭር ልቦለድ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
7.4K viewsAbela, edited  17:36
Open / Comment
2023-04-27 13:42:50 ​​ሰው የስርዓት ውጤት ነው፡፡ የሚያስበው በስርዓት ነው፡፡ ማንም ዝም ብሎ አያስብም፤ ዝም ብሎ ያስብ ዘንድ የተፈጠረ የለም፡፡ ሰው ለማሰቡ ሰበብ አለው፤ ለሃሳቡ ምክንያት አለው፡፡ ምክንያቱና ስርዓቱ ያመጣው ነው፡፡ ለማሰቡ መነሻ ሃሳብ ያስፈልገዋል፡፡ ከሰማው፣ ካየው፣ ከዳሰሰው፣ ከቀመሰው፣ ካሸተተው፣ ከነፍሱ ጥሪ፣ ከመንፈሱ ግፊት ተነስቶ ነው የሚያስበው፡፡ በል በል የሚለው ስሜት አለ፡፡ ያስብ ዘንድ የሚገፋፋው ውስጣዊ ግፊት አለ፡፡ እንዲያስብ የሚያደርገው ከአዕምሮው ጋር የተዋሃደ የሚንጠው ሃይል አለ፡፡ የሚከውነው በስርዓት ነው፡፡ ስርዓት ከልባችን ጋር ተጋምዷል፡፡ አፈጣጠራችን ራሱ ስርዓት አለው፡፡ መላው አካላችን በስርዓት ነው የሚሰራው፡፡ የልባችን አመታት፣ የኩላሊታችን አሰራር፣ የአዕምሯችን መዋቅር፣ የዲኤንኤያችን ድርድሮሽ፣ መላ አካላችን በስርዓት ነው የታነፀው፡፡ ሰው ከስርዓት ውጪ መሆን አይችልም፡፡ ሰማይና ምድሩ፣ ፀሐይና ጨረቃው፣ ባህርና የብሱ፣ ነፋሳቱና ዝናቡ፣ ወጀቡና ሞገዱ፣ የዓየር ንብረቱ ሁሉ በስርዓት ነው ስራውን የሚሰራው፡፡

ፍቅር ስርዓት አለው፡፡ ጠብም ስርዓት አለው፡፡ ሰው በሚያጋጨው ነው ከሌላ ሰው ጋር የሚጣላው፡፡ ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ ካልበደለው ሰው ጋር የሚጣላ ሰው ስርዓት የሌለው ነው፡፡ ሰው ፍቅር ይዞኛል ብሎ በየሜዳው ፍቅሩን አይገልጽም፡፡ ቦታና ጊዜ ይመርጣል፡፡ ሰው ያለቦታውና ያለጊዜው ያለስርዓት ምንም ነገር ሲያደርግ አያምርበትም፡፡ አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ የሚለቀልቀው እኮ አሳሳም ስርዓት ስላለው ነው፡፡ ትዳር ስርዓት አለው፣ አበላል ስርዓት አለው፣ አነጋገር ስርዓት አለው፣ አለባበስ ስርዓት አለው፣ አኗኗር ስርዓት አለው፡፡ ስርዓት የሌለው ምንም ነገር አይገኝም፡፡ አሟሟትም ቢሆን ሰርዓት አለው፡፡ ሰው በየሜዳው እየተገደለ፣ በየጢሻው እየሞተ በቡልዶዘር በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ሬሳው ተሰብስቦ ሲቀበር ማየት ልብን የሚያደማውና ቅስም የሚሰብረው አሟሟትም ስርዓት ስላለው ነው፡፡ አዎ ሰው በህግና ስርዓት ካልተመራ አውሬ ነው የሚሆነው፡፡

ሰው ተፈጥሯዊ ስርዓቱን መለወጥ ባይችልም ዓለማዊውን ስርዓት ያሻሽላል፡፡ ጎጂ የሆነውን በጠቃሚ ስርዓት መተካት አዕምሮ ላለው ሕዝብ ዋና ተግባር ነው፡፡ አድሏዊና ዘረኛ የሆነውን የመንግስትን ስርዓት ሁሉን አካታችና በእኩልነት ወደሚያገለግል ፍትሐዊ ስርዓት መቀየር ከሰለጠነ ማህበረሰብ የሚጠበቅ ነው፡፡ ያለመልካም ስርዓት መኖር አይቻልም፡፡ ስርዓት ከሌለ ሰላም የለም፤ ብዙ ነገሮች ይመሰቃቀላሉ፣ ጉልበተኞች ይፋንናሉ፣ ባለመሳሪያዎች ሁሉን ለእኔ ይላሉ፡፡

ከተፈጥሯዊው ስርዓት መቃረን ከራስ መጣላት ነው፡፡ ዓለሙ የጫነብሽን ያረጀ አስተሳሰብ አስወግደሽ በአዲስ ሃሳብ ትተኪያለሽ ማለት በዘመናዊነት ስም ከስርዓት ነጻ ትሆኚያለሽ ማለት አይደለም፡፡ ሳይንስ የሚለፋው ስርዓት ለማፍረስ ሳይሆን ጥቃቅን ችግሮቻችንን ለመፍታትና ያልተደረሰባቸውን የሰው ልጅና የተፈጥሮን ስርዓት ለመረዳት ነው፡፡ የተፈጥሮ ስርዓቱን ልጣስ ቢል ግን አይችልም፡፡ ከስርዓቱ አፈነግጣለሁ ብትዪ ከተፈጥሮሽ ነው የምትጋጪው፡፡ አንቺነትሽን በስርዓት ካልመራሽ፣ አኗኗርሽ ስርዓት ከሌለው፣ ሴትነትሽን በስርዓት ካልያዝሺው ገላሽም ይረክሳል፣ ሰውነትሽም ይቆሽሻል፡፡ በኮስሞቲክ ብቻ ሳይሆን በስርዓትም ራስን መጠበቅ ታላቅ ብልህነት ነው!

ዘመናዊነት ሥርዓትን ማሻሻል እንጂ ከሥርዓት ነፃ መሆን አይደለም!

#ሞጋቿነኝ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
351 viewsBewketu, 10:42
Open / Comment
2023-04-27 09:01:26


           WORK VISA CANADA 2023
---—--------------------------------        
            አስደሳች ዜና ለመላው ኢትዮጲያውያን

ከ 5000- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት እና በልምድ

Number of Positions: 5000+ positions 0 EXP and with Exp

በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች የወጣ የስራ ማስታወቂያ

የኮንትራት ሰራ ወደ ካናዳ
የስራ ማስታወቂያ በ 0 ዓመትና በልምድ
የስራው አይነት ኮንትራት
ብዛት 5000+
ደሞዝ: በስምምነት $ በዶላር
አየር ትኬት በነፃ
ቪዛ በነፃ

ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ

Apply Now
                                 
https://addiszemenvacancy.com/2023/03/18/canada-jobs-2023/


----------Follow Our Website---------
                           
         https://addiszemenvacancy.com

----------Join Our Telegram----------
                              
     https://t.me/Addis_Zemen_Vacancy
1.4K viewsAbela, 06:01
Open / Comment
2023-04-27 07:30:24
በስመአብ ወወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን መርጌታ ላቀው
የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
እነሆ የባህል መድሀኒት ከአባቶቻችን
0912956067
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
               እንዲሁም የተለያዩ
      መድኀኒቶችን እንቀምማለን
እነዚህን እና ሌሎች አገልግሎቶችን እንሰጣለን
     መድሀኒቱን ባሉበት ቦታ ሰርተን  መላክ እንችላለን
ይደውሉ
ለጥያቄወ 0912956067 ይደውሉልን 
የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል https://t.me/+wlW6dTssQ_lkODY0
https://t.me/+wlW6dTssQ_lkODY0
1.6K viewsAbela, 04:30
Open / Comment