Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 130.11K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 3

2023-07-05 09:35:29 እኩል ነው የሸጥነው
'
'
በመምጫሽ ጊዜ ድግሱም አሰልች፣
አብሮ አደግ እንቦሳ ተሰረገ ለአንች
'
'
ስሰክር በንዴት

አስቤማ ነበር፥ ጠላ በጆክ ይዘን ፣
አስቤማ ነበር ፥ ቋንጣ ስጋ ሰርቀን ፣
አስቤማ ነበር ፥ከሜዳው ጨለማ በጨዉ ለዋውሰን፣
አስቤማ ነበር ፥በሃሳብ ጎራርሰን ፣
ያራቀን ገደሉ ለሜዳ እንዲያደርሰን፣

'
'
አስታውሽ እቴዋ ልንበላው ያሰብኩት በሬ
እኩል አብሮ አድጓል ሳልከዳው ለዛሬ

ያኔ እምቦሳ ነበር ካንቺ ጋር ስተሻሽ
እኩል ቦርቀናል እረኛ ቤት ሲዋሽ
'
'
በገዛ ሰርግሽ ላይ ሰርግሽን ሳጠና ፣
የኔ ያልኩት በሬ፥ ለገንዘብ ሸጥኩት ባላባት ያዝሽና ፣

ይሁን አልኩ'

ባል'ሽ አንቺን ገዛሽ ፥እኔንም በሬዬን፣
እስከሸጡ ድረስ፥ ሁሉም ያስገምታል ብበላ ቋንጣዬን ፣
ለሰርግ አለመቅረት
ሁለት ብሰርግ ነው የሸጥኩት ዕንባየን፣

እያልኩ እያየውሽ፥ ደብቄ አልሰድር፣
ታዲያ እኔ አልወቅስሽ
እኩል ነው የሸጥነው በሬን እና ፍቅር፣
'
'

ግዕዝ ሙላት

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
868 viewsAbela, 06:35
Open / Comment
2023-07-04 21:18:34 ... ሰነፍ-አክራሞት..
------ ------
ከአመድ አፋሽ መዳፍ
በሙት ጥፍር ህያው አፈር ተሰግስጎ
ከወንድ ገፅ ስባሪ አይን እንባ ምጎ
መንፈስ ቅዱስ በራቀው ቃል
......................መረዳትን በተከዳ
በተከርቸም ልሳን ደም በላሰ የፊት ቆዳ
እየገበሩ የሚከፍሉት
ያልተረዱት የራስ እስር
ያልተረዱት የራስ ፍዳ
መክረም ትግል መኖር እዳ!።

#በልጅ ብዕር Nebiyat Mulat

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.8K viewsAbela, 18:18
Open / Comment
2023-07-04 10:27:48 (አይዞን ጨረቃዬ,,,,,)
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ጥበብ ፈልቃ ፈልቃ 
ፀሐይ ደምቃ ደምቃ
ከጨረሰች ወዲህ ቦታዋንም ለቃ
ለ ...ጨ   ረ    ቃ

ምስኪኗ ጨረቃ በኮከቦች ደምቃ ጨለማን አብርታ
ትክ ብዬ ሳያት የኔን ይመስለኛል ህይወቴን ሕይወቷ

የኔ ምስኪን አንቺ
ያንቺ ምስኪን እኔ
ነይ እንተዛዘን ነዪ ጨረቃዬ
አልቃሽ አንፈልግም,,,, እኛው እንበቃለን
ሲመጡ አመስግነን ሲሔዱ እንሸኛለን

አይዞሽ ጨረቃዬ
እኔም ያንቺ አይነቷ አዛኟ ለራሴ
ሲመጡ መቀበል
ሲሔዱ መሸኘት
ለምጄ በነፍሴ
ያለቅጥ ምተክዝ ያለ አዛኝ ምባዝን
ያንቺ አይነቷ ምስኪን አለሁኝ በምድር

አይዞሽ ጨረቃዬ አይዞን,,,,

#Lidiya_y

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.6K viewsAbela, 07:27
Open / Comment
2023-07-03 19:38:29 ወይ ጥጋብ!

ተርባለች ብለው ሲያዝኑልሽ አይቼ
በአገልግሌ ሙሉ
አልጫና ቀዩን አንድ ላይ ፈትፍቼ
በቅመም በእንቁላል በደንብ አጣፍጬ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
እህል እስክትቀምሽ
አፌን አልሽር ብየ እኔም ተራብኩልሽ!

ታርዛለች ብለው ሲከፉ አየሁና
በሻንጣየ ሙሉ
አልባሳት ሞላሁት ቢሸፍን ገመና
ይሄን ኮተት ሁሉ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
ልብስ እስክደርቢ
ብርድ አልፈራ ብየ እኔም ታረዝኩልሽ!

ተጠምታለች ብለው ሲያሙልኝ ሰምቼ
በዕቃየ በሙሉ
በባልዲ በሀይላንድ በስኒ ሞልቼ
በመልክተኛየ
ከፍቅር ፖስታ ጋር አብሬ ላኩልሽ
አንጀትሽ እስኪርስ
ውሀ አልቀምስም ብየ እኔም ጥም ሞትኩልሽ!

አሁን በተራየ
በአካላቴ ሁሉ
በአይን በጆሮየ በነፍሴ እንደያዝኩት
ልቤን ረጋ በል እስክንደርስ እያልኩት
መልክተኛ አስትተሽ ራሴን አስላክሽኝ
መልስሽ ግን ይገርማል
ፍቅር እንኪ ብልሽ 'ጠግቤአለሁ' አልሽኝ

ወይ ጥጋብ!

የተራበ እህል
የተጠማ ውሀ
የበረደው ልብሱን እየደራረበ
ማባበል ተስኖት
ማስታገሻ ላጣው ይብላኝ ለጠገበ!


             በአቤኒ የተጻፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.1K viewsAbela, 16:38
Open / Comment
2023-07-03 14:21:21 ያልተፃፈ ፅሁፍ ለንባብ ስጋብዝ
"ንፉግ......................ግብዝ"
ያልተቋጨ ሀሳብ ያልተሞነጨረ
ገና ከጅምሩ ተቀጭቶ የቀረ
    ሳሰፍር ሰሌኑ ላይ
          "ድንጋይ"
አውጡት አውጡት ብለው ወጥቼ ከመድረክ
ብሶቴን ሳካፍል "እሰይ ደግ አደረክ"
የህዝቡ ጫጫታ ሲቀልጥ የእጅ ጥፊ
ሳቀርበው ስቃዬን
              "ውረድ....ቀጣፊ ለፍላፊ"
ተሰምቶኝ ስስ ከንፈር እንባዬን ባራግፍ
            "የእጅህ ግፍ"
ባይበሉባ መዳፍ ጉንጬን ብዳብሰው
       "አስመሳይ ንፉግ ሰው"




ለዚ ብኩን ትውልድ ላልገባው ዝምታ
ገና ከጅምሩ ኑረው በሁካታ
ዶማን ዶማ ብለን ካላስረዳናቸው
      ጉዳቸው።
ሲቀላጠፍ ምሬት ከባዶ ገፄ ስር
አይቶ ካልተረዳው የለንም ትስስር
ሰሌን ላይ ያረፈው የቀለም ድብልቅልቅ
          ማየት ካልተቻለ
ቀለም ተከለለ።

ትርጉምን ለማይሰጥ ለበዛ ሆይሆይታ
የሁላችን መዳፍ በጥፊ ተመታ
ዝም ላለ አንደበት መፃፍ ለተሳነው
ወርደን አሳነስነው።

ያልተፃፈ ፅሁፍ ለንባብ ስጋብዝ
"ንፉግ......................ግብዝ"
ያልተቋጨ ሀሳብ ያልተሞነጨረ
ገና ከጅምሩ ተቀጭቶ የቀረ
    ሳሰፍር ሰሌኑ ላይ
          "ድንጋይ"

ደረጃችን ጎልቶ ኖርንና በርቀት
ለንባብ እንዲሆን
ብናስተላልፈው አንዲቷን ወረቀት
ላልተገነዘበን ላልተረዳን ከንቱ
    አይበቃም እውቀቱ
ሞንጭረን ላክንለት ከነወረቀቱ

ዮኒ
    ኣታን  @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.7K viewsAbela, 11:21
Open / Comment
2023-07-03 08:42:47 ከኦሪት ዘፍጥረት እስከኛ መለያየት

ቀራንዮ ነሽ! አለኝ በቃሉ ሰቀለኝ
አንቺ የሁሉ ምክንያት ጎልጎታዬ
አይን አይኔን እያዬ
አንቺ ለኔ ሄዋኔ
ትእዛዝ የጣስኩልሽ ቃልን የሻርኩልሽ
ሎሌሽ ሆኜ የታዘዝኩሽ
ፈጥሮኝ ፈጥሮሽ ከሱ በላይ የምሰማሽ
ሰርክ ለኔ የምጠራሽ።
እሱ፤
ላቤን ጠብ እንዳደርግ
ለፍቼ እንድበላ ጨክኖ የፈረደው
ጣር ስቃይ ለግሶሽ
ምጥሽን ያበዛው እንደምን ቢነደው?
ዳሩ፤
ለምን አይብሰለሰል እንደምን አይነደው?
የሞት ሞትን ትሞታለህ
የሚል ማስጠንቀቂያን
እንካ በሚል ቃልሽ
ብላ በሚል ቃልሽ አለቅጥ ስንደው
እንደምን አይነደው
እሱ፤
ብቻዬን እሆን ዘንድ ፍፁም ያልወደደው።
አንቺ ፍጡር አንቺነትሽ በኔ ነሁላላነት
ብቻ አለመሆንን በማመን ሲንደው
ይህን ይሆን እንዴ
መፋቀር እያለ ሰው የሚነጉደው ?።
መልሺልኝ! አለኝ
አይ! አይመስለኝም አልኩት
ምን ነካኝ በሞቴ የቱን ያህል ከፋኝ
ለምን ተቃወምኩት?
ፊቱን ከሰከሰ
ድጋሚ ሰቀለኝ ድጋሚ በደልኩት።
በስንብት አይነት በጥልቀት አየሁት።

#በልጅ ብዕር Nebiyat Mulat

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.5K viewsAbela, 05:42
Open / Comment
2023-07-02 21:57:12 #የፍቅር_ጊዜ

ብዙዎች ይላሉ...
ሳያት ነው የወደድኳት
በልቤ የሳልኳት
እሷ ልጅ የኔ ናት።

የእኔው ግን...
ሳላያት፥ በመስማት ወደድኳት
ለእምዬ ማርያም፥ አታሳጪኝ አልኳት
ቦታዋን ሰጠዃ።
...
ግን ምን ሊያደርግ...
ምኗንም ሳላስቀር፥ ብወድላት እንኳ
በሯን ዘጋችብኝ፥ ልቤ ልቧን ሲያንኳኳ!

Meku Mura

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.9K viewsAbela, 18:57
Open / Comment
2023-07-02 20:27:08 ናፍቆት ይሉትን ወግ
ነፍስ እየሸመኑ ስጋ ካለበሱት
ሸማኔዋን አንቺን
ነጠላውን እኔን ነበር ሚያስመስሉት

ባገሩ ሰው ሞልቶ የሚወርድ 'ሚወጣ
አልታይህ አለኝ
አንቺ ሸፍነሽው የመውደዴን እጣ

ትዝታ ብቻውን ናፍቆት ላያስወጣ ህመም ላያክመኝ
እየመላለሰ አንቺን አንቺን ብሎ ልቤን አደከመኝ

ትዝታ ውበቱ
የናፈቅሽኝ ለታ ትናንትን ማየቱ
ትዝታ ክፋቱ
የናፈቅሽኝ ለታ አሁንን መሳቱ


         በአቤኒ የተጻፈ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.9K viewsAbela, 17:27
Open / Comment
2023-07-02 10:56:17 የመፅሐፍት ሊንኮቹን ይንኩ File ያገኛሉ።

ሌዮኔ
የሸገር ወጎች
ደቂቀ እስጢፋኖስ
የብርሃን እናት
መፅሐፈ ሚርዳድ
የልቤ ወዳጅ የሰዉ ዘር ልጅ
የደም ዕንባ  Red Tears
መንትዮቹ
ስውሯ ገዳይ | And Then There Were None
ቦርጨቅ
ምዕራባዊት
የፍቅርና የፍልስፍና አባባሎች
የድሀ ጠበቃ The Street Lawyer
ኤቶዮጵ
ቶማስ ሳንካራ ጥቁር አብዮተኛ
6.5K viewsAbela, 07:56
Open / Comment
2023-07-02 09:55:18 ትናንት እና ዛሬ
.......
ሰው መውደድ ሰው መጥላት
ሰው ማመን ሰው መርሳት
እንደኑሮ ቅመም እንደኑሮ ውጋት
እንደጥልቅ ሳቆች እንደትንሽ ተስፋ
ሁሉም በየተራ እየበራ ጠፋ
ትዝታ ብቻውን እንደዋርካ ሰፋ።
#በልጅ ብዕር Nebiyat Mulat

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.1K viewsAbela, 06:55
Open / Comment