Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 133.38K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
✥--------------------✥
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 7

2023-06-05 20:54:08 ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 6


••••••••••• ምን ይመስልሀል?"
"በምን አይነት መልኩ ነው ይምናደርሰው?"
"ቀላል ነው በሆነ ነገር መምታት ወይንም የሆነ ነገር ላይ እንድትወድቅ በማድረግ"
"አይሆንም በፍፁም እሷ ህይወት ላይ አደጋ የሚያመጣ ምንም አይነት ነገር ማድረግ አልፈልግም"
" አለበለዚያ ያንተ ህይወት አደጋ ላይ ይወድቃል"
"አታስጨንቀኝ ያሬድ ያንን ማድረግ አልችልም"
"እሺ !"
"አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ"
"መልካም አስብበት ናሆም በደምብ አስብበት"
"እሺ" ብሎ አሰናበተው ብዙም ሳይቆይ ከ ቤቲ ጋር መግባባት የሚችልበት ትልቅ ሀሳብ መቶለት ሳይታወቀው "የስስስስስስ....." አለ
ሀሳቡም ይህ ነበር ቤቲ ከሱ ድርጅት ጋር ተመሳሳይ ስራ ያለው ድርጅት ስላላት በጋራ ለመስራት የ ስምምነት ውል ማስፈረም ነበር። ከዚያ ምናልባት ቤቲን በተለያዩ ምክንያቶች ማግኘት ለሱ ቀላል ይሆናል ....
°°°
ቤቲ ሁሉንም የሚወራውን ነገር እየሰማች ነበር ምክንያቱም ጠዋት የለበሰውን ልብስ እስካሁን አልቀየረም ወዲያው ስልኳ ጠራ ናሆም ነበር ።
"ሄሎ "
"ሄሎ ቤቲ "
"አቤት"
"ለ አንድ ጉዳይ በጣም ፈልጌሽ ነበር ቢሮ ልምጣ?"
"አይ ስራ አልገባሁም"
"ተገናኝተን ማውራት እንችላለን?"
"አይ አይመቸኝም "
"ግዴለም አንዴ ብቻ"
"ጥሩ በስልክ ንገረኝ"
" እሺ እየውልሽ አንዱ ድርጅቴ ካንቺ ድርጅት ጋር ተመሳሳይ ስራ ነው ያለው እና እዛ ያንን በጋራ ስምምነት እንድንሰራ ፈልጌ ነበር እንደ ሀሳብ ነው"
"አስቤበት መልስልሀለሁ "
"እሺ የኔ ቆንጆ እና ስራ ካልገባሽ ሻይ ቡና ብንልስ?"
" ደስ ይለኛል"
"እሺ ምሳ ሰአት ላይ ቤት እመጣለሁ"
"እሺ እጠብቃለሁ"
"እሺ ቻው "
"ቻው"
ስልኩን ዘግታ ወደቤት መሄድ ጀመረች የዱርዬ አለባበሷን ለብሳ ጠበቀችው ምሳ ሰአት ላይ መጥቶ ወሰዳት እና ምሳ በሉ 8 ሰአት ተኩል አልፏል "ከዚህ ቦሀላ የት ነው የምታሳልፈው? "
"ያው ቤት "
" አንድ ቦታ ልውሰድህ?"
"በጣም ደሲለኛል" በደስታ ፊቷን እያየ
"ስለዚህ እንሂድ " ብላው መኪናውን ከፍታ ገባች እሱም ገብቶ ወደምትመራው አቅጣጫ እያሽከረከረ ከ አዲስ አበባ ወጡ •••••••

••••••••••• ከ አዲስ አበባ ወጡ እና አንድ ሜዳ ላይ አስቆመችው ናሆም ሁኔታውን ፈርቶታል ሽጉጡን ዳበሰው ወደ አንድ ጫካ እየወሰደችው ነበር ጫካው አረንጓዴ ሆኖ አጠር ያለ ነው ጥቂት ተራምደው ከ ጫካው ሲወጡ አንድ ገደል ጫፍ ላይ ደረሱ እና ቤቲ ቀድማው ሄዳ አንዱ ድንጋይ ላይ ተቀመጠች እየተሰማው የነበረው መጠራጠር ለራሱም ገረመው 'ቤቲ እኮ እኔ እንዳስገደልኩት አታውቅም ምንድነው የሚያስፈራኝ ብሎ ሽጉጡን በደምብ ወደውስጥ ገፋ አድርጎ ሄዶ ከጎኗ ተቀመጠ ስፍራው ከሚባለው በላይ ውብ ነበር በህይወቱ አይቶት አያውቅም አለ ብሎም አያስብም ያውም እንደዚህ ቅርብ ቦታ ከፊት ለፊታቸው ያለችው ፀሀይ የ ልግባ አልግባ ትግሏን ተያይዛው ደም መስላለች ከፊት ለፊታቸው ትልቅ የ አለት ተራራ ከቧቸዋል ፊትለፊት ወደታች የሚፈሰው ነጭ ፏፏቴ ልቦናን ይሰርቃል ለጊዜው ሁለቱም በ ቦታው ውበት ተማርከው ዝም አሉ ጥቂት ቆይቶ ግን ናሆም ዝምታቸውን ሰብሮ ገባ
"እዚህ ቦታ ብዙ ጊዜ ትመጫለሽ?"
"አዎ በጣም ብዙ ጊዜ"
"መቼ መቼ"
"ብቸኝነት ሲሰማኝ"
"እና ዛሬ...?"
"አይ ዛሬ እንኳን ላሳይህ ነው"
"በጣም ደስ ብሎኛል በጣም ያምራል ! ደምበኛ እሆናለሁ" ከ ለስላሳ ፈገግታ ጋር
"አዎ በጣም ቆንጆ ቦታ ነው"
"ልክ እንዳንቺ "
"ኧረ ከሰው ውበት ጋር ይወዳደራል ብዬ አላስብም"
"እውነት ነው"
"እና እኔ ሰው አይደለሁ እንዴ?"
"አደለሽም"
"እና ምንድነኝ ?"
" መልአክ "
"እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ ?"
"በቃ ውበትሽ ተፈጥሮሽ ፀባይሽ"
"ተፈጥሮና ፀባዬን በምን አወክ?"
"ወፏ ነግራኝ"
"ወፌ ሁልጊዜ ልክ ናት ብለህ ታምናለህ?"
"አዎ ምነው ልክ አይደለችም እንዴ?"
"ሰሙን ናት ወርቁን ነው እንጂ "
"ስለዚህ መልአክ ነሽ ያልኩት ልክ ነኝ"
"ከከፍታዬ ወድቄ ሰይጣን ሳልሆን በፊት" ድምፅዋን ቀንሳ
" እ?"
"እ?"
"ምን አልሺኝ?"
"አይ መልአክም አይደለሁም ሰው ነኝ ነው ያልኩህ"
"ይሁንልሽ እሺ........... እና ስለ ቤቲ ንገሪኝ እስቲ?"
"ስለ ቤቲ ምን?"
"ለምንድነው የምታጨሽው?"
"በቃ ለጊዜውም ቢሆን ለህመሜ ማደንዘዣ ስለሚመስለኝ"
"ምንድነው ህመምሽ?"
"ወንድሜ!" ድንገት ተፈጥሮ ላይ ፈዞ የነበረ ፊቱን ወደሷ እያዞረ
"ወንድምሽ ምን? .... ማ...ማለቴ ወንድም እንዴት ህመም ይሆናል?"
" እንደዚህ!"
"አልገባኝም?"
"ፊሊጶስ ይባላል••••••••••••••



.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
2.4K viewsAbela, 17:54
Open / Comment
2023-06-05 13:54:06 (ማሪኝ ..)
=========

ደብዛዛ ናት ብዬ
ያማኋት በሸንጎ ከጸሐይ ስፋቀር
ያቺ ጨረቃዬ
ለካ የጨለመችው መቆሸሼን አይታ
ልትሸሽገኝ ነበር

(ማሪኝ ጨረቃዬ )
#Da_kiyorna

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.9K viewsAbela, 10:54
Open / Comment
2023-06-05 09:31:04 #ማራናታ
( ጌታ ሆይ ቶሎ ና )
Repost
.
.
ነፍሴን ሳላሽራት ከሀጥያት ዕድፍ፣
በስምህ ሳልዳኘው የስጋዬን ጉድፍ።
እንደ ጷግሜ ዝናብ፤
እንደ ውሃ ደራሽ አልፎ የቀን ስንኩል፣
ስናፍቀው የነበር ከተስፋ ቃል እኩል።
ደርሶ ሳያበቃኝ ለሀገሬን ትንሳኤ፣
ሳልወጣ አደባባይ ሳልከርመው ሱባኤ።
ጌታ ሆይ አትምጣ !!
ጌታ ሆይ አትምጣ ትንሽ ጊዜ ሰጠኝ፣
ነፍሴም ልተጣጠብ ፍቅርህ ይለውጠኝ።
እባክህ ጌታ ሆይ.......
እኔ ስልጡን ባርያ እኔ ብኩን ልጅህ፣
አፈር ትቢያ አካሌን አቁሜው ከደጅህ።
በተማፅኖ እንባ በኩርማን በዓቴ፣
እስክትምረኝ ድረስ ይህ ነበር ፀሎቴ።
"እባክህ አትምጣ!!!"
.
.
አሁን ግን አምላኬ ፤
አሁን ግን ጌታ ሆይ አልልህም ማረኝ፣
መሰንበቴም ይፍረስ አልልም አኑረኝ።
በተቀጠቀጠ በቆጠለ አካል፣
በተነባበረ በሰው በድን መሃል፣
እንዴት ነው መፀለይ?፤
እንዴት ነው መማፀን ?!
እንደምን እንደምን እንዴት ልለማመን።?
አምባ ነፍስያችን ቤተ እምነት ነደዱ፣
አፀደ እግዜር ማሳ ተርታ ሆኗል መስጂዱ።
እንዴት ነው መፀለይ ፤?
መሻገሪያው ድልድይ፤
ሙሴ ያልነው መሪ መንገድ ላይ ትቶናል፣
ማን ቀብቶት እንጃ ወርዶ አዋርዶናል።
ሚስኪን ሀገሬ እንኳን፤
ከአለም ተነጥላ ላመነችው ጌታ፣
"ኤሎሄ"
"ኤሎሄ"
"ኤሎሄ" እንዳለች እጆቿን ዘርግታ።
ለልጆቿ ታምና ታፍራ እንዳልተመካች፣
በአብራኳ ክፋይ በጥፊ ተመታች።
( የሚያሳዝን እውነት )
.
.
እንደምን ልማፀን ?፤
እንዴት ልለማመን።?
የስጋ ፍላጎት ሰው ከመሆን ነግሷል፣
በልባችን መንበር ሰይጣን ቤት ቀልሷል።
መፀለይ ምንድነው፤
መንበርከክ ምንድነው።?
በገረረ ብረት በጦር በጎራዴ፣
በሳንጃ በጩቤ በሻገተ ጓንዴ።
የፈጠርከውን "ሰው" እንደ በግ አርደናል፣
እንደ እንጨት ረብርበን ፍጡር አንድደናል።
.
.
እናም ጌታችን ሆይ.....
እየደጋገምን ዝንት ብንበድልም፤
እፁብ ቤተ መቅደስ እልፍ ሰው ብንገድልም፤
ባለ ብዙ ምህረት ቸር አምላክ ነህና፣
አገኛለሁ ብለህ ቀናዒ ልቦና።
በእዝነት አስበህ ልትምረን ከመጣህ ፣
አትጠራጠረኝ፤
ድጋሚ መገረፍ መሰቀል ነው እጣህ።
ስለዚህ ጌታ ሆይ.....
እኛ ብኩን ህዝቦች፣
እኛ ብስቁል ህዝቦች፤
በ'ለት ኑረት መሃል በስጋ ህላዌ፣
ክፋት ምቀኝነት የከረመ ደዌ።
ጠፍሮ ተብትቦ እንዳወላገደን፣
'ባክህ ቶሎ ናና ጠራርገህ ውሰደን።
.
.
.
"በል ፀሎቴን ስማኝ፤
አንተ ታላቅ ንጉስ አንተ ታላቅ ጌታ፣
"እግዚኦ.. ዘላለም እግዚኦ.. ማራናታ።"
.
.
.
......የወንድምህ ህመም አንተን የማይሰማህ ከሆነ "ሰው" መሆንህን ተጠራጠር....

       ዓቢይ ( @abiye12 )

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.4K viewsAbela, 06:31
Open / Comment
2023-06-04 20:30:43 ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 5

•••••••••••• ዝም አለ ።
"ምነው? አለው ቶማስ ሁኔታውን በሚመረምር አስተያየት
"ይቅርታ ቶም ይሄንን ማድረግ አንችልም እንዳጋጣሚ ልጅቷን አውቃታለሁ እና ይህንን አሁን ማድረግ አልችልም" ብሎ ትቶት ወጣ ቶም ባየው ነገር በጣም ተደናግጧል ያ ሀይለኛ ቁጡ ኮስታራ እና ጠንካራው አለቃው ዛሬ እንደዚህ ሲዳከም ማየት ለሱ ከመቼውም በላይ ያልተለመደ ነበር
°°°
ቤቲ ፎቶውን ያሰራችው እነ ናሆም የተገናኙበት ሆቴል ነው ምክንያቱም ጠዋት ናሆምን ስታቅፈው የ ድምፅ መቅጃ አብራ ኮቱ ኮሌታ የውስጠኛ ክፍል ላይ ለጥፋበት ነበር በዛ ምክንያት ሁሉንም የሚያወሩትን እየሰማች ነበር የ ቶማስን ማንነት ለማረጋገጥም በ ካፌው በር ጋር አልፋ ነበር እናም በደምብ አይታዋለች ......

ናሆም ቀጥታ ወደቤቱ ከሄደ ቦሀላ መኝታ ክፍሉ ገብቶ ስለተፈጠረው ሁሉ ማሰብ ጀመረ ውስጡ ምስቅልቅል ያለ ስሜት እየተሰማው ነው ምን ማድረግ እንዳለበት አያውቅም ወዲያው አንድ ሀሳብ መጣለት እንደ ፈጣሪ የሚያየውን ሳይካትሪስቱን አቶ ያሬድን ደውሎ መጥራት ነበር ወዲያው ስልኩን አነሳና ያሬድ ጋር ደውሎ ችግር ውስጥ እንደሆነ እና ሊያወራው እንደሚፈልግ ነገረው አቶ ያሬድ ሴኮንድ ሳያባክን በ 40 ደቂቃ ውስጥ ናሆም ቤት ተገኘ.
"እሺ ልጅ ናሆም ምን ተፈጠረ?"
"ምን ያልተፈጠረ አለ?"
" ምነው በሰላም?"
"እኔ እንደ ንስሀ አባት ላንተ የምደብቀው እንደሌለኝ ታውቃለህ"
"በሚገባ ታዲያ...."
" ፊሊጶስን አስታወስከው?"
"አዎ ያስገደልከው?"
"አዎ"
" እና ፊሊጶስ ምን?"
"እህቱን አገኘናት "
"እና?"
" እና ምን ይመስልሀል?"
"ብዙ ጊዜ ልታስገድላት እንደምትፈልጋት ነግረኸኛል በስተመጨረሻም እጅህ ላይ ወደቀች ያ ምርጥ የምስራች ሆኖ ሳለ ያንተ መከፋት እና መደበር ምክንያት ነው ግራ የሆነብኝ"
"አዎ ግን ልጅቷን ከዚህ በፊት አውቃታለሁ"
" ለምን ያህል ጊዜ?"
"3 ቀን "
" ሀሀሀ እየቀለድክ ነው? እሽ ቆይ እና?"
"እኔንጃ ለህይወቴ አደጋ እንዳለው ባውቅም ልጅቷን ማስገደል ግን አልችልም"
"ለምን?"
"ምክንያቱም ለራሴም ግራ በሚገባ መልኩ አፈቅራታለሁ"
"ምን? በ 3 ቀን?"
" አዎ በ 3 ቀን!"
"ለነገሩ ተዋት እንደሌሎቹ ካገኘሀት ቦሀላ ትጥላታለህ ... "
" አይመስለኝም ሲጀመር በቀላሉ የምትገኝ ልጅ አደለችም ሲቀጥል ደግሞ ብትገኝ እንኳን አልተዋትም አልችልም እሷን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳያት የተሰማኝ ስሜት እስካሁን ከሴት ልጅ ተሰምቶኝ አያውቅም!"•••••••••

"ማለት ናሆም አፈቀርክ እንዴ"
"-ይመስለኛል!" ከ ፈዛዛ ፈገግታ ጋር
"ተው ስሜት እንዳይሆን"
"በፍፁም!"
"ወይኔ ወንድሜ ስንቱን እንዳላርበደበድክ የ መስፍን በቀለን ደም መላሽ ዘፈን እየሰማህ ቁጭ ትል?"
"አቶ ያሬድ እየቀለድኩ አይደለም "
"ከ መጨነቅ ምንም የሚገኝ ነገር የለም ከማሰብ እንጂ"
"እኮ አስባ... አስብ"
"መተው ካልቻልክ አብረሀት ብትሆን የሚፈጠረውን ችግር እንዴት ማስወገድ ይቻላል?"
"እኔስ ግራ የገባኝ እሱ አደል?"
"እኮ መላ ፍጠራ"
"ተዋት"
"ምን?"
"አዎ ተዋት በቃ"
"አልችልም አልፈልግምም"
"እሺ ቆይ አብረሀት ብትሆን እና ድንገት የወንድሟ ገዳይ መሆንህን ብታውቅ ምን እንደሚፈጠር አታውቅም?
"እኔ አልገደልኩትም "
"ያው ነው አስገድለኸዋል ለሷ ልዩነት የለውም ይሄ በተጠመደ ፈንጂ ላይ ከመራመድ ለይቼ አላየውም"
"ግን እኮ ይቅርታ መጠየቅ እንችላለን"
"ተው እንጂ የገደልከው እኮ ድመቷን አይደለም ወንድሟን ነው!"
"የገደልከው አትበለኝ አልገደልኩም!" ብሎ ጮኸበት
" ጥሩ ያስገደልከው"
"አዎ ግን እኮ ይቅርታ ታደርግልኝ ይሆናል "
"አታደርግልህም ! ፍቅር ያጃጅላል የሚባለው ለካ እውነት ነው ተጃጃልክብኝ እኮ ናሆም? ለማንኛውም ጊዜ ወስደህ አስብበት"
"እሺ አንተም አስብበት "
"ፎቶዋን አሳየኝ እስቲ"
"ይሄው" ቶም የሰጠውን ፎቶ ከኪሱ እያወጣ
"ዋ.....ው አንተ እውነትም ቆንጆ ናት" ገላመጠውና ፎቶዋን ነጠቀው
"ለተራ ሴት እንደማልሸነፍ ታውቃለህ"
"እንዴ በሚገባ እንጂ ወዳጄ ግን አንድ ሀሳብ አለኝ"
"ምን?"
"ለምን አልዛይመር እንዲይዛት አናደርግም?"
"ምን? ጥሩ ሀሳብ ነበር ግን አልዛይመር ቫይረስ አይደል በ መርፌ መሰጠት አይችል?"
"አዎ ግን ብዙ ሰዎች እንደዛ የሚሆኑት ከኋላ በኩል አለው የ ጭንቅላት ክፍላቸው ላይ አደጋ ሲደርስ ነው"
"ስለዚህ....?"
"ስለዚህ ያንን አደጋ ሆነ ብለን ማድረስ እንችላለና ምን ይመስልሀል?"••••••••••••

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.4K viewsAbela, 17:30
Open / Comment
2023-06-04 12:01:56 1.
የተነቃነቀን አጠበቅን ብለው የሚቀጠቅጡት
በሀገሬው ምድር ህፃንን አብዝተው
ወልደው ያላረጡት።
ከጨቅላ መንጋጋ የእናት ጡት ወትፈው
ለቅሶን ሚያስታግሱ
መመገቢያ ቋቱን እሬት እየቀቡ ድግስ የደገሱ።
አፈር ስሆን ብለው በጥቅልል እንጀራ
ሚያጣድፉ ጉርሻ
ለታይታ ለወሬ እህል ለሚዘሩ በደረቀ እርሻ

እናመሰግናለን!

2.
ለፈሰሰ እንባ ከንፈር ተመጦለን አለሁኝ ለሚለን
አባሽ ያጣ አይን ደም ለብሶ ደም ቢያለቅስ
ዞር ብሎ ላላየን።
ለመሸበት ሯጭ አዳር ፈቅደውለት እንቅልፉን ቢያሸልብ
ከመተኛው ስፍራ ባንድ ከፍተውበት
ቀልቡን ላሳጡት ልብ።

እናመሰግናለን!

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.6K viewsAbela, 09:01
Open / Comment
2023-06-04 08:20:06 *"*ድንጋይ ና ገንቦ*"*

አቅሟን አታቅ ገንቦ
   ከድንጋይ ተጣልታ፣
በጥፊ በርግጫ
   በቴስታ ልትመታ፣
ገልጋይ አስቸግራ
   ሩጣ ብትገጨው፣
ያ ደንዳና ድንጋይ
   መላ አካሏን ፈጨው።


ኤዶምገነት ፃፈችው
@Edom_Ge

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.5K viewsAbela, 05:20
Open / Comment
2023-06-03 21:01:44 ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 4

•••••••ወደ ውስጥ ገባ ሁሉም ክብ ሰርተው መጠጥ እየታዘዘ ነበር ምንም የተለየ ነገር እንደማያይ ሲገባው ተመልሶ ወጣ 11 ሰአት ሊሆን ነው የቀጠሯቸው ሰአት እየደረሰ ነው ልብሱን ለመቀየር ወደቤት ሄደ ልብስ ቅየራው ብቻ አንድ ሰአት ፈጀበት ይህ ይሻላል?
አይ ይህ ይሻላል? .እያለ ሲያማርጥ የመጨረሻ ምርጫው ሸሚዝ እና ሱሪ ላይ አረፈ ያንን አድርጎ ስልኳን መጠባበቅ ጀመረ እንደምትደውልለት እርግጠኛ ነበር ሰአቱ እየሄደ ነው 1 ሰአት ሆነ አሁንም አልደወለችም ከምሽቱ 2 ሰአት ሲሆን ትግስቱ አለቀ ደወለላት
"ሄሎ"
"ሄሎ"
"ቤቲ እስካሁን ስልክሽን እየጠበኩ ነበር እኮ"
"ኦ ይቅርታ ዛሬ ከሰው ጋር መዝናናት ሙዴ ስላልሆነ ነው" ወዲያው ቅድም ከሰዎች ጋር ግሮሰሪ የገባችው ትዝ አለውና
"ከሰዎች ጋር ወይስ ከኔ ጋር?" አላት
" ካንተ ጋር " አለችው ንዴቱ አናቱ ላይ ሲወጣ ይታወቀዋል
"እሺ" ብሎ ስልኩን ዘግቶት መኪናውን አስነስቶ ወጣ ቅድም አያት ግሮሰሪ ሄደ ቅድም አየው ቦታ ላይ የለችም ወደውስጥ ገባ ባንኮኒው ጋር ተቀምጣ ብቻዋን እየጠጣች አያት ቀጥ ብሎ ከሄደ ቦሀላ "ወምበሩ ሰው አለው?" አላት ከፊቷ ወዳለው ባዶ ወምበር እየጠቆመ
"እ?" ምላሿ ዝምታ ነበር የንቀት መሆኑ ስለገባው በ እምቢተኝነት ወምበሩ ላይ ተቀመጠ ቤቲ እስካሁን እያጨሰች እየጠጣች ነው ድንገት ስልኩ ጠርቶ ወደ ውጪ ወጣ ቶማስ ነበር
"ሄሎ ቶም!"
"ሰላም ነው?"
"አለሁ ምን አዲስ?"
"እንኳን ደስ አለህ!"
"ምን ተገኘ?"
"በ እግር በፈረስ ስታፈላልጋት የነበረችው የ ፊሊጶስ እህት በ እጃችን ገብታለች "
"እና ምን እየጠበቃችሁ ነው አስወግዷታ"
"እሱ የማይቀር ነው ግን ለሁሉም አንተ ማንነቷን መኖሪያ ቤቷን እና አኗኗሯን ማየት አለብህ ከዛ ፖሊስ ጣቢያ ለጥያቄ ብትፈለግ እንኳን ብዙም ቃል ለመስጠት አትቸገርም !"
"መልካም ነገ እንገናኛለን ሁሉንም ትነግረኛለህ"
"እሺ ደህና እደር"
ስልኩን ዘግቶት ወደ ውስጥ ተመለሰ አሁንም እያጨሰች ነው

"ቆይ ለምንድነው የምታጨሽው?"
" ለምን ይመስልሀል? "
"እኔ በምን ላውቅ እችላለሁ"
"አላውቅም!"
"እሺ የሆነ ህይወትሽን ያበላሸው ነገር ያለ ይመስለኛል ምንድነው?"
"ምንም ደህና ነኝ"
"አይ ጥሩ መጠጥ ወጪ ዛሬ በኔ ነው በደምብ ጠጪ" ከ ፌዝ ፈገግታ ጋር
" ይቅርታ ጋብዤ እንጂ ተጋብዤ አላውቅም " በተያያዘ አፍ
" እሺ በቃ ደስ ያለሽን አድርጊ"
ፍዝዝ ብሎ እያያት ነው ልቡን ስታሸንፈው ይታወቀዋል ግን ሽንፈቱ በጣም አናዶታል ምክንያቱም የተሸነፈው ከማንም በላይ ለምትንቀው ሴት ነው
"ቆ..ቆ...ቆ...ቆይ ግን እዚህ እንዳለሁ እንዴት አወክ?" በጥርጣሬ የስካር አይን እያየችው ...
"ወፏ ነግራኝ"
"ሀ..ሀ..ሀ ያንተዋ ወፍ ደግሞ ትለያለች ባክህ?" ከ ለበጣ ሳቅ ጋር
"አንቺ ያለሽበትን ቦታ ማግኘት ለኔ እጅግ በጣም ቀላል ነው"
"እኔን ግን የማይታሰብ ነው!"
"አንቺን ምን?"
"ማግኘት!"
"ጊዜ ይፍጅ እንጂ አህያ የጅብ ናት ቤቲዬ!"
"እውነት ነው ችግሩ አህያና ጅቡን መለየቱ ላይ ነው"
" ሀሀሀ ቅኔዎችሽ ጦር ናቸው ባክሽ?"
"ጥሩ ትፈታለህ ማለት ነው እንውጣ?"
"እሺ"
በመኪና ከሸኛት ቦሀላ በደስታ ወደቤቱ ገባ ነገር ግን አንድ ነገር አየ ቤቲ ቦርሳዋን ረስታው ነበር ያ ደግሞ ነገ በጠዋት ቤቷ እንዲሄድ ምርጥ አጋጣሚ መሆኑ ከምንም በላይ አስደስቶታል......
አይነጋ የለም ነጋ 2 ሰአት ላይ ውጭ በሯ ጋር ተገኝቶ በክላክስ ሰፈሩን መበጥበጥ ጀመረ ወጥታ በሩን ከፈተችለት እና ሳሎን ገባ
"በጠዋቱ ምንድነው እንደዚህ ..." ሳትጨርስ ማውራት ጀመረ
" ትላንት ቦርሳሽን.... " ብሎ ቦርሳዋን በ አንድ እጁ ከፍ አደረገላት
"ኦ ...ይቅርታ !" ብላ ተቀብላው
"አረፍ በል" ስትለው እንደማንገራገር እያለ አንድ ፎቶ አይኑ ውስጥ ገባ ከመጠን በላይ ደነገጠ እጆቹ መንቀጥቀጥ ጀመሩ በጣም እንደደነገጠ ፊቱ ያሳብቃል ቤቲ"ምን ሆነህ ነው?" ብትለውም በድን ሆኖ አይኑን ፎቶው ላይ ተክሎ ቀረ ምክንያቱም ፎቶው•••••••••
የሚያውቀው ሰው ነበር እጁ እየተንቀጠቀጠ ወደፎቶው እየጠቆመ
"ይ ይ ይ ... ይሄ ማነው ? " አላት
"ይሄ....." ወደ ፎቶው ተራምዳ ከ ብፌው ላይ አንስታ ይሄ ወንድሜ ነው ፊሊጶስ ይባላል " ይባስ ደነገጠ
"ምነው ደነገጥክ? ችግር አለ?"
"ይ..ይቅርታ መሄድ አለብኝ!"
"ይሻላል?"
" አ አ አ ዎ ይሻላል !" ምራቁን ከጉሮሮው ላይ ለመዋጥ እየታገለ
" እሺ! " ብሏት ቤቱን ለቆ መውጣት ጀመረ አራት እርምጃ ሳይራመድ ጠራችው
"ናሆሜ"
"ወዬ"ወደ ኋላ እየዞረ
"ለቦርሳው አመሰግናለሁ እሺ? በጣም የምፈልገው ፋይል ነበር ውስጡ" ብላ ተንደርድራ መጥታ አቀፈችው ሁኔታዋ ግራ አጋብቶታል ትላንትና ከዛ በፊት እንደዛ ስትንቅ እና ስታንቋሽሸው የነበረች ልጅ ዛሬ እንደዚህ መሆን ቅድም ካየው ፎቶ በላይ አስደንግጦታል ስታቅፈው የሆነ ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶታል
"እሺ ምንም ችግር የለውም" ብሎ ተሰናብቷት ሄደና መኪናው ውስጥ ገብቶ ለ ቶም ደውሎ በፍጥነት ሊያገኘው እንደሚፈልግ ነግሮ ቀጥሮት መኪናውን ወደ ቀጠረበት ቦታ ማክነፍ ጀመረ
°°°
ቤቲ ሲወጣ ጠብቃ በሩን ከውስጥ ከዘጋች ቦሀላ ሶፋ ላይ ያለውን የወንድሟን ፎቶ አንስታ ካቀፈችው ቦሀላ ወንድሜ አሁን እኔ አለሁልህ ገዳይህን በቁሙ እገልልሀለሁ ከሞቱት በላይ ከቆሙት በታች አደርግልሀለሁ!" ብላ ትላንት የተፈጠረውን ማስታወስ ጀመረች ትላንት ከ ልዑል ጋር ተገናኝተው የ ወንድሟን ገዳይ ፎቶ ሲሰጣት ትዝ አላት አገዳደሉን ምክንያቱን የነግራት ትዝ ሲላት አይኗ ደም ለበሰ ፊቷ ቲማቲም መሰለ የያዘችውን ፎቶ ወረወረችው ...ፍሬሙ ድቅቅ አለ ደንግጣ አንስታ አቀፈችው እና ወዲያው ፍሬሙን ለማስቀየር በመኪናዋ ይዛው ሄደች ከሰፈር ወደ ዋናው አፓልት መውጫ አካባቢ መኪኖች ተጨናንቀው ነበር....
°°°

ናሆም ቶማስን ቀጠረበቅ ሞል ደርሶ ወደ ካፌው ገባ ቶማስ አንድ ወምበር ይዞ ተቀመጧል እንዳየው እጁን አወዛወዘለት ናሆምም ወዲያው በቀላሉ አየውና በፍጥነት ወደ ቶማስ ሄዶ ሰላም እንኳን ሳይለው ወምበር ስቦ ተቀምጦ
"እ ... የታለ ፎቶዋን አሳየኝ !"አለው
"ኧረ ተረጋጋ ......እሺ ቆይ " እጁን ወደ ደረት ኪሱ ውስጠኛ ክፍል እያስገባ.... ጥቂት ቆይቶ አንድ ፎቶ አወጣና "ቆይ የቤቱ ደግሞ ... ብሎ በሌላኛው እጁ ኪሱ ሲገባ ናሆም ትግስት በማጣት በ እጁ የያዘውን ፎቶ መንጭቆ አየውና ፊቱን በ አንድ እጁ ሸፍኖ በረጅሙ እየተነፈሰ ወደኋላው ተደገፈ ሁኔታውን ያየው ቶማስ
" ምነው አለቃ ችግር አለ እንዴ?" አለው
"አዎ ያውም እጅግ በጣም ትልቅ !" እጁን ከፊቱ ላይ ሳያነሳ
"ኧረ አለቃ ምንም አታስብ ይሄኛው እንደውም ቀላል ነው ልጅቷ ብቻዋን ነው የምትኖረው ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም አደገኛ ብትሆንም ለማስወገድ ግን ሴኮንድ አትፈጅም ሁሉም የቤተሰቦቿ አባላት በህይወት የሉም ማንም አይጠይቀንም የድመት ነፍስ በለው እሷን ማስወገድ ከ ፊሊጶስ በላይ ቀላል ነው እንደውም ናፍቋታል እያሉ ነበር " ከ ፌዝ ሳቅ ጋር
'' በዛ ላይ እኮ ቤት ያለው ሀብት ራሱ....."
"በቃህ!" ብሎ ጠረጴዛውን ሲመታው ሁሉም የ ካፌው ሰዎች ደንግጠው ዝም ብለው ሲያፈጡበት አጎምብሶ ዝም አለ......


.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.3K viewsAbela, 18:01
Open / Comment
2023-06-03 20:25:06 ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 3


••••••••• ቤተልሄም ... ቤተልሄም ይል ይላል በህይወቱ እንደዚህ እንቆቅልሽ የሆነች ሴት ገጥማው አታውቅም ዝናዋ የልቡን የሆነ ክፍል ሲያጠምድ ይሰማዋል ወንድነትን የተላበሰ ሴትነቷ ገዝቶታል ቢሆንም ከሁሉም በፊት እሷን ወጥመድ ውስጥ ማስገባት እንዳለበት ያውቃል ግን ወጥመድ ውስጥ የምትገባ አይነት ቀሽም ሴት እንዳልሆነችም ያውቃል ህሊናም ብዙ ነግራዋለች ስለዚህ የመጀመርያ እርምጃዬ ከሷ ጋር መግባባት ይሆናል አለ ለራሱ ይህንን እያሰበ እንቅልፍ ወሰደው በማግስቱ ተነስቶ ስለ ቤቲ ማቀዱን ቀጠለ የመጀመሪያ ስራው ወሰ መስሪያ ቤቷ መሄድ ነበር ነገር ግን ሁለት ድርጅት እንዳላት የሰማው ትዝ ሲለው የትኛው ጋር መሄድ እንዳለበት ግራ ተጋባ ጠዋት የምትገባበትን ደውሎ የትኛው ጋር እንደምትገባ አረጋገጠ እና ዘንጦ መንገዱን ወደ መስሪያቤቷ አደረገ ....
..... ያለምንም ፈቃድ የ ቢሮዋን በር በርግዶ ገባ በዝምታ ትመለከተው ጀመር
" ይቅርታ የኔ ቆንጆ አረፍ ማለት ይቻላል?" እየተንተባተበ ... ያየውን ማመን አልቻለም ያ ትላንት ተጥሎ በ ከለላ ሲያየው የነበረ ውበት ዛሬ በ ኮስሞቲክስና በ ውብ ቀሚስ ታጅቦ ሲመለከት ያየውን ማመን ተሳነው ወምበሩን በ እጁ እየዳበሰ አይኑን ሳይነቅል ተቀመጠ
" ተቀመጥ እኮ አላልኩህም ?"
"አይኖችሽ ይናገራሉ"
" አይን የማምበብ ችሎታው እንኳን ያለህ አትመስልም"
"እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ"
" ምክንያቱም ችሎታው ቢኖርህ አይኖቼን አይተህ ትወጣ ነበር"
"ይሄንን የመሰለ ውበት ለማን ነው ጥዬ የምወጣው?"
"ለራሴ! ሰው አያስፈልገውም!"
"ይሻላል? "
"አዎ ምን እግር ጣለህ? "
"አይ አለፍ ስል በዛው ሀይ ልበልሽ ብዬ ነው "
" እሺ አመሰግናለሁ"
" እና ማታ ተገናኝተን ሻይ ቡና ብንልስ?"
"ማታ ላይ ሻይ ቡና ነው? ወይስ ራት የሚባለው?" የ ምፀት ፈገግታ ፈገግ እያለች
" እራት !" ከ አግራሞት ፈገግታ ጋር
" መልካም! ደስ ካለኝ እደውልልሀለሁ"
"ካላለሽስ?"
" እንደሙዴ".........
"መልካም ማታ ትላንቱ ሆቴል እጠብቅሻለሁ"
"እንደዛ አይነት ቦታ አይመቸኝም ይቅርታ!"
"እሺ የት ነው የሚመችሽ?"
"እኔንጃ ብቻ የሚመቸኝ ቦታ ያንተ መኖር ከተመቸኝ ደውዬ አገኝሀለሁ"
"እሺ እጠብቃለሁ"
" አሁን ስራ ላይ ነኝ ከይቅርታ ጋር..."
"እሺ አመሰግናለሁ" ብሎ ወጣ እና የ ፀሀፊዋን ስልክ ተቀብሎ ምሳ ሰአት ላይ ቀጥሯት ሄደ....
ምሳ ሰአት ላይ ከቀጠራት ከፀሀፊዋ ጋር ተገናኝተው ስለ ቤቲ ማውራት ጀመሩ
" እና ስራ ቦታ ምን አይነት ባህሪ አላት? "
" ተግባቢ አይደለችም!"
"ማለት? "
"በቃ በጣም ኮስታራ ናት በ ሳምንት ሁለት ወይም 3 ቀን ነው ስራ የምትገባው እነዛን ቀናት ግን በደምብ ትቆጣጠረናለች እንግዶችን ሁሉ ቀጠሮ የማሲዘው ለነዛ ቀናት ብቻ ነው "
"እና ኮስታራ ናት እያልሺኝ ነው?
" አዎ"
"እሺ እሺ ሌላስ ስለሷ የምትነግሪኝ ነገር አለ ስለሷ?"
"ኧረ ምንም የለም ቆይ አንተ ግን ለምን ማወቅ ፈለክ ስለሷ?"
"እሱ ያንቺ ጉዳይ አይደለም" ብሎ ጠረጴዛው ላይ የታሸገ 10 ሺ ብር አስቀምጦላት ተነስቶ ሄደ
"የማታ እንጀራ ይሉሀል... ይሄ ነው! " ብላ 10 ሺ ብሯን አንስታ ሂሳብ ከፍላ ወጣች ናሆም የተቻኮለው ያለ ምክንያት አልነበረም ቤቲ ከስራ ስትወጣ ስላያት ለመከተል ነበር እናም መኪናዋን ተከትሏት የቤቲን መኖሪያ ቤት አወቀ ስትገባ አያት "ወይ ሴት እና ውበት? " ብሎ ለራሱ ተገረመ እስክትወጣ ብዙ ቢጠብቅም በጣም ቆየች ከስአት ስራ እንደማትገባ በ ሰአቱ አረጋግጧል ውስጥ ገብታ ቆይታ ይሆናል ብሎ ለመመለስ ሲያመነታ ድንገት የውጪ በራቸው ተከፍቶ ቤቲ ስትወጣ አያት ያየውን ማመን አቃተው ቅድም ጉልበቷ ድረስ ቀሚስ ሄል ጫማ ኩል ሊፒስቲክ ሳምሶናይት እጇ ላይ ያየባት ልጅ አሁን ስትወጣ ፍሪዝ ፀጉሯ ግምባሯ ጋር ተይዟል ረጅሙ ፀጉሯ ወደላይ ተይዞ ግምባሯ ላይ ተበትኗል ሊፒስቲኳ የለም ከላይ ባለኮፍያ ረጅም ሹራብ ከስር የተቦጨቀ ጥቁር ሱሪ እና ስኒከር አድርጋ ሲጋራ እየለኮሰች ከቤቷ ወጣች አይኑን ማሸት ጀመረ የሚያውቃት ቤቲ አልመስልህ አለችው በርግጥ ከትላንቱ ማንነቷ ጋር ብዙም ለውጥ የለውም ቅድም ካያት ጋር ግን እህቷ እንኳን አትመስልም ቅርፁዋ ውበቷ ሁሉ የተደበቀ ሆነበት ያም ሆኖ ታምራለች እንደምታጨስ ግን አያውቅም ነበር ወዲያው እንቅስቃሴዋን መከታተል ጀመረ እናም ጥቂት ተራምዳ ከሰፈሩ ጎረምሶች ጋር ሰላም ተባብላ ተቀላቅላቸው መሳቅ መጫወት ጀመረች ስትስቅ ለመጀመሪያ ጊዜ አያት በጣም ነው የምታምረው ወዲያው ወደቤት ተመልሰው ገብተው ሁሉም በመኪና ወጡ ሾፌሯ ቤቲ ናት መኪናቸውን ተከትሎ ሲሄድ አንድ ግሮሰሪ ማረፊያው አደረገ ሲገቡ ሳያዩት ተከትሏቸው ወደ ውስጥ ገባ •••••••••

.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.7K viewsAbela, 17:25
Open / Comment
2023-06-03 10:06:19 የሞት ንፋስ በምድሪቱ ባለነበረ አይነት ነፈሰ ።
ደቂቅ ሊቁን እያፈሰ ፤
ያቀፉትን እየቀማ
ቀሪዎቹን እያመሰ ።
በዚህ ሁሉ ቁጣ መሐል
የኔ ማለፍ ወይም መትረፍ
መች ይታያል እንዳግራሞት ?
ሳላገኝሽ ብቻ እንዳልሞት ።

በእርግጥ ሞት የማይቀር ነው
ይሄን ነገር ስናስበው
ትንሽም ቢሆን አፅናኝ ነው ።
ያለ ፍርሃት እንዲሰው
ያስጎነጫል መሪር ሐሞት ፤
ሳላገኝሽ ብቻ እንዳልሞት ።

እንደ አጋፋሪ እንዳሻው
ውስጥ ለውስጥ በየ ዋሻው
በመንገድ ዳር ፥ በየ ጢሻው
ዕጣን ዣንጥላው ለታቦት
ለአዉልያ አርዳለሁ ጠቦት
ሳላገኝሽ ብቻ እንዳልሞት ።

By Hab HD

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.9K viewsAbela, 07:06
Open / Comment
2023-06-02 21:20:11 ቤተልሄም


በ ኤልሳ

ክፍል 2

•••••••••• ጠጣው ። ሁሉም ዳንሳቸውን አቋርጠው ከበቡት "ማናት?" አላት ህሊናን
"ምነው ናሆም ችግር አለ እንዴ?" አለችው
" የለም ግን የሆነ ነገሯ ስቦኛል " አላት የ እልህ ፈገግታ ፈገግ እያለ " አይ እንደዛ ከሆነ ደሲላል !"
"አዎ እና ስልኳን ስጪኛ" ...ስልኳን ሰጥታው ተለያዩ ህሊና የጓደኛዋ ናሆም እቅድ ውስጥ መግባት ቢገባትም ቤቲን በደምብ ስለምታውቃት ብዙም ግድ አልሰጣትም ምክንያቱም ቤቲን በደምብ ታውቃታለች
ቤቲ ቤት ገብታ ሰራተኛዋን ራት እንደበላች ነግራት ወደ መኝታ ክፍሏ እየገባች እያለ ሱሪዋ ኪስ ውስጥ ያፈረገችው ስልኳ ቫይብሬት ሲያረግ ጭኗን ተሰማት አንስታ ማውራት ጀመረች
"ሄሎ"
"ወዬ የ ቤቲ ስልክ ነው?"
"አዎ ነኝ ማን ልበል?"
"ናሆም ነኝ!"
"ናሆም ናሆም ?"
" ስንት ሰው እያናገረሽ ጥለሽ ሄደሻል?"
" ኦኬ አወኩህ"
"ደህና አመሸሽ?"
"የሰራኝ ይመስገን !"
"ቤት በጊዜ ገባሽ?" በ ለበጣ አነጋገር
"እሱ ያንተ ጉዳይ አይደለም " ብላው ስልኩን ዘጋችው ..... ድጋሚ ተደወለ

" ሄሎ"
"ማን ስለሆንሽ ነው ስልኩን ጆሮዬ ላይ የምትዘጊው የተዋወቅን አልመሰለኝም እኔ ጆሮ ላይ ስልክ የመዝጋት መብቱም የለሽም!....." አውርቶ ሳይጨርስ ስልኩ ጆሮው ላይ ተዘጋ በጣም ተናዷል በህይወቱ አይደለም ተራ ብሎ የሚያስባት ሴት እና ደፋር የሚባሉ ሰዎች እንኳን እንደዚህ ደፍረውት አያውቁም የ ቤቲ የንቀት ሚስጥር ባይገባውም የሆነ የ እልህ ፍቅር እንደያዘው ገብቶታል ሲያገኛት እንደሚንቃትም ያውቃል ወዲያው ህሊና ጋር ደወለ
"ሄሎ"
"ሄሎ ናሆም"
"ይቅርታ ከመሸ ደወልኩ"
"አዎ በሰላም ነው?"
"አይ ስለ ቤቲ የምታውቂውን ሁሉ እንድትነግሪኝ ነው"
"እሺ ምን ልንገርህ?"
"ፀባዩዋ ልማዶቿ... ብቻ ሁሉንም"
"እሺ ቤቲ ማለት•••••••••
በጣም ከባድ ሰው ናት ቤተሰቦቿ ሀብታም ስለነበሩ አሁን ሁሉም ሀብት የሷ ነው ሁለቱም በህይወት የሉም "
" ብቸኛ ወራሽ ናት?"
"አዎ እንደነፍሷ የምትወደው ታላቅ ወንድም ነበራት ግን እሱም በህይወት የለም እናም አሁን ብቸኝነትን ስራዬ ብላ ይዛዋለች በጣም ተጎድታ ስለነበር ሰው መቅረብ አትፈልግም ትጠጣለች ታጨሳለች በቃ የማታደርገው የለም ታሳዝነኛለች ብታይ"
"አዎ ያሳዝናል በጣም
ግን አሁን ብቻዋን ነው የምትኖረው?"
"አዎ "
"ምን አይነት ወንድ ይመቻታል?"
"ማን ሞክሮት ብለህ? ስለወንድ ሲነሳ የንቀት መአት ነው የምታዘንብብህ "
"የምር? ቆይ እሺ ለምን ወንድ ትጠላለች? ከ ፍቅር ግንኙነት ጋር የሚያያዝ መጥፎ ታሪክ አልሰማሁም እስካሁን "
"አዎ ግን ካላገኙ ማጣት የለም የምትለው ፈሊጥ አላት ለዛ ይመስለኛል"
"እና ቤቲ የ ምን አይነት ወንድ የምትሆን ይመስልሻል?"
"እሱ የሁላችንም እንቆቅልሽ ነው"
"እኔ እፈታዋለሁ"
"አይመስለኝም ናሆሜ"
"ለምን?"
"በኔ እይታ ቤቲ ነብር ከተባለች አንተ ድመት ነህ"
"አልገባኝም?"
"ጭራሽ አትወዳደሩም ልልህ ፈልጌ ነው እንደ እውነታው"
"እሱን አሳይሻለሁ ናሆም ነኝ ታውቂኛለሽ!"
"ለማየት ያብቃህ !..... ደክሞኛል በቃ ደህና እደር !"
" እሺ ቻው አመሰግናለሁ"
" anytime !"
ስልኩን ዘግቶ ማሰብ ጀመረ ህሊና የሱን ባህሪ እና ሀያልነት ምን ያክል እንደምትፈራ ያውቃል ነገር ግን ስለ ቤቲ ሲነሳ እንደዚህ የሆነችበት ምክንያት የ ቤቲን አደገኛነት ይበልጥ አጉልቶ አሳየው እንዳይተዋት አፍቅሯታል ቢተዋት ደግሞ ፍቅሩ ይልቃል እንጂ አይቀንስም እንዳያፈቅራት እና እንዳይጋፈጣት የ ህሊና ቃላት አስፈርተውታል ቢሆንም ግን 2ኛውን መርጧል !
ልቡ ውስጥ አንድ ቃል ያቃጭላል
"ቤተልሄም ...ቤተልሔም... ቤተልሔም... ቤተልሔም ••••••••••


.......... ይቀጥላል........

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
7.1K viewsAbela, 18:20
Open / Comment