Get Mystery Box with random crypto!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Logo of telegram channel bewketuseyoum19 — በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ
Channel address: @bewketuseyoum19
Categories: Courses & guides
Language: English
Subscribers: 129.49K
Description from channel

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


The latest Messages 9

2023-05-10 18:47:45 የካድኩት ልጅ አለኝ
ወልጄ 'ማላቀው አሱም የማያቀኝ።

ግሩም ድንቅ ፍጡር
ከሱ በላይ ላሳር።
አይኖቹ ከዋክብት ጠይም አሳ
መሳይ
እኔን እናቱን ሲሆን አይኑ ዞሮ 'ማያይ

ምጡቅ አንጎል አለው
አለም ያደነቀው
ግንሳ.... ብልሀት ጎደለው።
አንጀቱ እንስፍስፍ
ማየት የማይችል ግፍ።
ግንሳ ለናቱ....
አይራራ አንደበቱ።

እናትህ ትቃጠል እናትህ እንዲ
ትሁን
እናትህ..... እናትህ.....የስድብ
ውርጂብኝ።

የካድኩት ልጅ አለኝ
እሱም የማያቀኝ
ስድብ የሚያረገኝ
አስር ጣት እያለው...
ሁለቱን ሦስቱን ካልቆረጥኩ
የሚለኝ።


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.3K viewsAbela, 15:47
Open / Comment
2023-05-10 10:56:03
የሚሸጥ ቤት
105 ካሬ አለም ባንክ ሜዳ መስጊድ አካባቢ
ፊቱ ወደ ምሥራቅ የሆነ ከፊትለፊት ሰፊ መንገድ እና የሚያምር ግሪን ኤሪያ ያለው።
ዲጅታል ካርታ ሙሉ ዶክመንት ያለው
ለመኖሪያ በጣም ተመራጭ ሠፈር
ዋጋ 13 ሚሊዮን
2% ኮሚሽን ተደስተው ይከፍላሉ
ስልክ 0911468394 ገዢ ብቻ ይደውል
4.4K viewsAbela, 07:56
Open / Comment
2023-05-10 09:52:35 የስርቻው መጣጥፍ | Notes from the undergroun

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
4.0K viewsAbela, edited  06:52
Open / Comment
2023-05-10 09:01:25
0978076525
በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩም መምጣት ሳያስፈልግ ባሉበት እንሰራለን 
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሄ ሀብት
2 ለህማም
3 ለመስተፋቅር
4 ቡዳ ለበላው
5 ለገበያ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ሚስጥር የሚነግር
8 ራዕይ የሚያሳይ
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ስራይ
14 ጋኔን ለያዘው ሰው
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለቁራኛ
17 ለአምፅኦ
23 ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት

ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ

1 የመኖሪያ ፍቃድ ላላገኙ  መፍትሄ
2. ከሀገር ውጪ ስራ እድል ላጡ
3. ንግድ ጀምረው አልሳካ ላላቸው
4. ገንዘብ ለሚያባክኑ
5 ሰውፊት መቆም መናገር ለሚፈሩ 
6. ለሀብት  ለንብረት ሚሆንም አለን
7   ለስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ለውጪ ሀገር ለሚኖሩትም እየሰራን ነው
8 ፍቅረኛ አልያዝ ላላቸውም አለን
9. ትምህርት አልገባ ላለው
10 መስተፋቅር ፣የህዝብ መስተፋቅር
11. ከሀገር መውጣት እየፈለጉ ላልተሳካላቸው ። ከሀገር ውጪ ላላችውም መፍትሄ በልዩ ሁኔታ አለን  ይምጡ ይደውሉ ያማክሩን ።
ለምንኛውም ጥያቄዎ ይደዉሉ
0978076525
 
ባላቹህበት እንሰራለን
ቴሌግራም ቻናላችንን
ለመቀላቀል
3.9K viewsAbela, 06:01
Open / Comment
2023-05-10 08:43:13 "አለሽ ወይ"

በዕውቀቱ ስዩም

አለሽ ወይ አለሽ ወይ
አለሽ ወይ በጤና
ይመስገን ደመና፤

በገበሬው አጥንት፣ መሬቴን እያረስኩ
እንጀራ ሲጠፋ፣ ገበሬ እየጎረስኩ።
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና፤

ሰው ሲያፈርስ እያየሁ ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭቃ ነገድ ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
ያለምንም ፀፀት ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና፤

በምቾት መዲና የምንዱባን ትዝብት
እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳው ጎዳና
ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አናቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ
ልክ እንደ ገባሮች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብም እጀን እየሰደድሁ
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና፤

ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
ማዕበል ሲቃረብ ያመልጣል ሺመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ደመና
የኔ አዚም ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ አይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል፤

ይህንን እያየሁ
ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና፤

አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
አለሁ ግርምት ወሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
ምናገረው ኖሮኝ
የምለው ቸግሮኝ።


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
3.9K viewsAbela, 05:43
Open / Comment
2023-05-09 14:17:11 እዮሪካ

ከአይኔ ርቆ ተሸሽጎኝ ያጣሁትን
ቀን በሃሳብ ሌትም ሳይቀር ያለምኩትን
ናፍቆት ቀርጾ የሰራውን ገላ አካልሽን
በአይኔ አየሁት ዉብ አይንሽን
እዮሪካ
እዮሪካ
እዮሪካ. . .
ማየት ብቻ መች ሊያረካ
አገኘሁሽ በሃሳቤ በአይኔ በኩል
ዉበትሽን ከልቤ አጸድ ስክብ ስኩል
እፎይ
እፎይ
አገኘሁሽ እሰይ


የኔ እዮሪካ

ተጻፈ በ ይታያል ጌቴ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.4K viewsAbela, edited  11:17
Open / Comment
2023-05-08 18:26:04 #ዝም_ብትል_ምን_ትሆናለህ?

ስታስበው የሚቆጭህን ለመጨረሻ ጊዜ የተናገርከውን መጥፎ ነገር አስታውስ፡፡ ለምን ተናገርከው? ማለት የማያስፈልግህ ለመሆኑ እድል ነበረህ፤ አንተ ግን መናገርህ ብልህ ወይም የተረጋጋ ወይም ከሰው እኩል እንደሚያደርግህ   አሰብክ፡፡

ሮበርት ግሪን እንደጻፈው፣ “ብዙ ባልክ መጠን፣ በበለጠ ሁኔታ የማይረቡ ነገሮችን የመናገር አጋጣሚ ይኖርሃል፡፡” በዚህ አባባል ላይ እኛም፤ የበለጠ በተናገርክ መጠን፣ በበለጠ ሁኔታ ያለፉ መልካም አጋጣሚዎችን ልታበላሽ፣ ምላሽን ችላ ልትልና ራስህ ላይ ስቃይ ልታመጣ ትችላለህ የሚል እንጨምርበታለን፡፡

ልምድ የሌላቸውና በፍርሃት የተሞሉ ሰዎች ራሳቸውን እንደገና ለማረጋገጥ ይናገራሉ፡፡ ሆን ብሎ ከንግግር ልውውጥ ውጪ ለመሆንና ያለ እሱ ተቀባይነት ለመቀጠል የማዳመጥ ችሎታ ብዙም የማይገኝ ነው፡፡ ፀጥታ ጥንካሬና በራስ በቂ የመሆንን መንገድ የምንገነባበት መንገድ ነው፡፡

#ወርቃማ_ሕጎች መጽሐፍ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
6.1K viewsAbela, 15:26
Open / Comment
2023-05-08 17:16:20 መልከ ቀና አድርገኝ
ህይወቴ ቢቀለኝ.. .
አውለኝ በክብር
ቀባኝ ሞገስ ቅባት
ቀኖቼ ላይ ልንገስ
በሌሎች ፍርሀት።
ስጠኝ የመሪ ድምፅ
አጥር የሚሻገር...
መንገዴ እንዲሳለጥ
እንዲሆን ገር በገር ።
አልያ አልገፋትም...
ይህችን ስንኩል ዕድሜ
ለአይን አስቀይሜ፥
ቀልዬ ያለ ሞገስ...
ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው
ከሞት ደጅ የሚደርስ !!

(ሚካኤል.አ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.2K viewsAbela, 14:16
Open / Comment
2023-05-08 13:48:52 ( ባይገርምሽ )
እኔ አንቺን ማስብ በሞተ ሰውነት በቆማጣ ሰው ልብ
በጎደለ ይምሮ ፤ በማይታይ ምናብ
እንደምንም × 2
እያለ ጭልምልም ፤ ቀና ብዬ ባይም
መልክሽ አይታይም፡፡
Amu

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.2K viewsAbela, 10:48
Open / Comment
2023-05-08 09:04:39 እየወደዱ መራቅ


ትንቅንቅ ግብ ግብ
ከራስ ጋር መታገል
ከ አፋፍ ላይ መቆም
ከ ዝናብ መጠለል

መውደቅ እየፈለጉ
መበስበስን ሽተው
እግርን ከመራመድ ፍርሀት ሲመክተው
አፋፍ ደለል ሲሆን
ዳመናም ሲበተን
ፍቅር ሲኮሰምን
መውደድም ሲመክን

አይተው እንዳላዩ
አውቀው እንዳላወቁ
ተሰምቶ እንዳልተሰሙ
ራስን ሸሽገው
እውነትን በሀሰት አጣፍተው ገልድመው
አንገት አዘቅዝቀው መንገድ ሲራመዱ
ልብ ያለቅሳል እውነት ለጎረቤት ሆዱ

እየወደዱ መራቅ

ከነብስ ጓደኛ ከልብ ከታሰረ ነጠላ ቁራኛ
ሀሳብ ከገባ በችሎት አልባ ዳኛ
በውድም በግድም ከሆነ ቤተኛ
ከነብስ ትራስ ላይ ከተንተራሰ
ከአንድ ማዕድ ቀርቦ ከእጅ ከጎረሰ
በአንድ ሀዘን ስሜት እኩል ካለቀሰ
በአንድ ደስታ ስሜት እኩልም ከሳቀ
የህይወት መንጠቆ-ን ከስር ከሰበቀ
የኑሮውን ጓዳ ገልጦም ካልደበቀ

ምን ተብሎ ይሸሻል ምን ፈር ተይዞ
እንዴት ይሰጣል ጀርባ ፊትን አጠማዞ
ይሰቃል ይከብዳል አጥንትን ይወጋል
አይን እያለቀሰ ነብስ እዥን ያዣል
መላው ቢጠፋብን ነው እንጂ ቢቸግር
እንዴት ያለ ጉልበት ይራመዳል እግር

በሀሳብ መበለት መከፈል በሁለት
በናፍቆት መናጥ በትዝታ መቅለጥ
እሹሩሩ ማለት ራስን በለሆሳስ
እፍ ብሎ መጥፍት ልክ እንደ ንፋስ
ያሰኘኛል ከርሞ ከምወደው መራቅ

ከአፌ ልቃቂ አንድ ቃል አላወጣው
እወድሻለሁ ያለ ምላሴ እንዴት ሌላ ሊቃጣው
ከማንም አልባው ከከንፈር ላይ መሶብ ቅንጣትን ቀንሼ
ወደ ማንም አልሄድኩ እንኳን በሙሉ እግር ከጉልበቴም አንክሼ
ልላን ሰው አላቀፍኩ በርሀ አቋርጬ እርቀትን ጥሼ

ዛሬ ብዘጋ አንድበቴን
ከፊትሽ ብጋራድ እንዳታይ እኔነቴን
ጠልቼሽ አይደለም መውደዴም ተቀብሮ
አስችሎኝም አይደል ካንቺ መሄድ ዞሮ

ህምምምምምምም

ሁኖብኝ ነው እቴ እየሞሉ ማለቅ
በነገ ፍራቻ ዛሬ ላይ መጨነቅ
በስስት ሙሉ ፍቅር በስጋት መጨመቅ
ስነግርሽ ሀቂቃውን እውነታውን ሀቅ
የሞት ማቅ መልበስ ነው ካንቺ ጎን መራቅ
ቧልትም ነገር አይደል ዝባዝንኬ እንዲያው
ደርሶበት ያየው ነው ነገር የሚነባው



▾▵Řu‌▴▿

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
5.3K viewsAbela, 06:04
Open / Comment