Get Mystery Box with random crypto!

Corporate Lawyer

Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer C
Logo of telegram channel henoktayelawoffice — Corporate Lawyer
Channel address: @henoktayelawoffice
Categories: Loans, Taxes and Laws
Language: English
Subscribers: 461
Description from channel

⌚️10-11
⚖️" "⚖️

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


The latest Messages

2022-08-23 14:35:36
2.4K views11:35
Open / Comment
2022-08-23 14:35:00 _የሠ/መ/ቁ.188086_

በሌለበት ታይቶ የተወሰነ የወንጀል ክስ እንዲነሳ አቤቱታ ቀርቦ ውድቅ በተደረገ ጊዜ በወንጀል ህግ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 202(3) ስር ለተከሳሹ የተሰጠው በቅጣት ውሳኔ ላይ በይግባኝ የመከራከር መብት ተከሳሹ ባይኖርም እንኳን በህግ ረገድ ፍርድ ቤት በራሱ ተነሳሽነት በቅጣት ማቅለያነት መያዝ ሲገባው ያልያዘውን አልያም በቅጣት ማክበጃነት መያዝ ሳይኖርበት በተሳሳተ የህግ አተረጓጎም የተያዘ የቅጣት ማክበጃ ምክንያትን ብቻ የሚመለከት ስለመሆኑ በፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠ አስገዳጅ የህግ ትርጉም
2.5K views11:35
Open / Comment
2022-07-29 22:13:31
በጋብቻ ክርክር ላይ፣እንደኛው ተከራካሪ በጋብቻ እያለን የጋራ እዳ ለሶስተኛ ወገን አለብን ሌላኛው ተካራካሪ ድርሻውን እንዲከፍል ይወሰንልኝ ብሎ የመጠየቅ መብትና ጥቅም የለውም
ሰ.መ.ቁ.181649
6.5K views19:13
Open / Comment
2022-07-22 09:30:15
7.9K views06:30
Open / Comment
2022-07-20 10:21:15 የአካባቢያዊ ማስረጃ ምዘና
----------------
የሰ/መ/ቁ109441፡-የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃ ወንጀልን የፈፀመው ተከሳሽ መሆኑንና ከተከሳሽ
ውጭ ሌላ ሰው ወንጀሉን ሊፈፅመው አይችልም ከሚል መደምደሚያ ላይ ለመድረስ በቂና
አሳማኝ በሆነ ሁኔታ የሚያስረዳ ሆኖ ሲገኝ የአስረጅነት ብቃት ያለው ማስረጃ ተደርጎ
እንደሚወሰድ የማስረጃ ብቃት መስፈርትና የማስረጃ አመዛዘን መርሆች ያሳያሉ፡፡የአካባቢ
ሁኔታ ማስረጃ አንድን የተፈፀመ ወንጀል ለማስረዳት የአስረጅነት ብቃት ያለው ማስረጃ
የሚሆነው ወንጀል ከመፈፀሙ በፉት እና ወንጀሉ ከተፈፀመ በኃላ ስላለው ሁኔታ የተረጋገጡት
ፍሬ ነገሮች (የአካባቢ ሁኔታዎች) ተከሳሽ ወንጀሉን ፈፅሞታል ከሚል እርግጠኛ መደምደሚያ
መድረስ የሚያስችል ይዘትና ባህሪ ያላቸው ሲሆን: የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች ተያያዣነት
ያላቸውና ክፍተት የሌለባቸው ሲሆኑ፤ የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች የተከሳሹን
ወንጀል መስራት የሚያረጋግጡ እንጅ በተቃራኒው ተከሳሹ ንፁህ ነው፣ወንጀሉን አልፈፀመም
ወደሚለው ሎጂካል መደምደሚያ የማይወስዱ ሲሆንና የቀረቡት የአካባቢ ሁኔታ ማስረጃዎች
በማናቸውም የሞራልና የህሊና መመዘኛ ወንጀሉ በተከሳሽ ሳይሆን በሌላ ሰው የመፈጸም
እድልና አጋጣሚ የሌለ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማስረዳት የሚችሉ ሆነው ሲገኙ እንደሆነ
ተቀባይነት ያላቸው የማስረጃ ህግ መርሆች ያሳያሉ፡፡
ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 27(2) የሠጠውን የተከሳሽነት ቃል ተከሳሽ ላቀረበው
ማስረጃ ማስተባበያነት ከተጠቀመበት በዚህ ቃል ውስጥ ተከሳሽን የሚጠቅም ነገር ካለ የተከሳሽን
ቃል ከእነሙሉ ይዘቱ ሊቀበል ይገባል እንጅ ተከሳሽን ጥፋተኛ የሚያስብለውን የቃሉን ክፍል ብቻ
ወስዶ ከጥፋቱ ነፃ የሚያደርገውን ክፍል መተው መሠረታዊ የማስረጃ ምዘና መርህን
ያልተከተለ ነው፡፡
በመሆኑም በተሠሙት የአካባቢ ምስክሮች ወንጀሉን ከተከሳሹ ውጪ ሌላ ሰው ሊፈፅመው
የሚችልበት እድል አለመኖሩን በሚያረጋግጥ መልኩ ካላስረዱ ተከሳሽ ተከላከል ሊባል
አይገባም፡፡ቅጽ/19
(ከተጠቃለሉ የሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉሞች ከቅፅ1-23 መፅሀፍ የተወሰደ)
@Henoktayelawoffice
7.8K viewsedited  07:21
Open / Comment
2022-07-15 08:48:51 ጭብጥ
===============
• ተከራካሪ ወገኖች የተለያዩበት የህግ ወይም የፍሬ ነገር ጉዳይ

ማንኛውም ፍርድ ቤት ባለጉዳዮችን ማከራከር የሚገባው የተለያዩበት የሕግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ምን እንደሆነ አረጋግጦ ለጉዳዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ ስለመሆኑ፣ የነገር ጭብጥ የሚመሰረተው አንደኛው ተከራካሪ ወገን ያመነውን የሕግ ወይም የነገር አግባብ ሌላኛው ተከራካሪ ወገን በማስተባበል የካደ በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጭብጥን ለመመስረት የሚችለውም ከግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር እና ማስረጃ እንዲሁም በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት በሚደረግ ምርመራ በተከራካካሪ ወገኖች የሚሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ የጭብጥ አመሰራረትን በሚደነግጉት ከቁጥር 246 እስከ 248 በተመለከቱት የስነ ስርዓት ሕጉ ድንገጌዎች እንዲሁም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ በክርክሩ የተያዘው ጭብጥ ምን እንደሆነ እና ጭብጡ በአንድ ወይም በሌላ አግባብ የተወሰነበትን ምክንያት በውሳኔው ላይ መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ የፍርድ አጻጻፍን በሚመለከተው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 182(1) ስር በአስገዳጅነት ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 105869 ቅጽ 18፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 182(1)፣ 241፣ 246-248
@Henoktayelawoffice join
7.9K views05:48
Open / Comment
2022-07-15 08:47:43 ወለድ አግድ
==============
• አንድ ባለዕዳ ግዴታውን ለመፈጸም ማረጋገጫ በማድረግ ለገንዘብ ጠያቂው የማይንቀሳቀስ ንብረት ለማስረከብ የሚገደድበት ውል

ማንም ሰው በወለድ አግድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ካስያዘ ወለድ አገዱ የተቋቋመበትን ግዴታ በመፈጸም በማናቸውም ጊዜ ወለድ አገድ እንዲቀር ማድረግ ይችላል፡፡

ሰ/መ/ቁ. 72463 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 3117፣ 3124፣ 3128(2)
@Henoktayelawoffice join
6.0K views05:47
Open / Comment
2022-07-15 08:46:44 የሰበር ሰበርና ተግዳሮቶቹ በኢትዮጽያ
በመሐሪ ረዳኢ
@HenokTayelawoffice Join
5.1K views05:46
Open / Comment
2022-07-15 08:46:44 የጤና ባለሙያዋች ተጠያቂነት
@fenothig1234
4.9K views05:46
Open / Comment
2022-07-15 08:38:41 የጋብቻ_ውል_ስምምነት
# የተጋቢዎች_ስም
1, አቶ ____ _ አድራሻ ______
2, ወ/ት/_______ _ አድራሻ__________
የጋብቻውን ስነስርአት የፈጸምነው እንደ ሀገራችን ባህል መሰረት በፌደራል
ቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 4 መሰረት የአካባቢው
ሽማግሌዎች ባሉበት በሁለታችንም ወገን በመግባባት በዛሬው ቀን የጋብቻ ውል
አድርገናል፡፡
እኔ አቶ ______ የሚገባውን ማንኛውንም ቅድመ ሁኔታ አሟልቼ
በሀገር ልማድ መሰረት ወ/ት______________ አግብቼአለሁ፡፡
እኔ ወ/ት ______ የሚገባውን ማንኛውንም ቅድመ ሁኔታ አሟልቼ
በሀገር ልማድ መሰረት አቶ______________ አግብቼዋለሁ
ይህን የጋብቻ ውል ካደረግንበት ቀን ጀምሮ ማንኛውም የምናገኘውንና
የምናፈራውን ሀብትና ንብረት ሁሉ በፍ/ህ/ቁ 1730 ፣ 1732 ፣ 2005 እና
በፌደራል ቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 42 መሰረት የጋራ
ሀብታችን ነው፡፡
# የተጋቢዎች_ፊርማ
አቶ ___ ወ/ት/__________
# ይህ_የጋብቻ_ውል_ሲደረግ_የነበሩ_ምስክሮች
በአቶ. በኩል በወ/ት_____ በኩል
1. ____ 1, ____
2. ____ 2, ____
እኛም ምስክሮች ሁለቱም ተጋቢዎች ሲፈራረሙ ያየን መሆናችንን በፊርማችን
እናረጋግጣለን፡፡
____________________________________
ከዚህም በተጨማሪ ከጋብቻ በፊት የነበራቸዉን የግል ንብረት ቀጣይ እጣ ፈንታ
እና ከጋብቻ በኋላ ስለሚያፈሩት የጋራ ንብረት አስተዳደር በተመለከተ ተጋቢዎች
በጋብቻ ዉል ዉስጥ አካተዉ መዋዋል ይችላሉ

ሌሎች ፎርሞችን ለማግኘት #join


@Henoktayelawoffice
@Henoktayelawoffice

Share
5.0K viewsedited  05:38
Open / Comment