Get Mystery Box with random crypto!

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Logo of telegram channel nesiha_ouserya — 🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺
Channel address: @nesiha_ouserya
Categories: Education
Language: English
Country: Ethiopia
Subscribers: 2.48K
Description from channel

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة
ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን!
ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት
በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን!
እናመሰግናለን!
@nesiha_ouserya

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages

2022-08-29 21:01:44 በትዳር ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችና ሸሪአዊ መፍትሄዎቻቸው

አቡ ጁነይድ ሳላሕ አሕመድ

Share Link
https://t.me/abujunaidposts/188
----------------
የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts
465 views18:01
Open / Comment
2022-08-28 07:59:42 ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!

☞ለባለ ትዳሮች ምክር

አግብተህ ከሆነ ከትዳር አጋርህ ጋር ስለ ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!

በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ታማኝ ከትዳር ህይወት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!

በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!

ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማድረግ ባለቤቷን ማስደሰት አለባት!

እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህችን አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ! ጀግና ሁን/ሁኚ!

በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል። አስተንትን! በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ!
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታድርጋቸው!

ኢብኑ'ል ወርዲይ በግጥማቸው እንዲህ ብለዋል ፦
إنَّ أحلى عيشةٍ قضيتُها
ذهبتْ لذاتُها والإثمُ حلْ

ስሜቴን ያራገፍኩባቸው ጣፋጭ ግዜያቶች
ጥፍጥናቸው ሄዷል ወንጀሉ ግን ቀርቷል/ተመዝግቧል


ሁላችንንም አላህ ለሚወደው ይምራን!


https://t.me/abdurezaq27
370 viewsedited  04:59
Open / Comment
2022-08-28 07:55:51 ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!

☞ለላጤዎች ምክር!

ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!

ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!

ማግባት ካልቻልክ ትርፍ የምትለውን ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ ስፖርት በመስራት፣ መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......

በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብ

አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያደርግህ ተማፀን!

መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!

ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር! መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!
327 views04:55
Open / Comment
2022-08-28 07:53:22 ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!

☞ ከዚህ ከምትመለከተው ቀፋፊ ምልከታ እውነተኛ ተውበት አድርገህ ወደ አላህ ካልተመለስክ እጅግ ከባድ ዋጋ ለወደፊት እንደሚያስከፍልህ ታውቃለህ?

☞እጅግ የምትወደውና የምትቀርበው ሰው ሞት ዜና ይህን ነገር እየተመለከትክ ብትሰማ ትወዳለህ?

☞ ከዚህ ወንጀል አፀያፊነት የተነሳ አላህ መሬትን ደርምሶ ሊያስውጥህ እንደሚችል ታውቃለህ?

☞በዚህ ቀፋፊ ምልከታ ላይ ሆነህ ሞት ሊመጣህ እንደሚችል ታውቃለህ? አስከፊ ኻቲማ ሊያስደነግጥህ እንደማይችል እርግጠኛ ነህ?

☞ጌታህ ቻይ ነው! ለግዜው ይተውኃል፤ ነገር ግን በምትሰራው ወንጀል ደስተኛ ሆኖ እንዳይመስልህ! ከዚህ ወንጀልህ ተውበት ካላደረክ ለወደፊትም ቢሆን ከባድ መከራ ትጋረጣለህ!

☞ የዒባዳህን ጥፍጥና እንደሚያሳጣህ አምልኮ ላይ ደካማ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

ለዒባዳ በቆምክ ቁጥር የምታያቸው ምስሎች አዕምሮህን ተቆጣጥረው እንደሚፈታተኑህ ታውቃለህ? በዚህም ከአምልኮ መሸሽና ተስፋ ቢስነት ሊሰማህ ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ አደገኛው አዘቅት ክህደት የሚጎትት ጠንቅ ነው።

☞ ራስህን የምትጠላ የወንጀል ምርኮኛ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞ለአላህ ብሎ አንዳች ነገርን
የተወ ሰው አላህ የተሻለ መልካም ነገር እንደሚተካለት ታውቃለህ?

☞አላህ በባሪያው መመለስ የሚደሰት የተብቃቃና ምስጉን ጌታ መሆኑን ታውቃለህ?

☞ከወንጀል ጥብቅ ከሆንክ አላህ ከችሮታው እንደሚያብቃቃህ ታውቃለህ?

☞ለደቂቃዎች (ሻህዋ) ስሜት ተብለው የሚሰሩ ወንጀሎች የአመታት ቅጣት እንደሚያመጡ ታውቃለህ?

☞ዛሬ በዱንያ ላይ የምትሰራቸው ወንጀሎች፦ የተከለከለን ማየት፣ መስራትና ሌሎችንም በዱንያ ላይ ቅጣቱን በድህነት፣ በአደጋ፣ ሪዝቅህን በመከልከል በቤተሰብህ፣ በልጆችህና በቅርብ ሰዎች ላይ አደጋ ሊከስት እንደሚችል ታውቃለህ?

☞ይህ ወንጀል አእምሮህን ተቆጣጥሮ ከምትመለከታት ሴት ሁሉ ቀፋፊው ዝሙት ላይ ለመወደቅ እንደሚገፋፋህ ታውቃለህ?
322 viewsedited  04:53
Open / Comment
2022-08-28 07:51:49 ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!

☞ይህ ወንጀል አላህ ዘንድ ወራዳ ሰው እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞የእነዚህ ዝሙተኞች ምስል አእምሮህ ላይ ተቀርፇል? (ይህ የአላህ ቁጣ ምልክት ነው!)

☞እነዚህን ነገሮች መመልከት ትንንሽ ነገሮችን ሁሉ የምትሰጋ ፈሪና ልፍስፍስ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞ይህን እርቃን ብልግና የምትመለከት ሆይ! የሸሪዓ እውቀትን ብርሃን በፍፁም ማግኘት እንደማትችል ታውቃለህ?

☞በዚህ ወንጀልህ ከምትወዳትና ከምትወድህ የህይወት አጋርህ ባለቤትህ ጋር የተረጋጋ ህይወት መኖር እንደምትነፈግ ታውቃለህ?

☞ይህን አስቀያሚ ተግባር የምትመለከት ከሆነ ደጋግ የአላህ ባሪያዎች ይህን ቀፋፊ ተግባርህን ባትነግራቸውም እንኳን ሊጠሉህ እንደሚችሉ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞችን ማየት ግዴታ የሚሆንብህ በዝሙት ወንጀላቸው በድንጋይ ተወግረው ሲገደሉ ብቻ እንደሆነ ታውቃለህ?
285 viewsedited  04:51
Open / Comment
2022-08-28 07:47:55
ልቅ የሆኑ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን በመመልከት ለተለከፉ ሁሉ!

እነዚህ ፊልሞችና ምስሎች የጀሀነም በሮች ናቸው!

እነዚህን የበከቱና የተግማሙ ዝሙተኞችን በማየት እስረኛ የሆንክ/ሽ ሁሉ በዚህ ሰበብ ምን እንደሚከተልህ/ሽ ተከታዩን እስተውለህ/ሽ አንብብ/ቢ!

☞ለላጤዎችና ለባለትዳሮች መጨረሻ  የተቀመጠውን መፍትሄ በጥሞና አንብቡት!

☞የተራቆቱ ዝሞተኞችን ማየት እጅግ ከባባድ ወንጀሎች ውስጥ እንደሚካተቱ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት ውርደትና ደካማነት እንደሚያወርስ ታውቃለህ?

☞እነዚህን ዝሙተኞች መመልከት በሰዎች አይን ያነስክና ወራዳ እንደሚያደርግህ ታውቃለህ?

☞እነዚህን አፀያፊ ምስሎችና ቪድዮዎች በማየት የተለከፈ ወጣት በቀላሉ ካገኘው ተቃራኒ ፆታ ጋር ሁሉ ዝሙት ላይ  የሚወድቅ ይሆናል። እንዲሁም ራስን ወደ ማርካት (masturbation) ሱስና የስንፈተ ወሲብ አደጋ ተጋላጭ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።

☞እነዚህን የዝሙት ዌብሳይቶችና የቪድዮ ምስሎች መመልከት በአእምሮህና በአይንህ ላይ ድክመትን እንደሚከስት ታውቃለህ?  ይህን በመመልከት ሱሰኛ የሆነ ሰው ቀለል ያሉ ጉዳዮችን በቀላሉ ይረሳል። ይህ አደጋ እያደገ ሲሄድ የአእምሮ ድክመት አስከትሎበት እንዴት መናገር እንዳለበት ሁሉ ላያውቅ ይችላል! ሌሎችም ብዙ የጤና እክሎች ያጋጥሙታል!
322 views04:47
Open / Comment
2022-08-20 08:20:42 ደረሰ
ነሲሓ የወንድ ታዳጊዎችና ወጣቶች ልዩ የክረምት ኮንፈረንስ

ወጣት የነብር ጣት! የዲኑ የጀርባ አጥንት!

ታዳጊ እና ወጣት ወንዶችን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ድንቅ ኮንፈረንስ!

በዕለቱ የተለያዩ ወሳኝ ርዕሶች የሚዳሰሱ ሲሆን

ዐቂዳ እና ቁሳዊነት

የቁሳዊነት ጭለማ በእምነት ብርሃን የሚገፈፍበት። ዘመን አይሽሬ ኢስላማዊ መፍትሄ የሚሰጥበት።

በአንጋፋው ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

መዝናናት እና መደሰት በሸሪዓ ሚዛን

መዝናናት ምንድን ነው? እውን ኢስላም መዝናናትና መደሰትን ከልክሏል? እና መሰል ጥያቄዎች ከመድረኩ መልስ ያገኛሉ!

ለወጣቶች በወጣቱ ኡስታዝ ዐብዱረዛቅ ፈረጃ

በተጨማሪም

በሌሎች ዳዒዎች እና ባለ ተሰጥኦ ወጣቶች ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ!

እንዲሁም:

☞ልዩ ዶክመንተሪ

☞ "የነብዩላህ ዩሱፍ ዐለይሂ ሰላም ድንቅ ፅናት" ልዩ በሆነ አቀራረብ ተካቷል።

ፒያሳ በሚገኘው ኸሊፋ አዳራሽ

ቀን: እሁድ ነሐሴ 15 / 2014

ከጠዋቱ 3:00 - 6:30

መግቢያ በነፃ

ከእናንተ የሚጠበቀው ማስታወቂያውን ያልሰማ ወንድማችሁን ይዞ መምጣት ብቻ!

https://t.me/darulhadis18
713 views05:20
Open / Comment
2022-08-18 20:20:36 ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን (رحمه الله)

"አንዳንድ ሴቶች እንደሚያረጉት የቤታቸውን ሚስጥርና የትዳር ህይወታቸውን የተመለከቱ ነገሮችን ለዘመደኞችና ለጓደኞች ማሰራጨት የተከለከለ ነው።
ለሴት ልጅ የቤቷን ሚስጥርና ከትዳር አጋሯ ጋር ያላትን ግንኙነት ለየትኛውም ሰው መርጨት አይፈቀድላትም።"

فتاوى الإسلامية 212/3

አብዱረዛቅ አል ሐበሺይ

የሱና እህቶች የለውጥ ሚና
https://t.me/yeswnaehitochmena
872 views17:20
Open / Comment
2022-08-18 19:53:06 እንዳያመልጥሽ
ሴቶች ለሴቶች የሙሀደራ ፕሮግራም

በተለመደው ወርሃዊ የሙሀደራ ፕሮግራማችን በአላህ ፈቃድ፦

እምነታችን

የልብ በሽታዎች እና መድሀኒታቸዉ
እንዲሁም አስተማሪ መነባንብ ይቀርባል።


ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ቅዳሜ ነሐሴ 14፣2014

ከጠዋቱ 3:00-6:00
ቀጠሮአችን በኢማሙ አህመድ መስጂድ ይሁን።

አድራሻ: አለም ባንክ/ አንፎ አል-ጋዚ አደባባይ

መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!


https://t.me/darulhadis18
650 views16:53
Open / Comment