Get Mystery Box with random crypto!

ጉባኤው በወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት አወገዘ! በጥ | YeneTube

ጉባኤው በወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት አወገዘ!

በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን አስነዋሪ ድርጊት እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ።

ጉባኤው በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር የተፈጸመውን ሕገወጥ ድርጊት በመቃዎም መግለጫ አወጥቷል።

በመግለጫው ሃይማኖቶች የትኅትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሰረቶች ናቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሰረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃዎማለን ነው ያለው።

ጥር 12 በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በሕግ ማስከበር ሽፋን በቤተክርስቲያኗ ላይ የተቃጣው ድርጊት ፍጹም ሕገ ወጥ ነው ያለው መግለጫው መንግሥት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቋል።

መንግሥት የሃይማኖትን እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀው የጉባኤው መግለጫ የሕይዎት፣ የአካል እና የመንፈስ ስብራት በደረሰባቸው ወገኖች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘንም በተሰበረ ልብ እንገልፃለን ነው ያለው።

መንግሥት ቀድሞ ባወጣው መግለጫ በተፈጠረው ክስተት፣ በደረሰው የሞትና ከባድ የአካል ጉዳት እንዳዘነ አስቀድሞ ጉዳዩን አጣርቶ አጥፊዎችን ለሕግ እንደሚያቀርብ አሳውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa