Get Mystery Box with random crypto!

'በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ 1.4 ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት ርብርብ እየተደረገ ነው”፦ የክልሉ | YeneTube

"በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ 1.4 ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት ርብርብ እየተደረገ ነው”፦ የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ቢሮ

በሶማሌ ክልል በድርቁ ምክንያት በሰዎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ እንዲሁም ሰዎች በድርቁ ምክንያት ለረሃብ እንዳይጋለጡ በተሠራው ቅንጅታዊ ተግባር አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ አህመድ አስታወቁ።

አቶ አብዱልፈታህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በሶማሌ ክልል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተከሰተው ድርቅ ሰዎችን ከቦታ ቦታ እያፈናቀለ እንስሳትን ደግሞ እየገደለ ነው።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከ235 ሺ 700 በላይ እንስሳት በዚህ ድርቅ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል።
በክልሉ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሕዝብ ደግሞ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለከፋ ጉዳት ተጋልጧል ብለዋል።

የክልሉ መንግሥት ችግሩን ለመቋቋም ከተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በቅንጅት በመሆን በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን በዚህም ለእንስሳቱ የሚውሉ የተለያዩ የመኖ ዓይነቶችን በማሰባሰብ ከ19 ወረዳዎች በላይ ማዳረሱን አብራርተዋል።

በተለይ የግብርና ሚኒስቴርና የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በጋራ በመሆን በአብዛኛው የአካባቢው ማህበረሰብ የአርብቶ አደር እንደመሆኑ ማህበረሰቡ በእንስሳት ላይ በሚደርሰው ጉዳት ቀጥተኛ ተጋላጭ እንዳይሆን የእንስሳት ሀብቱ ሕይወት እንዳያልፍ የመታደግ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa