Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ የቻይና አየር መንገዶች ላይ የበረራ እገዳ ጣለች! የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀው እገዳ | YeneTube

አሜሪካ የቻይና አየር መንገዶች ላይ የበረራ እገዳ ጣለች!

የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀው እገዳው ከፊታችን ጥር 22 እስከ መጋቢት 20 ድረስ የሚቆይ ሲሆን፤ አጠቃላይ 44 በረራዎች እንዲቋረጡ የሚያደርግ ነው።

በክልከላው በተለይም አራት የቻይና አየር መንገዶች ማለትም ዢመን፣ ኤር ቻይና፣ ቻይና ሰሳውዘርን እና ኢስተርን የተባሉ አየር መንገዶች የሚጎዱ መሆኑ ታውቋል።

የቻይና ባሳለፍነው ወር 20 የዩናትድ አየር መንገድ፣ 10 የአሜሪካን አየር መንገድ፣ እና 14 የዴልታ አየር መንገድ በረራዎችን ከኮሮና ጋር በተያየዘ ማገዷ የሚታወስ ሲሆን፤ የአሜሪካ ውሳኔም ለቻይና እርምጃ አጸፋ መሆኑ ተነግሯል።

[Alain]
@YeneTube @FikerAssefa