Get Mystery Box with random crypto!

21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው፣በወንዶች ደግሞ | YeneTube

21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው፣በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ አሸናፊ ሆነዋል።

25 ሺህ ሯጮች የሚሳተፉበት 21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመዲናችን በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው።የ21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ከጎረቤት አገሮች የመጡ አትሌቶች እና የሩጫው ተሳታፊዎች ተገኝተዋዋል።

በተካሄደው የአትሌቶች ሩጫ በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው 1ኛ ስትወጣ ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር 2ኛ ፣መልክናት ውዱ 3ኛ ውድድሯን አጠናቃለች።

በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ 1ኛ ሲወጣ ፣አትሌት ጌታነህ ሞላ 2ኛ፣ አትሌት ቦኪ ድሪባ 3ኛ ደረጃን አግኝቷል።ሩጫው እየተካሄደ ያለው “መጸዳዳት በሽንት ቤት” በሚል መሪ ቃል ነው።ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረውን የ2014 ቶታል ኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፥ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa