Get Mystery Box with random crypto!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ዓመት በላይ ምንም አይነት የ | YeneTube

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁለት ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት ከሁለት ዓመት በላይ ምንም አይነት የመብራት አገልግሎት እንዳላገኙ ተነገረ፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መለሰ በየነ ለአሐዱ እንዳሉት ባለፉት ዓመታት በመተከል እና ካማሽ ዞኖች በታጣቂዎች የተስተጓጎለው የመብራት አገልግሎት መፍትሔ ሳያገኝ እስካሁን ድረስ ዘልቋል ብለዋል፡፡

በዚህም ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርጓል፤በተለይም በከተሞች አካባቢ በመብራት ኃይል ብቻ ስራቸውን የሚሰሩ ዜጎችን ለስራ አጥነት ተጋላጭ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡

ችግሩ መቼ መቋጫ ይሰጠዋል ስንል ላነሳንላቸው ጥያቄም በቀጣይ የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ሲስተካከል እግር በግር በመከተል ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመመለስ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

[አሐዱ]
@YeneTube @FikerAssefa