Get Mystery Box with random crypto!

ህወሓት በድጋሚ በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት መክፈቱን የአፋር ክልል አስታወቀ! አሸባሪው ህወሓት በ | YeneTube

ህወሓት በድጋሚ በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት መክፈቱን የአፋር ክልል አስታወቀ!

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ውስጥ ገብቶ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ አሁንም በኪልበቲ ረሱ ዞን ጦርነት መክፈቱን የክልሉ መንግስት አስታቋል፡፡የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ የሸብር ቡድኑ በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል በአብአላና በመጋሌ ወረዳ የከፈተውን ውጊያ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ምንም አይነት ሰብዓዊነትና ርህራሄ ፈፅሞ የሌለው አሸባሪ ቡድኑ በንፁሀን ዜጎች ላይ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ እያሸበረ ይገኛል ነው ያለው መግለጫው፡፡
 
ሁሌም ከትንኮሳ አርፎ የማያውቀው የሽብር ቡድኑ ለዘመናት የቆየውን በድንበር የሚዋሰኑ የአፋር እና የትግራይ ክልልች ህዝቦችን ግንኙነት ከምንም ሳይቆጥረው ሁለቱን ህዝቦች በማጋጨት የማይረባ ትርፍ ለማግኘት ሌት ተቀን እየጣረ ይገኛል፤እያደረሰ ባለው ጥቃትም የአፋር ንፁሃን ኢላማ በማድረግ የሽብር ተግባሩን በማስፋት ላይ ነው ብሏል፡፡

በዛሬው እለት እንኳን በኪልበቲ ረሱ ዞን በተለያዩ ቦታዎች የአፋር ክልልን ወሰን ጥሶ በመግባት በአብአላ፣ በመጋሌ እና በበራህሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በመክፈት በርካታ ንፁሃንን ለጉዳት ዳርጓልም ነው ያለው መግለጫው።
ይሁንና ሁሌም በማጭበርበርና በውሸት ፕሮፖጋንዳ እድሜውን የሚያራዝመው ጁንታው በአፋር ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በኩል ዘልቆ በመግባት ንፁሀን የጎዳ ቢሆንም ጥቃት እንደተፈፀመበት አስመስሎ በማቅረብ አሁንም ማደናገሪያውን እየነዛ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa