Get Mystery Box with random crypto!

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ተሽከርካሪዎች በከተሞች የመንገድ አገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ | YeneTube

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ተሽከርካሪዎች በከተሞች የመንገድ አገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ የሚያስችል ሕጋዊ ሥርዓት እየዘረጋ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ሚንስቴሩ የመንገድ አገልግሎት ክፍያ ሥርዓቱን በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለመዘርጋት ባሕርዳር፣ አዳማ እና ድሬዳዋ ከተሞችን በናሙናነት ወስዶ የጀመረው ጥናት የመጨረሻው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ሥርዓቱ በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ጠቁሟል። ጥናቱ በተሽከርካሪዎች ምልልስ መጠን እና ተሽከርካሪዎች በመንገዶች ላይ በሚፈጥሩት ጫና ላይ ያተኮረ እና የመንገዶች መጠገኛ ወይም መልሶ መገንቢያ ገንዘብ በአገልግሎት ክፍያው የሚሸፈንበትን አሠራር የሚዘረጋ እንደሆነ ተገልጧል። የመንገድ አገልግሎት ክፍያ ሥርዓቱ ዓላማ የከተሞችን ገቢ ማሳደግ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa