Get Mystery Box with random crypto!

ኦፌኮ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ባለፉት ጥቂት ወራት በኦሮሚያ ክልል 297 ሰዎችን ገድለዋል ሲል ዛ | YeneTube

ኦፌኮ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ባለፉት ጥቂት ወራት በኦሮሚያ ክልል 297 ሰዎችን ገድለዋል ሲል ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መናገሩን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። በክልሉ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በገባበት ግጭት ከግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ተፈናቅሏል በማለት ኦፌኮ በመግለጫው ጨምሮ ገልጧል። የፓርቲው መግለጫ ትኩረት ተባብሰው ቀጥለዋል ባላቸው የርስበርስ ግጭት፣ የፖለቲካ ውድቀትና የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ ነው። አገሪቱ ከቀውስ የምትወጣው፣ ግጭቶችን አቁሞ ወደ ፖለቲካዊ ድርድር በመመለስ እንደሆነ ፓርቲው ገልጧል።

@YeneTube @FikerAssefa