Get Mystery Box with random crypto!

የዘኢኮኖሚስት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የስራ ፈቃድ ተሰረዘ! የዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት ዘጋቢው ቶም ጋ | YeneTube

የዘኢኮኖሚስት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር የስራ ፈቃድ ተሰረዘ!

የዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት ዘጋቢው ቶም ጋርድነር በኢትዮጵያ የነበረው የሥራ ፈቃድ መሰረዙን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አስታውቋል።ባለስልጣኑ ለጋዜጠኛው በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዳስታወቀው፤ ጋዜጠኛው ከሙያ ስነ ምግባር ውጭ በተደጋጋሚ ሲሰራ በመገኘቱ ተደጋጋሚ የቃል እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል።

በተጨማሪም ከጋዜጠኛው ጋር ውይይት በማድረግ ከስህተቱ እንዲታቀብ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ባላስልጣኑ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ቶም ጋርድነር የሙያውን ስነ ምግባር በማክበር ለመስራት ባለመቻሉ ከዛሬ ግንቦት 5 ቀን 2014 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ የነበረው የጋዜጠኝነት የስራ ፈቃድ መሰረዙንና ከዚህ በኋላ በጋዜጠኝነት ስራ በኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እንደማይችል ባለስልጣኑ አስታውቋል።

ዘ ኪኮኖሚስት በዚህ ጋዜጠኛ ምትክ ሌላ የሙያውን ሥነ ምግባር አክብሮና ገለልተኛ ሆኖ መስራት የሚችል ሰው መድቦ ማሰራት እንደሚችልም ባለስልጣኑ በዚሁ ደብዳቤ ላይ ገልጿል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa