Get Mystery Box with random crypto!

‹‹አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝ | YeneTube

‹‹አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ››
-የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሃይሌ ተናግረዋል፡፡

መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በሚፈጽሙ የመንግስት ሰራተኞችም ሆነ ሃላፊዎችን ተጠያቂ በማድረጉም ሆነ ባለማድረጉ ፣ ከህዝብ የበለጠ ተጎጂ ስለሆነ ተጥያቂነት ማንበር እንደሚገባው በአፅንኦት ተናግረዋል።

ሃላፊው ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተገኝተው ለህግ ፣ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ 10 ወራት የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡

ዋና ዕንባ ጠባቂው ከቋሚ ኮሚቴዉ አባላት ከተጠያቂነት አንጻር ለተነሳላቸዉ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ መመረጥ እና በስልጣን ላይ መቆየት የሚፈልግ ከሆነ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ሰራተኞች እና ሃላፊዎች ላይ እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባውና ጠቀሜታው ለራሱ እንደሆነ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

በተያያዘም ዶ/ር እንዳለ " እኛ እንደ አንድ ዴሞክራሲ ተቋም እንዲሁም የተከበረዉ ምክርቤት ማድረግ የሚችለዉ ነገር ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል ህግ እና ደንብ እንዲሁም ስርዓት፣ መመሪያ ወይም አዋጆችን ማዉጣት ነዉ፤ ከዛ ባለፈ የወጡ አዋጆችን ወይም ደንቦችን የመፈጸም ሃላፊነት ያለበት ግን የመንግስት አስፈጻሚ አካል ነዉ "ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በነዚህ ምክረሃሳቦች ላይ መግባባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በማንሳት መግባባት ከሌለ ግን ምክር ቤቱ ብዙ ህግ ቢያወጣ ፤ የዴሞክራሲ ተቋማት ምክረሃሳቦችን ቢሰጡ እና መፈጸም ባይችሉ ፤ መንግስት ተጎጂ እሆናለዉ ብሎ በማሰብ የበለጠ ቢሰራ የተሻለ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa