Get Mystery Box with random crypto!

በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ! ከሚያዝ | YeneTube

በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ!

ከሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ በነዳጅ ጭማሪ ምክንያት በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡በዚህም መሠረት ነባር ታሪፍ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ በአስፋልት መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 493 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር ብር 0 ነጥብ 532 ሆኗል፡፡

ደረጃ አንድ በጠጠር መንገድ በሰው በኪሎ ሜትር ታሪፍ 0 ነጥብ 548 የነበረው ወደ 0 ነጥብ 596 ከፍ ብሏል፡፡ በሌላ በኩል በደረጃ ሁለት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 457 የነበረው በአዲሱ ታሪፍ በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 496 መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በደረጃ ሁለት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎሜትር 0 ነጥብ 505 የነበረው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 039 ጭማሪ በማድረግ በአዲሱ በኪሎ ሜትር 0. ነጥብ 554 መደረጉ፤ደረጃ ሦስት በአስፋልት መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 416 ይከፈልበት የነበረው 0 ነጥብ 039 በኪሎሜትር ጭማሪ በማድረግ 0 ነጥብ 455 በኪሎሜትር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ደረጃ ሦስት በጠጠር መንገድ ነባር ታሪፍ በሰው በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 471 የበነረው በኪሎ ሜትር የ0 ነጥብ 049 ጭማሪ በማድረግ በኪሎ ሜትር 0 ነጥብ 520 ሆኗል፡፡ የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ በ100 ኪሎ ሜትር ሲታይ በደረጃ አንድ ተሽርካሪ ለአንድ ሰው በነባር ታሪፉ በአስፋልት መንገድ ብር 49 ነጥብ 29 ይከፈል የነበረው በአዲሱ ብር 53 ነጥብ 16 ሆኗል፡፡ ይህም በ100 ኪሎ ሜትር ጭማሪ ያደረገው የብር 3 ነጥብ 87 ነው፡፡በደረጃ ሁለት ተሽከርካሪዎች ለአንድ ሰው በነባር ታሪፍ በ100 ኪሎ ሜትር 45 ነጥብ 70 ያስከፍል የነበረው በ100 በኪሎ ሜትር ብር 3 ነጥብ 87 በመጨመር 49 ነጥብ 58 በ100 ኪሎ ሜትር ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ በደረጃ ሦስት ተሸርካሪ በ100 ኪሎ ሜትር ለአንድ ሰው ብር 41 ነጥብ 61 ያስከፍል የነበረው በ100 ኪሎ ሜትር የ3 ነጥብ 88 ጭማሪ በማድረግ በ100 ኪሎ ሜትር ብር 45 ነጥብ 49 መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa