Get Mystery Box with random crypto!

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአገሪቱ ምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ተፋሰሶች ላይ የተሻለ የዝናብ ሁኔታ እን | YeneTube

በሚቀጥሉት አሥር ቀናት በአገሪቱ ምዕራብና የደቡብ ምዕራብ ተፋሰሶች ላይ የተሻለ የዝናብ ሁኔታ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ በአገሪቱ የምዕራብ አጋማሽ አካባቢዎች እየተስፋፋ ይሄዳል ብሏል።እነዚሁ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ እንደሚያገኙም የሚቲዎሮሎጂ ትንበያዎች ያመለክታሉ ነው ያለው።የዝናቡ ሁኔታ በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ ከሞላ ጎደል ቀጣይነት እንደሚኖረውም አመልክቷል።

በእነዚሁ ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የሚቲዎሮሎጂ ክስተቶች ቀጣይነት እንደሚኖራቸውም ተጠቁሟል።ይህም በተለያየ የዕድገት ደረጃዎች ላይ ለሚገኙ የበልግ ሰብሎችና ለቋሚ ተክሎች የውሃ ፍላጎትን ለማሟላት ይረዳልም ተብሏል።

በአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ለግጦሽና ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሻሻል የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም ነው የገለጸው።በተጨማሪም ለመኸር ግብርና ዝግጅት መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥርም ኢንስቲትዩቱ አመላክቷል::

@YeneTube @FikerAssefa