Get Mystery Box with random crypto!

መንግስት ለአምራች ኢንደስትሪው የመሬት ፖሊሲውን ቀየረ! በዚህም መሰረት ለአዳዲስ አምራች ኢንደስ | YeneTube

መንግስት ለአምራች ኢንደስትሪው የመሬት ፖሊሲውን ቀየረ!

በዚህም መሰረት ለአዳዲስ አምራች ኢንደስትሪዎች የተመቻቸ መሰረተ ልማት ባላቸው የኢንደስትሪ ፓርኮች ውስጥ ቦታ ይመቻቻል ተብሏል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዳሉት አሁን ላይ ለሚታየው ምቹ የቢሮክራሲ ጥያቄ እና ብልሹ አሰራር የመሬት ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡

በመሆኑም ይህን ችግር ለመቅረፍ ከዚህ በኋላ በኢንደስትሪው ዘርፍ ለመሰማራት ለሚፈልግ ኢንቨስተር በከፍተኛ ሃብት በተገነቡ ግን በበቂ ባልተያዙ የኢንደስትሪ ፓርኮች ቦታይመቻቻል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባም ሆነ በክልሎች ለኢንደስትሪው ዘርፍ መሬት አይቀርብም፤ ለብልሹ አሰራር በር አይከፈትም ብለዋል፡፡ባለፉት ጥቂት አመታት ብቻ 13 የኢንደስትሪ ፓርኮች እና ሶስት የግብርና ማቀነባበሪያዎች የተገነቡ ቢሆንም በባለሃብቶች ሙሉ ለሙሉ አልተያዙም፡፡

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa